TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ማስታወቂያ🔝ዘመኑ ባፈራቸው ቀለል ባሉ የቤት ውስጥ የስፖርት መገልገያች ጤናዎን ይጠብቁ። በ Revoflex Xtreme የስፖርት መገልገያ ከ40 በላይ  ስቴፖችን ይስሩ። እዲሁም በpolice mace power bar በተባለው ተጣጣፊ ዱላ የተለያዩ ቀለል ያሉ ስፖርቶችን ይስሩ። በምስሉ   የሚታዩትን ሁለቱንም Orginal የስፖርት መገልገያዎች በብር  2,800   እንሸጥሎታለን። ያሉበትም ቦታና ሀገር   እናመጣለን እንልካለን። አድራሻ   አ . አበባ ቃሊቲ ካፍደም ህንጻ 2ኛ ፎቅ የሱቅ . ቁ  207። ለመረጃ 0911042543
ደብረ ብርሀን‼️

በደብረብርሃን ከተማ ዘንድሮ ይገነባሉ ተብሎ ለህብረተሰቡ  ቃል የተገባው የመሰረተ ልማት ግንባታ እስካሁን ባለመጀመሩ ነዋሪዎቹ ቅሬታቸውን ገለፁ።

በከተማው ዘንድሮ የተለያዩ የመሠረተ ልማት ግንባታ ለማካሄድ 100 ሚሊዮን ብር መድቦ እየሰራ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል፡፡

በደብረ ብርሃን ከተማ የቀበሌ 04 ነዋሪ የሆኑት አቶ ኢብራሂም ሁሴን እንደተናገሩት በከተማ አስተዳደሩ ይገነባሉ ተብሎ ለህብረተሰቡ ቃል የተገቡ የመሰረተ ልማት ስራ መዘግየት በእለት ከእለት እንቅስቃሴያቸው ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እየፈጠረ ነው።

በከተማው ከብርድ ልብስ ፋብሪካ መገንጠያ አካባቢ ያለው የጠጠር መንገድ በአስፓልት ይገነባል ተብሎ በመንገዱ ዳርቻ የነበሩ ኮንቴነሮችና  የመኖሪያ ቤት አጥር ከፈረሰ ከአንድ ዓመት በላይ ቢሆነውም መንገዱ እስካሁን ባለመሰራቱ ለችግር መዳረጋቸውን ተናግረዋል፡፡

አቶ አዲስ ጥላዮ የተባሉ የከተማው ነዋሪ በበኩላቸው በሸቀጣ ሸቀጥ ንግድ የሚተዳደሩበት ኮንቴነር ሱቅ ለመንገድ ግንባታ ማስፋፊያ ተብሎ ከአንድ ዓመት በፊት ቢፈርሰም  ግንባታው አለመጀመሩ እንዳሳዘናቸው ተናግረዋል፡፡

በከተማ አስተዳደሩ የሚሰሩ የመንገድም ሆነ የጎርፍ መፋሰሶሻ ቦዮች  ግንባታ ክረምቱ ሲገባ የሚሰሩ በመሆናቸው የጥራት ችግር እንደሚገጥማቸው የከተማዋ ነዋሪ ወይዘሮ መሰረት መንግስቴ አመልክተዋል።

የውስጥ ለውስጥ የአስፓልትና የጌጠኛ ድንጋይ መንገዶች  አገልግሎት ሳይሰጡ መፍረሳቸውን የጠቆሙት አስተያየት ሰጪዋ “በተያዘው አመት ለመገንባት ቃል የተገቡ የመሰረተ ልማት ስራዎች ባለመጀመራቸው ቅሬታ ተሰምቶኛል” ብለዋል፡፡

የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማት ቤቶች ኮንስትራክሽን አገልግሎት ጽህፈት ቤት የቤቶችና መሰረተ ልማት ቡድን መሪ አቶ ዳውድ ማሩ በከተማው በበጀት ዓመቱ ተለይተው ለሚከናወኑ 31 የልማት ፕሮጀክቶች 100 ሚሊዮን ብር በጀት መመደቡን ተናግረዋል፡፡

ከብርድ ልብስ ፋብሪካ እስከ መገንጠያ ያለው 710 ሜትር የአስፓልት መንገድን ጨምሮ 3 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር የጠጠርና የጌጠኛ ድንጋይ መንገድ ንጣፍ ስራዎች እንደሚከናወኑ ቡድን መሪው አስረድተዋል፡፡

የፕሮጀክቶችን የግንባታ ስራ ለማስጀመር የዲዛይንና መሰል ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ዳውድ የመሰረተ ልማት ግንባታዎችን የህዝቡን ቅሬታ በሚፈታ መንገድ ለማከናወን ጥረት እንደሚደረግ አስታውቀዋል፡፡

የከተማዋ ነዋሪዎች በአካባቢያቸው ለሚካሄደው የመሰረተ ልማት ግንባታ  የጥራት ደረጃውን ጠብቆ እንዲከናወን የበኩላቸውን ድጋፍና ክትትል እንዲያደርጉ ቡድን መሪው አሳስበዋል።

በደብረ ብርሃን ከተማ ቀደም ሲል ከ179 ኪሎ ሜትር የውስጥ ለውስጥ የአስፓልት፣ የጠጠርና የድንጋይ ንጣፍ መንገድ በመስራት ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ማደረግ መቻሉ ታውቋል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዶክተር ደብረፅዮን‼️

የሀበሻ ወግ መፅሄት በህዳር እትሙ ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ምእራብ ትግራይን ሲጎበኙ "ከአማራዎች ይልቅ #ሱዳኖች ይሻሉናል" ብለው ተናገሩ ብሎ ይዞ የወጣውን ዘገባ #እውነትነት ለማጣራት የትግራይ ክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮ ሀላፊ #ሊያ_ካሳ ጋር የAPው ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ስልክ ደውሎ ነበር። እሷ እንዳለችው ዶ/ር ደብረፅዮን በፍፁም እንደዛ እንዳላሉ እና ንግግሩ ከየት እንደተወሰደ እንደማታውቅ ገልፃለች። አክላም: "የትግራይ ህዝብ ከአማራው፣ የአማራ ህዝብ ደግሞ ከትግራዩ ምን ያህል #የማይነጣጠል ህዝብ እንደሆነ ህዝቡ እራሱ በደንብ ያውቀዋል። ይህ ሆን ተብሎ #ለመነጣጠል የሚደረግ ጥረት እና የሚፈበረክ #ወሬ እንጂ የተባለ ነገር አይደለም። ምእራብ ትግራይ ዶ/ር ደብረፅዮን የሄደበት ግዜ ይታወቃል እናም የተናገረውም ይታወቃል። እንደዚህ አይነት ነገር ጭራሽ አላነሳም።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጉለሌ ፖስት🔝ዛሬ ህዳር 22 በሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ ቶኩማ አዳራሽ #ጉለሌ_ፖስት መፅሄት በርካታ ሰዎች በተገኙበት ተመርቋል። በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ አክቲቪስ ጃዋር መሀመድ ተገኝቶ ነበር።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሀድያ ዞን ምክር ቤት የሀድያ ብሔረሰብ የራሱን #ክልል እንዲመሰርት የቀረበለትን የውሳኔ ሀሳብ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።

©ኤርመኮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የብሔራዊ የፀጥታ ምክር ቤት አለመረጋጋት በሰፈነበት የቤኒሻንጉል ጉምዝና የኦሮሚያ አዋሳኝ ድንበር #የፌደራል_ሀይሎች እንዲሰማሩ ወሰነ። ውሳኔው በሁለቱ ክልሎች ግብዣ መሆኑ ተገልጿል።

ምንጭ፦ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለአምስተኛ ጊዜ ያሰለጠናቸውን 76 የህምክና ዶክተሮች ዛሬ አስመርቋል፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የገዳ ስርዓት በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የተመዘገበበት 2ኛ ዓመት ዛሬ በአዳማ ከተማ በፓናል ውይይት አክብሯል፡፡

©የኦሮሚያ ኮሚኒኬሽን ቢሮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በሳውላ ከተማ #ረብሻ ሁለት ሰዎች ተገደሉ አምስት ቆሰሉ‼️
.
.
በትናንትናው ዕለት በጋሞ ጎፋ ዞን #ሳውላ_ከተማ በተካሔደ ስብሰባ ላይ በተቀሰቀሰ ኹከት ሁለት ሰዎች #መገደላቸውን እና አምስት መቁሰላቸውን ፖሊስ አስታወቀ።

የሳውላ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር #ብስራት_አንበርብር በከተማዋ ሊካሔደ በታቀደው ስብሰባ ላይ የተፈጠረውን ረብሻ ለመቆጣጠር የጸጥታ ኃይሎች በተኮሱት ጥይት ሁለት ሰዎች መገደላቸውን እና አምስት ሰዎች
መቁሰላቸውን ለ«DW» አረጋግጠዋል።

በስብሰው የተካፈሉ አንድ የአይን እማኝ በዞኑ ጉዳይ ላይ ለመመካከር የተጠራውን ስብሰባ "የሚቃወሙ ብዙ ወጣቶች ወጥተው ነበር። መጨረሻ ላይ እኛን ሊወክሉ የማይችሉ ሰዎች ወደ ስብሰባው መምጣት የለባቸውም በሚል ይመስለኛል" ሲሉ የኹከቱን ምንጭ ተናግረዋል። ስብሰባው እንደታቀደው ሳይካሔድ መቋረጡን የተናገሩት የአይን እማኙ የድንጋይ መወራወር ድርጊት መመልከታቸውም ገልጸዋል።

ኮማንደር ብስራት አንበርብር በበኩላቸው "እንግዶችም ወደ አዳራሹ ሊመጡ አልቻሉም። [ወጣቶቹ] ዙሪያውን ከበቡ። እኛ ስንከላከል በድንጋይ መስታወቶችን መስኮቶችን እየመቱ በአጥር ላይ ዘለው ለመግባት ጥረት ሲደረግ ነው የጸጥታው ኃይል በተኩስ አካባቢውን በተኩስ ለማስለቀቅ ጥረት ያደረገው። ሁለት ሰው እዚያ አካባቢ ሞቷል። አምስት የሚሆኑ ሰዎች ቆስለዋል" ሲሉ አስረድተዋል።

ፖሊስ ግጭቱን በማነሳሳት የተጠረጠሩ ያላቸውን 78 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ማዋሉን ኮማንደሩ ጨምረው ተናግረዋል። በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል የሚገኘው የሳውላ አካባቢ ባለፈው ጥቅምት ወር በዞን ደረጃ እንዲዋቀር ከተነሳ ጥያቄ ጋር ተያይዞ በተነሳ ግጭት በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን DW ዘግቧል።

የክልሉ ምክር ቤት በቅርቡ ባካሔደው መደበኛ ጉባኤ አካባቢው ቀደም ሲል ከነበረበት የጋሞ ጎፋ ዞን በመውጣት ራሱን ችሎ በዞን ደረጃ እንዲዋቀር ወስኗል።

ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ(ሸዋንግዛው-ሀዋሳ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia