TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"አንዱ #ብሄር ሌላውን መጣብኝ ካለ፣ #ውጣልኝ! #ሂድልኝ! ካለ፣ ይሄኛው የኢትዮጵያ ክፍል #የኔ እንጂ ያንተ አይደለም ካለ፣ ታዲያ ቅኝ ገዥዎችስ ከዚህ የተለየ ምን ሊያደርጉ ይችላሉ!?"

ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#የኔ_ትውልድ የሙዚቃ ኮንሰርት የትኬት አሸናፊዎች፦ አሞሌን ለስጦታው እናመሰግናለን!

•አማኑኤል
•ያሬድ
•ቴዎድሮሥ
•ሳሙኤል
•ቅዱስ

ስልክ ቁጥሮቻችሁን በMeda በኩል ላኩልኝ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ስጦታ!

@medachat የሮፍናንን "የኔ ትውልድ" የሙዚቃ ኮንሰርት እንድታደሙ ለ20 አሸናፊ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ነፃ ትኬትና ሌሎች ሽልማቶች አዘጋጅቶልናል!

MedaChat App ስልኮት ላይ ተጭኗል??
1.ካልተጫነ በዚህ ያገኛሉ www.bit.ly/medachatapp

2. በመቀጠል በሜዳ ቻት APP ውስጥ discovery የሚለው ውስጥ በመግባት meda hunt የሚለውን ይክፈቱ

3.ከዛም ከላይ በምስሉ ላይ ያለውን QR code ያንብቡ . . ይሸለሙ

ሰላም፣ ፍቅር፣ አንድነት!
#የኔ_ትውልድ #አሞሌ #ሜዳ_ቻት
#update የሮፍናን #የኔ_ትውልድ ኮንሰርት ባሳለፍነው ቅዳሜ በተፈጠረው መጉላላት ትኬት ቆርጠው መሳትፍ ላልቻሉ ታዳሚያን የፊታችን ቅዳሜ በድጋሚ ሊደረግ መሆኑ ተሰምቷል።

Via ዳሰሳ አዲስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሮፍናን "የኔ ትውልድ ኮንሰርት"🔝

#ቃና_ስቱዲዮ👉ከወሎ ሰፈር ወደ ጎተራ መንገድ ከድሬዳዋ ህንፃ ፊት ለፊት ይገኛል። #የኔ_ትውልድ #MyGeneration

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የተማሩ ልጆቿን ያላከበረች ሐገር የትም አትደርስም! #የኔ_ትውልድ እውቀትና ሙያውን ያስከብራል።

(ዶ/ር ኤልያስ ገብሩ አዕምሮ)

ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት በጠቅላላው 10,000 ገደማ ሐኪሞች የሚበልጥ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያውያን ሐኪሞች በቺካጎ ከተማ ብቻ ይገኛሉ። እደግመዋለሁኝ! በአንዷ የአሜሪካ ስቴት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ዶክተሮች ቁጥር ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት ጠቅላላ ዶክተሮች ቁጥር ይበልጣል። >የህክምናው ጉድ ቢብስም በሁሉም የትምህርት ዘርፍ ጥሩ ደረጃ ላይ የደረሱ ኢትዮጵያውያን ይህቺን ምስኪን ሐገር ትተው ውጭ ይገኛሉ።

> አይለፍልሽ ያላት ሐገር ውስጥ ከተማረና ከሰራ ይልቅ ያወራና የደለለ ይከበርባታል። የእውነተኛ እድገቷ ሞተሮች የሆኑ ሊቃነ ጭንቅላቶቿን ለባዕድ ትገብራለች።

>አሁንም ጆሮ ያለው ይስማ መከበርና መጠቀም ያለበት የህዝብ አገልጋይ ከተዋረደና ጥቅሙን ከተከለከለ ጉዳቱ ከባድ ነው።

... የእውቀት ባለቤቶችና ሙያተኞች ተንቀው አፈ ቀላጤዎችና ገንዘብ አሳዳጆች የሚከበሩባት ሐገር አያልፍላትም። የሌሎች እውቀትና ባለሙያን የሚያከበሩ ሐገራት ጭራ እንደሆነችም ትቀራለች። ሐገርን የሚለውጥ፣ የሚያሳድግና ትብታቧን የሚፈታ የተማረ፣ ያነበበና የተመራመረ ትውልዷ እንጂ ቁጭ ብሎ የሚደሰኩረው አይደለም።

... የዚህች ሐገር አሰራርና አመለካከት ግን በተለይ በቅርብ አስርተ አመታት ውስጥ የተማረን ሰው አውርዶ አውርዶ መሬት ላይ አንጥፎታል። ስንት ሐገርና ህዝብን ሊጠቅሙ የሚችሉ አዕምሮዎች ተሰደዋል... ተገድለዋል... ተስፋ ቆርጠው በየስርቻው ቀርተዋል።
..
... ዛሬ ይህን ፅሑፍ የፃፍኩት ሰሞኑን እየተነሳ ላለው የኢትዮጵያ ሐኪሞች ጥያቄ በርካታ የማጣጣልና የወቀሳ ኮሜንቶችን ስላየሁኝ ነው። አዎ ሐኪሙ ለዘመናት ተገፍቷል፤ ይሄ የኔ ትውልድ ግን ይህንን የግፍ ቀንበር የሚሸከም አይደለም። ምክንያቱም ወጠጤ ካድሬ በቬ 8 እየተንፈላሰሰ 10 ዓመት ሙሉ ህፃናትን ሲያክም የቆየ የህፃናት ሐኪም ታክሲ መጋፋት ስለሌበት። ሌሊቱን ሙሉ ሳይተኛ የወገኑን ግሉኮስና ኦክስጅን ሲከታተል ያደረ እጩ ሐኪም ጥዋት ሲወጣ የቁርስ መብያ ገንዘብ ማጣት ስለሌለበት። ለአመታት ከታካሚዎቹ ጋር ሲጨነቅ የሚውልና የሚያድር ሬዝደንት ሐኪም የደከመው ጎኑን የሚያሳርፍበት ቤት ስለሚሻ። ከኢትዮጵያ በGDP የሚያንሱ ድሃ የአፍሪካ ሐገራት እንኳን የሐኪምን ክብር አውቀው ከኢትዮጵያ ሐኪሞች ደሞዝ በ5 እና 10 እጥፍ የሚበልጥ ደሞዝ መክፈላቸው የሐገራችን ሐኪሞች ክብር ማጣታቸውን ስለሚያመለክት።
... እናም ለዘመናት የጤናውና የትምህርቱን ስልጣን ይዛችሁ የገደላችሁን ካድሬዎች ቦታ ልቀቁ። ለአዲሱ ትውልድ አስተላልፉ!
#የኔ_ትውልድ_ይችላል!
#ለእውቀት_ባለቤት_ቦታ_ልቀቁ
#ለተማረና_ለሚለፋ_ክብር_ይሰጥ

@tsegabwolde @tikvahethiopia