TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከትምህርት ሚኒስቴር⬇️

ሰሞኑን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለቀጣዩ 15 ዓመት የሚሆን የትምህርትና ሥልጠና ፍኖተ-ካርታ ረቂቅ የጥናት ሰነድ ላይ የመጀመሪያውን #ውይይት እያካሄደ መሆኑ እየታወቀ አንዳንድ የማህበራዊ ድረ-ገፅ ተጠቃሚዎች ግን ጥናት አጥኝዎች ለውይይት ያቀረቡትን ሃሳብ ብቻ በመያዝ #መላው የሃገራችን ህዝብ ውይይት አድርጎ ይሁንታ ባላገኘውና ባልፀደቀው ሃሳብ በመንተራስ ለህብረተሰቡ መረጃ እያሰራጩ መሆኑ ታይቷል ።

ስለዚህ ህብረተሰቡ በመረጃው ሳይዛባ በተጠናው ረቂቅ ሰነድ መነሻነት በባለቤትነት #በመሳተፍ ለሃገራችን የትምህርትና ሥልጠና ፍትሃዊ
ተደራሽነት፣ አግባብነትና ጥራት መረጋገጥ የበኩሉን እንዲወጣ በዚህ አጋጣሚ በድጋሜ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ።

በመጨረሻም ውይይቱ #ከመስከረም መጀመሪያ ጀምሮ እስከ #ታችኛው የህብረተስብ ክፍል የሚተገበር ይሆናል። በሚደረገው ውይይትም መግባባት ሲደረስ የ15 ዓመት የፍኖተ-ካርታው ዝግጅት ተጠናቆ በሚመለከተው አካል #መፅደቅ ሲችል ብቻ ተግባራዊ እንደሚሆን ትምህርት ሚኒስቴር ያሳውቃል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
7 ዓመታትን ያለ ኤሌክትሪክ . . .

ለ7 ዓመታት ኤሌክትሪክ በተቋረጠበት የቤንሻንጉል ጉሙዝ ፤ ካማሽ ዞን ነዋሪዎች " የከፋ ችግር ላይ " ስለመሆናቸው ቪኦኤ ሬድዮ ነዋሪዎችን ዋቢ በማድረግ ዘግቧል።

አቶ ለማ ሮሮ የተባሉ የካማሽ ዞን፤ ካማሽ ከተማ ነዋሪ ከ2010 ዓ/ም ጀምሮ ምንም አይነት የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንዳላገኙ  ገልጸዋል።

የኤሌክትሪክ እንዲጀምር ጥረት ቢደረግም ማታ ማታ ታጣቂዎች መስመሮች እየቆረጡ እንደሚያስቸግሩ በዚህም በመብራት የሚሰሩ ስራዎችን ለማከናወን መቸገራቸውን አስረድተዋል።

አሁን ያለውን ከፍተኛ ችግር ለመወጣት ስንል ነዳጅን በመጠቀም በጃነሬተር ለመስራት ጥረት እያደረግን ቢሆንም ነዳጅ ማግኘት በራሱ ፈተና መሆኑን ገልጸዋል።

በመብራት ምክንያት ኔትዎርክም እያስቸገረ መሆኑን አክለዋል።

አቶ ዳንኤል አየለ የተባሉ ነዋሪ ፤ ለዚህ ሁሉ ዓመታት የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተቋርጦ መቆየቱ መንግሥት ለችግሩ ትኩረት አለመስጠቱ ማሳያ ነው ብለዋል።

መንግሥት ሁሌም " የፀጥታ ችግር " ን እንደምክንያት ቢያነሳም እኔ የማስበው ግን ትኩረት ያለመስጠት ነው ሲሉ ገልጸዋል። ባለው ሁኔታ ችግር ውስጥ ነን ሲሉ አስረድተዋል።

ሌላ ነዋሪ ደግሞ ኤሌክትሪክ ከተቋረጠ #ከ6_ዓመት በላይ መሆኑና በህክምና ተቋማት ላይ ከባድ ተፅዕኖ እንዳሳደረ ገልጸዋል። በ5 ወረዳ ውስጥ ኔትዎርክ እንደማይሰራ ፣ ካማሽ ላይም በተቆራረጠ ሁኔታ እንደሚሰራ ፣ ባንክም አንዳንድ ጊዜ አስቸጋሪ ነው ሲሉ አክለዋል።

ሰዎች የባንክ አገልግሎት ፍለጋ 2 እና 3 ቀናት በእግር ተጉዘው ነው ካማሽ የሚመጡት ፤ ተማሪዎችም ለማጥናትም እንደተቸገሩ ነው ሲሉ አብራርተዋል።

በአካባቢው ፀጥታ ከደፈረሰበት 2010 በፊት ችግር መኖሩን ያነሱት እኚሁ ነዋሪ የሚዘረጉትን የኤሌክትሪክ መስመሮች የሚቆራርጡ አካላትን " ላይተው እንደማያውቁ " ገልጸዋል።

የካማሽ ዞን ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ጀርሞሳ ተገኝ ፥ በዞኑ አምስት ወረዎች እና አንድ የከተማ አስተዳደር እንዳለ ገልፀው ከ300 ሺህ በላይ ነዋሪዎች ከ2008 አጋማሽ አካባቢ አንስቶ መብራት መቆራረጥ እንዳጋጠማቸው ከግንቦት ወር በኃላ ግን ሙሉ በሙሉ መጥፋቱን አስረድተዋል።

አቶ ጀርሞሳ ተገኝ ለውጡን ተከትሎ በሀገሪቱ በተለያየ አካባቢ በተፈጠረ የፀጥታ ችግር የመብራት ኃይል ስራውን ማከናወን ስላልቻለ በአሁን ወቅት #መላው የዞኑ ማህበረሰብ የመብራት ተጠቃሚ እንዳልሆነ ገልጸዋል።

ቡድን መሪው ፤ " አሁን ካማሽ ከተማ ላይ ባንክ አለ ፣ ቴሌ አለ ጄነሬተር በ500 ሺህ ፣ በሚሊዮንም ገዝተው ያመጣሉ ጄነሬተሩ እራሱ እየተበላሸ ከፍተኛ እንግልት ነው እየደረሰባቸው ያለው። " ብለዋል።

" ነዳጅ በብላክ ማርኬት/ጥቁር ገበያ ነው የሚገዛው ዋጋው ደግሞ ከጣም ውድ ነው " የሚሉት ቡድን መሪው " ኮምፒዩተር ቤቶች አሉ፣ በትምህርት ቤቶች ተማሪዎች አሉ ፣ ሆስፒታል ላይ አልትራሳውንድ ፣ ላብራቶሪ ክፍል ያለመብራት አገልግሎት ስለማይሰጡ እነዚህ ተቋማት ላይ ከፍተኛ ችግር እየደረሰ ነው በመንግስት ስራ ላይ ማለት ነው " ሲሉ የችግሩን መጠን ገልጸዋል።

" እንደመፍትሄ አባይ አሁን ላይ አገልግሎት መስጠት እየጀመረ ስለሆነ ፤ የተወሰነ #ከአባይ በትልቅ ታወር ተቀንሶልን እዚህ ማዕከል ላይ ማከፋፈያ ተሰርቶ ከዚህ ጥገኝነት እንላቀቅ የሚል ጥያቄ ነው ህዝቡ እያነሳ ያለው " ብለዋል።

" የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል " ችግሩን #በዘላቂነት ለመፍታት አዲስ የማከፋፈያ ጣቢያ ለመስራት ቃል ተገብቶ የነበር ቢሆንም እስካሁን ድረስ ግን ተግባራዊ እንዳልተደረገ የቡድን መሪው አሳውቀዋል።

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለካማሽ ዞን አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው የ " ጊምቢ ኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ " አገልግሎት የተቋረጠው ከ2010 ጀምሮ መሆኑ አሳውቋል።

" ካማሽ " ላይ ብቻ ሳይሆን ፤ " ኪንጊ " በተባለ ስፍራ አዲስ ፕሮጀት ሰርተን በፀጥታ ችግር የዘረጋነው የኤሌክትሪክ መስመር በማይታወቅ አካል በመፈታቱ በአካባቢው አገልግሎት እንዳይኖር ተደርጓል ብሏል።

ያለውም ችግር ለመፍታት ከ2 ወር በፊት የጠፋውን የኤሌክትሪክ ሽቦ በመተካት ፕሮጀክቱ ሊጠናቀቅ ሲል 42 ኪ/ሜ በሚሆን ሽቦ ላይ ዛፍ ጥለው ፈተው ወስደውታል። የት እንዳደረሱት አይታወቅም ፤ ክትትል አድርጎ ያስመለሰም አካል የለም ሲል የማከፋፈያ ጣቢያው ገልጿል።

አካባቢው ነዋሪዎችን ስንጠይቃቸው ለሊት የሚፈፀም ድርጊት ስለሆነ ማን እንዳደረገው አናውቅም ይሉናል ፤ ህብረተሰቡ ንብረቱን እስካልጠበቀ እና የአካባቢው የፀጥታ ሁኔታ እስካልተሻሻለ ድረስ " መፍትሄ አይኖርም " ብሏል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሞገስ መኮንን የካማሽ ኤሌክትሪክ መቋረጥ መስሪያ ቤታቸውን እንደማይመለከት መግለፃቸውን ሬድዮ ጣቢያው ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
“ ልጅ ያለው የልጅን ነገር ያውቀዋል። ቶሎ ካልታከመች ክፍተቱ እየጨመረ ነገሮች ሁሉ ይከብዳሉ ” - የ9 ዓመቷ ታዳጊ እናት ልጃቸው ለየልብ ህመም የታመመችባቸው እናት ደጋግ ኢትዮጵያውያን እንዲያግዟቸው ተማጽኑ። ወ/ሮ መባ አላምረው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ “ ሊያ የ3ኛ ክፍል ተማሪ 2ኛ ልጄ ናት። #ልቧ 15 ሚሊ ሜትር #ክፍተት አለው ” ብለዋል። የልብ ስፔሻሊቲ ዶክተርም፣ “ ‘ችግሩ ክፍተት…
#ተመስግናችኃል🙏

ከሳምንታት በፊት ' የልብ ክፍተት ' ችግር ስላለባት እና በአስቸኳይ መታከም ስላለባት የ9 ዓመቷ ብላቴና ሊያ የእገዛ መልዕክት ወደናተ ደርሶ ነበር።

በወቅቱም እናቷ ወ/ሮ መባ አላምረው ለህክምና 700 ሺ ብር መጠየቁን በመግለጽ አቅም ያለው ኢትዮጵያዊ ወገን ልጃቸውን ለመታደግ ትብብር እንዲያደርግላቸው ተማጽነው ነበር።

አሁን ላይ ጉዳዩ ከምን ደረሰ ? ስንል ጠይቀናል።

እናት ወ/ሮ መባ አላምረው ትላንትና ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፥ “ እናንተ ልበ ቀናዎች ባደረጋችሁት ድጋፍ ጭምር የልጄ ሰርጀሪ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል ” ሲል መልካም ዜና አሰምተዋል።

ወ/ሮ መባ በሰጡት ቃል ፦

“ አሁን በጥሩ ጤንነት ላይ ትገኛለች። ከ4 ቀናት ቆይታ በኋላ፣ እሁድ ግንቦት 18 ቀን 2016 ዓ/ም ወደ ቤቷ ገብታለች። ሰርጀሪዋ በጣም ውጤታማ እንደሆነ ዶክተሯ ነግሮኛል።

እናተን እንድገናኝ የረዳኝን ሀይሌ ከፍያለው ከፈረንሳይ እንዲሁም ዶክተር ፈቀደ አግዋር ፈጣሪ እድሜ ያድልልኝ።

#መላው_ኢትዮጵያውያን ፣ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት ማመን በማልችለው ፍቅር እና በፈጣን ምላሽ በአጭር ቀን ውስጥ ልጄ ህክምና እንድታገኝ አግዛችሁኛል። 

ቤተሰቦቼ ፣ ወዳጆቼ በሙሉ እርዳታችሁ ለዚህ ቀን ለማመስገን አድርሶኛል።

አሁንም ፀሎታችሁ አይለየኝ። አመሰግናለሁ ! ” ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia