TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጅማ⬆️ጠ/ሚ ዶክተር #አብይ_አህመድ የተገኙበት 9ኛው የኦህዴድ ድርጅታዊ ጉባኤ የመክፈቻ ስነስርዓት #በጅማ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

ፎቶ፦etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና📌የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት/ኦህዴድ/ ስያሜውን ወደ ኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ቀየረ። ፓርቲው ስያሜውን የቀየረው #በጅማ እያካሄደ ባለው 9ኛው ድርጅታዊ ጉባኤ ነው።

14 ነባር አመራሮችንም በክብር አሰናብቷል፦

አቶ አባዱላ ገመዳ
አቶ ጌታቸው በዳኔ
አቶ ኩማ ደመቅሳ
አቶ ግርማ ብሩ
አቶ ድሪባ ኩማ
አቶ እሸቱ ደሴ
አቶ ተፈሪ ጥያሩ
አቶ ሽፈራው ጃርሶ
አቶ ደግፌ ቡላ
አቶ አበራ ሀይሉ
አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ
አቶ ኢተፋ ቶላ
አቶ ዳኛቸው ሽፈራው
አምባሳደር ጊፍቲ አባሲያ

©አቶ አዲሱ አረጋ, fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጥንቃቄ ይደረግ‼️

ከወለጋ #እንደተፈናቀሉ_በማስመሰል #በጅማ_ከተማ ህብረተሰቡን በማጭበርበር እርዳታ ሲያሰባስቡ እጅ ከፍንጅ የተያዙ ሁለት ግለሰቦች በእስራትና በገንዘብ መቀጣታቸውን ፖሊስ አስታወቀ።

የጅማ ከተማ ፖሊስ መምሪያ እንደገለጸው ግለሰቦቹ ከወለጋ እንደተፈናቀሉና ቤታቸው ንብረታቸው እንደተወሰደ በመናገር በሀሰት ከህብረተሰቡ ለአምስት ቀን #እርዳታ ሲያሰባስቡ ቆይተዋል።

ፖሊስ ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ በግለሰቦቹ ላይ ባደረገው ክትትል የካቲት 22/ 2011ዓ.ም. በጅማ ቢሺሼ የገበያ ማዕከል እንደያዛቸው የመምሪያው የኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ ኢንስፔክተር ገዛኸኝ አውጋቸው ተናግረዋል።

“በወንጀል ድርጊቱ ተሳትፈዋል የተባሉት ሁለቱ ግለሰቦች ነዋሪነታቸው አዲስ አበባ መሆኑ በተደረገባቸው ምርመራ ተረጋግጧል” ብለዋል።

በሃሰት ካሰባሰቡት ገንዘብ ውስጥ አንደኛው መኪናውን እንድታሰራለት 5 ሺህ 300 ብር ለባለቤቱ መላኩንና ሌላኛው ደግሞ 3 ሺ 23 ብር ለዘመዶቹ መላኩን በሰጡት የእምነት ቃል አረጋግጠዋል።

ከዚህ ገንዘብ በተጨማሪም ፖሊስ በግለሰቦቹ እጅ አራት ሺህ ብር ጥሬ ገንዘብ በኢግዚቢትነት መያዙንም አመልክተዋል።

በወንጀል ተከሰው ጉዳያቸውን ሲከታተል የቆየው የጅማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሰሞኑን በዋለው ችሎች እያንዳንዳቸው በአንድ ዓመት ከስምንት ወራት ጽኑ እስራትና በ500 ብር እንዲቀጡ የወሰነባቸው መሆኑን ኢንስፔክተሩ ገልጸዋል።

ግለሰቦች #ክስቸውን_እንዲከላከሉ እደሉ ቢሰጣቸውም #ባለመቻላቸው የቅጣት ውሳኔው ጸንቶባቸዋል፡፡

ምንጭ፦ ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሬዚደንት #JU

“ የ3 ወራት ያህል ደመወዝ አልተከፈለንም ” - የጅማ ዩኒቨርሲቲ ሬዚደንት ሀኪሞች

“ ይህ ጉዳይ ጤና ሚኒስቴርን ነው የሚመለከተው ” - ዩኒቨርሲቲው

በ2016 ዓ/ም በጤና ሚኒስቴር #በጅማ_ዩኒቨርሲቲ  ተመድበው በሆስፒታሉ ሥራና ስፔሳላይዜሽን ስልጠና የሚወስዱ 70 የአንደኛ ዓመት ሬዚደንት ሀኪሞች የ3 ወራት ደመወዝ እንዳልተከፈላቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ቅሬታ አቅርበዋል። 

“ የ3 ወራት ደመወዝ አልተከፈለንም። ከፍተኛ ችግርና ስቃይ ውስጥ ወድቀናል ” ያሉት ቅሬታ አቅርቤዎቹ፣ ጉዳዩ የሚመለከተውን አካል ቢያነጋግሩም ‘ መፍትሄ እየፈለግን ነው ፤ ዩኒቨርሲቲው በጀት የለውም ’ እንደተባሉ ገልጸዋል።

መጀመሪያ 100 ሬዚደንት ሀኪሞች እንደነበሩ ፤ በኋላ ግን ለቀው ለመሄድ በመገደዳቸው አሁን ላይ የቀሩት 70 ብቻ መሆናቸውን አስረድተዋል።

ቤተሰብ ጭምር ይዘው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሄዱ ሬዚደንት ሀኪሞችም እንዳሉ ፤ የሚተዳደሩት ከደመወዝ በሚያገኙት ገቢ እንደሆነ ገልጸዋል።

“ በጣም ከፍተኛ ችግር ውስጥ ነው ያለነው። ደመወዙ በዚህ ሳምንት ሊገባልን ይገባል ” ሲሉ አሳስበዋል።

ለተነሳው ቅሬታ ምላሽ እንዲሰጡ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበላቸው የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጀማል አባፊጣ ፣ “ ጤና ሚኒስቴርን ነው የሚመለከተው። እኛን አይመለከትም ” የሚል አጭር ምላሽ ሰጥተዋል።

በጉዳዩ ላይ ምላሽ ለመጠየቅ ወደ #ጤና_ሚኒስቴር የተደረገው ሙከራ ኃላፊዎቹ ተደጋጋሚ የስልክ ጥሪ ለማንሳት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ለጊዜው ቃላቸውን ማካተት አልተቻለም።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia