TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ኤክሳይዝታክስ

ከላይ ባለው ምስል የምትመለከቱት የኤክሳይዝ ታክስ የሚከፋባቸው ዕቃዎች ከኤክሳይዝ ታክስ ነፃ የተደረጉ ናቸው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
excise_amharic_new_8.pdf
21.1 MB
#ኤክሳይዝታክስ

ይህ ከኢፌዴሪ ገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው የPDF ፋይል ስለ ኤክሳይዝ ታክስ የተሟላ መረጃ የሚሰጥ ነው። ውድ ቤተሰቦቻችን ፋይሉን ከፍታችሁ ብታነቡት ስለኤክሳይዝ ታክስ ለሚፈጠርባችሁ ጥያቄዎች መልስ ይሰጣችኃል።

[21.1 MB WiFi ተጠቀሙ]
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#ኢትዮጵያ #ኤክሳይዝታክስ

ኤክሳይዝ ታክስ ላይ ማሻሻይ ተደርጎ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቧል።

ማሻሻያው ቴሌቪዥን እና ቪድዮ ካሜራ ከኤክሳይዝ ታክስ ነፃ እንዲሆኑ፤ ተሽከርካሪዎች ላይም የኤክሳይዝ ታክስ እንዲቀንስ ያደርጋል።

የገንዘብ ሚኒስቴር ለሁለት ዓመታት እና ከዛ በላይ ሲተገበር የቆየው የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ላይ አዳዲስ ማሻሻይ አደርጎ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ማቅረቡ ተሰምቷል።

ማሻሻያ ተድርጎ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት የቀረበው ረቂቅ የኤክሳይዝ ታክስ የያዛቸው አዳዲስ ጉዳዮች ፦

- በተሽከርካሪ ላይ ይጣል የነበረው የኤክሳይዝ ታክስ መጠን እንዲቀንስ ያደርጋል ፤

- ከ3000 ሲሲ ባላይ  ጉለበት ባላቸው ተሽከርካሪዎች ላይ ይጣል የነበረው 240 በመቶ የኤክሳይዝ ታክስ በረቂቅ አዋጁ 120 አካባቢ ዝቅ እንዲል ይላል ፤

- ከ2501 እስከ 3000 ሲሲ 106 በመቶ የኤክሳይዝ ታክስ ፤

- ከ1501 እስከ 2500 ሲሲ 90 በመቶ የኤክሳይዝ ታክስ ፤

- ከ1500 ሲሲ በታች 66 በመቶ የኤክሳይዝ ታክስ ፤ እንዲጣልባቸው ይላል ረቂቅ አዋጁ።

የገንዘብ ሚኒስቴር የታክስ ፖሊሲ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ መሳይ ወልዱ ለብሄራዊ ቴሌቪዥን በሰጡት ቃል ፤ " አሁን በጣም ትኩረት የምናደርገው ወደ ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ነው። ነዳጅን ለማበረታታ አይደለም (የኤክሳይዝ ታክሱ መቀነሱን ማለታቸው ነው) ግን በጣም ከፍ ያለ ከሚሆን ሌሎች ተያያዥ ነገሮች ስላሉት ሲወጣ ይታያል አሁን ያለውን ከፍተኛ ሁለት መቶ አርባ አካባቢ ያለው ወደ መቶ ሃያ አካባቢ ዝቅ እንዲል ፤ በየደረጃው እንደዛ እንዲስተካከል ነው። " ብለዋል።

ዳይሬክተሩ ፤ አዋጁን ለማሻሻል ያስፈለገበት ዋነኛው ምክንያት ከፍተኛ የሆነውን የኤክሳይዝ ታክስ ምጣኔ በመቀነስ #የኤሌክትሪክ_ተሽከርካሪዎች እና የሀገር ውስጥ አምራቾችን ለማበረታታ መሆኑን ገልፀዋል።

አቶ መሳይ ወልዱ ፤ " ታክሱን መቀነስ ብቻ ሳይሆን በተለይ የሀገር ውስጥ ገጣጣሚዎችን በማበረታታት አቅርቦትን ስለሚጨምር ፍላጎትም ይመጣል። አቅርቦትም ስለሚመጣ ዋጋ ተመጣጣኝ እንደሚሆን ምንም ጥርጥር የለውም ፤ ይሄ ወደ ቀረጥና ታክስ ነፃ የሚደረጉ ሩጫ ሁሉ ይቀንሰዋል፤ ይሄ ከፍተኛ መሆኑ ለዛ አንዱ ማበረታቻ ስለሚሰጥ ፤ ዋጋውን ይቀንሰዋል  በተለይ የኦውቶሞቲቭ ኢንድስትሪው የሀገር ውስጡ የራሱን ሚና ይጫወታል በማሳደግ እየተረጋጋ ይሄዳል የሚል ሃስብ ነው ያለው። " ሲሉ ገልፀዋል።

በረቂቅ አዋጁ ላይ የተካተተው ሌላው ፤ 10 በመቶ ኤክሳይዝ ታክስ ይጣልባቸው የነበሩት የቪድዮ ካሜራ እና ቴሌቪዥን ከኤክሳይዝ ታክስ ነፃ እንዲሆኑ ተደርጓል።

አቶ መሳይ " በመጀመሪያው ማሻሻያ እራሱ ቴሌቪዥን ወደ 40 % ነበር የነበረው በጣም ተቀንሶ 10% ነው የተደረገው። የቪድዮ ካሜራም እንደዛው ፤ በጣም አስተያየት ተደርጓል የመጀመሪያው ላይ ግን የገቢ ክፍተት እንዳይፈጠር ቀስ በቀስ መውጣት ስላለብን ከ40 % ወደ 10 % ተደርጓል በተለይ ከስነ ጥበብ ከማሳደግ እና ከመደገፍ አንፃር ታይቶ ፣ ቴሌቪዥንም ህብረተሰቡ መረጃ የሚያገኝበት የመንግስት ፖሊሲ እና ስትራቴጂ የሚሰማበት ስለሆነ እሱ ላይም ቅናሽ ተደርጓል። በሂደት ስናየው አሁንም ተጨማሪ ማሻሻያ ያስፈልጋል የሚል ነው #ቴሌቪዥንና #ቪድዮ_ካሜራ በተለይ በዛ ውስጥ ባይካተቱ የሚል ሀሳብ ነው የቀረበው " ሲሉ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ በ2012 ነበር ለ30 ዓመታት ስትጠቀምበት የነበረውን የኤክሳይዝ ታክስ ያሻሻለችው ፤ አሁን ከ3 ዓመት በኃላ የሚደረገው ማሻሻያ ኢትዮጵያ ከሌሎች ሀገራት ጋር  እኩል እንድትራመድ ለማድረግ የሚደረግ ጥረት መሆኑ ተገልጿል።

መረጃውን ከብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ የተወሰደ ነው።

@tikvahethiopia