TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አዲግራት ዩኒቨርሲቲ🔝

የአዲግራት ዩኒቨርሲቲ #በህክምና ትምህርት መስክ ያስተማራቸውን ተማሪዎቹን በአሁን ሰዓት #እያስመረቀ ይገኛል። በምረቃት ስነ ስርዓቱ ላይ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ዶ/ር #ደብረፅዮን_ገብረሚካኤል ተገኝተዋል።

Via Abraham(TIKVAH-ETH)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ETA

" ማንኛውም የግል ትምህርት ወይም ስልጠና ተቋም #የመምህርነት እና #የህግ ትምህርት ዘርፎችን ማስተማር አይችልም "

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ፤ ባዘጋጀው የከፍተኛ ትምህርትና የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ዘርፍ ፈቃድ አሰጣጥ ረቂቅ መመሪያ ላይ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ወይም የስልጠና ተቋማት በሁሉም መርሃ ግብሮች #የሕግ እና #የመምህርነት ትምህርት ዘርፎችን #አሁንም ማስተማር እንደማይችሉ ተገልጿል።

ከዚህ በፊትም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሁሉም መርሃግብሮች የሕግ እንዲሁም የመምህርነት ትምህርት እንዳይሰጡ የተደረገ ሲሆን አሁንም በአዲሱ መመሪያ የሕግ እና የመምህርነት ትምህርት መስጠት አይችሉም ተብሏል።

ሌሎች በአዲሱ የከፍተኛ ትምህርትና የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ዘርፍ ፈቃድ አሰጣጥ #ረቂቅ መመሪያ ላይ ምን ተካቷል ?

- ማንኛውም ተቋም አዲስ ፕሮግራም ለመከፈት ወይም ነባሩን ፕሮግራም ለማስቀጠል የፍላጎት ዳሰሳ፣ የገበያ ጥናት እና ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ እውደ ጥናት ማካሄድ ይኖርበታል፡፡

- ለማንኛውም የከፍተኛ ትምህርት እና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት የፕሮግራም ፈቃድ የሚሰጠው ባለስልጣኑ (የኢፌዴሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን) የሚያወጣቸውን መስፈርቶች አሟልተው ሲገኙ ብቻ ይሆናል፡፡

- የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚከፍቷቸው ፕሮግራሞች ባለስልጣኑ (የኢፌዴሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን) የሚያወጣቸውን የመመዘኛ መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

- ለማንኛውም ተቋም የሚሰጥ ፈቃድ የሚያገለግለው በባለስልጣኑ (የኢፌዴሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን) ተገምግሞ ለተፈቀደለት ካምፓስና የትምህርት መስክ ብቻ ይሆናል።

- ማንኛውም ተቋም የጤና የትምህርት መስኮችን መስጠት የሚችለው በመደበኛ መርሃ ግብር ብቻ ይሆናል፡፡

- ማንኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም በርቀት ትምህርት መርሃ ግብር ማስተማር የሚችለው ከድንበር ተሻጋሪ ወጪ በመጀመሪያ ዲግሪ ብቻ ይሆናል።

- ማንኛውም የግል ትምህርት ወይም ስልጠና ተቋም #የመምህርነት እና #የህግ ትምህርት ዘርፎችን ማስተማር አይችልም፡፡

- ማንኛውም የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋም የትኛውንም ስልጠና በርቀት መርሃ ግብር ለማሰልጠን የሚቀርብ የፈቃድ ጥያቄ የማይስተናግድ ይሆናል።

- ማንኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም #በህክምና_ዶክትሬት እና #በስፔሻሊቲ ትምህርት ፈቃድ ለማግኘት ተቋሙ #የህክምና_ሆስፒታል ሊኖረው ይገባል።

- በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ በተቋም ደረጃ የጸደቀ ስርዓተ ትምህርት የፈቃድ ጊዜው ሳያበቃ የስርዓተ ትምህርት ወይም የዲግሪ ስያሜ ለውጥ ካለባለስልጣኑ ፈቃድ ወጪ ማድረግ አይችልም።

- በሀገር ደረጃ በትምህርት ፖሊሲ ስርዓተ ትምህርቱ እስካልተቀየረ ድረስ በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ በተቋም ወይም በካምፓስ ደረጃ የጸደቀ ስርዓተ ትምህርት የፈቃድ/ፈቃድ እድሳት ጊዜው እስካላበቃ ድረስ በሌሎች ካምፓሶች መተግበር ወይም መጠቀም ይችላል።

- የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በበየነ መረብ ወይም በርቀት ትምህርት መርሃ-ግብር ፈቃድ ሲጠይቁ በባለስልጣኑ (የኢፌዴሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን) ስርዓተ-ትምህርቱ ቀድሞ መገምገም እና ተገቢ ማስተካከያ ተደርጎ መፅደቅ ይኖርበታል።

- ማንኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም በብሎክ ኮርስ ትምህርት ለመስጠት ያለው አመቺነትና ተገቢነት እንዲሁም የትምህርት ጥራት ላይ የሚኖረውን ተፅህኖ ከግምት በማስገባት ስርዓተ ትምህርቱ ከጸደቀ በኃላ ሊተገብር ይችላል፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ያገኘው ከትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን መሪ አስፈፃሚ ሕይወት አሰፋ ነው።

@tikvahethiopia