TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሜቴክ‼️

ሰሞኑን ከታሰሩት የሜቴክ እና ደኅንነት አመራሮች እና አባላት መካከል የተወሰኑት ሥም ዝርዝር ይፋ ወጥቷል፡፡ ከእነዚህም መካከል፦

🔹የሰሜን ጎንደር ደኅንነት ሃላፊ አቶ #አሸናፊ_ተስፋሁን

🔹እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የአማራ ክልል ደኅንነት ሃላፊ የነበረው አቶ #ነጋ_ኑሩ

🔹በሱማሌ ክልል የደኅንነት ሥራዎችን ሲያስተባብር የነበረው አቶ #ቢኒያም_ማሙሸት

🔹በደኅንነቱ ሥር የግንቦት 7 ክትትል ዴስክ ሃላፊ የነበረው አቶ #ሸዊት_በላይ

🔹የሐረሬ ክልል ደኅንነት ሃላፊ የነበረው አቶ #ተከተል (የአባት ሥም አልተጠቀሰም)፣

🔹የክትትል መምሪያ ሃላፊ እና የአፋኝ ቡድን ቁልፍ አባል የነበረው አቶ #አጽብሃ_ግደይ እና

🔹የጸረ-ስለላ መምሪያ ሃላፊ የነበረው አቶ #ሳሙዔል (የአባት ሥም አልተጠቀሰም) ይገኙበታል፡፡

በተያያዘ ዜና...

በሙስና ተከሰው የታሰሩት የሜቴክ እና ደኅንነትና መረጃ አመራሮች ዛሬ ከሰዓት በኋላ ፍርድ ቤት #ቀርበዋል። ተጠርጣሪዎቹ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ ልደታ ምድብ 10ኛ ወንጀል ችሎት ነው የቀረቡት፡፡ ፍርድ ቤት ከቀረቡት ውስጥ 36ቱ በሰብዓዊ መብት ጥሰት የተጠረጠሩ ሲሆኑ በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩት ደሞ 27 ናቸው፡፡ አቃቤ ሕግ በሁለቱም ምድብ ተጠርጣሪዎች ላይ የጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው ጠይቋል፡፡

ምንጭ፦ ዋዜማ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia