TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የዳንሻ ከተማ ወቅታዊ ሁኔታ‼️

ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በዳንሻ እየተስተዋለ ባለው #ግጭት የሁለት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የትግራይ ክልል መንግሥት አስታውቋል፡፡

ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በዳንሻ እየተስተዋለ ባለው ግጭት የሁለት ሰዎች ሕይወት ማለፉ የትግራይ ክልል መንግስት ዐስታውቋል፡፡ የከተማዋ ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች በተሽከርካሪዎች ላይ እየወሰዱት ያለው #እርምጃ የተቃወሙ ወጣቶች ከፖሊስ ጋር ወደ ግጭት ገብተው እንደሰነበቱ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ ግጭቱ በመስጋት የዳንሻ ነዋሪዎች ከተማዋ ለቀው በአቅራብያቸው ወደሚገኙ አካባቢዎች #መሰደዳቸው ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡

በምዕራብ ትግራይ ዞን ፀገዴ ወረዳ የምትገኘው ዳንሻ ከተማ ካሳለፍተው ሳምንት ጀምሮ ግጭት ስታስተናግድ ሰንብታለች፡፡ የአካባቢው ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች «ሕገ ወጥ» ያልዋቸው ሞተር ብስክሌቶችና ባለሦስት እግር ተሽከርካሪዎች መያዝ መጀመራቸው ተከትሎ በተከሰተው አለመግባባት ወደ ሁከት ገብታ የሰነበተችው ዳንሻ ከረቡዕ የካቲት 20 ጀምሮ በከተማዋ በተስተዋለ ግጭት የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡ ከሞቱት በተጨማሪ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ዜጎች ጉዳት ደርሶባቸው በተለያዩ ሆስፒታሎች እየታከሙ መሆኑ ነዋሪዎች ነግረውናል፡፡ በፖሊስና እርምጃው በተቃወሙ ወጣቶች መካከል የተከሰተው ግጭቱ እየተባባሰ መቀጠሉ ተከትሎ የከተማዋ ነዋሪዎች ዳንሻን እየለቀቁ መሆኑ ሰምተናል፡፡ በከተማዋ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት የሚተዳደር የነበረው በድህንነት ስጋት ምክንያት ከተማዋ ለቆ አሁን ሑመራ እንዳለ የሚናገረው ፀሐዬ የተባለ አስተያየት ሰጪ በግል ንብረቱ ጨምሮ በብዙዎች ሀብት ላይ ውድመት መድረሱ ለጀርመን ራድዮ ተናግሯል፡፡

እንደ ጀርመን ራድዮ ምንጮች መረጃ ግጭቱ ከተከሰተበት ቀን ጀምሮ የከተማዋ የመንግስት መስሪያቤቶች፣ የግል ድርጅቶች፣ የፋይናንስ ተቋማትና ሌሎች አገልግሎት አቋርጠው ሰንብተዋል፡፡ በከተማዋ ቅኝት ማድረጉ የሚናገረው ተመስገን ካሳሁን የተባለ የአይን እማኝ፡ ዳንሻ ዛሬ በአንፃራዊነት #ተረጋግታ ውላለች ብሏል፡፡ የተወሰነ የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ መመልከቱም ተናግሯል፡፡

መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ግጭቱ ለማብረድ ባለፈው ሳምንት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት ወደ ከተማዋ ገብተው የነበሩ ሲሆን ከጥቂት ቆይታ በኋላ የትግራይ ልዩ ሐይል ፖሊሶች በቦታው #ተተክተዋል፡፡

የዳንሻን ጉዳይ አስመልክተን የተጠየቁት የትግራይ ክልል ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሐላፊዋ ወይዘሮ #ሊያ_ካሳ የክልሉ መንግስት ለችግሩ ትኩረት መስጠቱ ተናግረዋል፡፡ ግጭት የፈጠሩ አካላትም "ሕግ የማስከበር ተግባር የማይዋጥላቸው ጥቂት ግለሰቦች ናቸው" ብለዋል፡፡ በከተማዋ ትራፋክ ተቆጣጣሪዎች የተወሰድ እርምጃ ክልል የለየ እንዳልሆነና ሕግ የማስከበር ተግባር ብቻ መሆኑ ሐላፊዋ ለጀርመን ራድዮ ገልፀዋል፡፡

ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia