አቶ ለማ መገርሳ!
በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች ለሚስተዋሉ የፀጥታ ችግሮች ሁነኛ መፍትሄ ፍለጋ በጥሞናና በሰከነ መንፈስ #መወያየትን እንደሚጠይቅ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ #ለማ_መገርሳ ተናገሩ፡፡
የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፉበት የሠላም ኮንፈረንስ በሻሸመኔ ከተማ ተካሂዷል፤ ተሳታፊዎቹ ከምስራቅ እና ምዕራብ አርሲ ፤ ባሌ ፤ ቦረና ፤ ምስራቅ እና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች የተውጣጡ ናቸው። በውይይቱ ላይ የኦሮሞን ህዝብ የትግል ታሪክ እና አሁን ያለውን ሁኔታ የሚያሳይ ፅሁፍ ቀርቧል።
ፅሁፉን ያቀረቡት የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ / ኦዴፓ / የገጠር ፖለቲካ አደረጃጀት ዘረፍ ሃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ ናቸው፤ አቶ አዲሱ ባቀረቡት ፅሁፍ በቄለም ወለጋ ፤ ምዕራብ ወለጋ ፤ ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ እና ጉጂ ዞኖች የፀጥታ ችግሮች እየታዩ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።
የእነዚህን ችግሮች ጉዳት አስቀድሞ በመረዳት ከወዲሁ መፍትሄ መስጠት ይገባልም ብለዋል። የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሣ በበኩላቸው በደቡብ እና ምዕራብ ኦሮሚያ የታጣቁ ሃይሎች ችግር እየፈጠሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ከእነዚህ የታጠቁ ሃይሎች ጋር ውይይት ቢደረግም በሰከነ መንፈስ መደማመጥ አለመቻሉን አክለዋል። የሚሻለው ግን በሰከነ መንፈስ መነጋገር እንደሆነ ርዕሰ መስተዳድሩ ግልጽ አድርገዋል።
የሚታዩ የፀጥታ ችግሮች የልማት ስራዎችን ለማከናወን እንቅፋት እንደሆኑም አቶ ለማ ተናግረዋል።
ህዝቡም ይህንኑ በመረዳት በተሳሳተ መንገድ ላይ ያሉ ወገኖችን ወደ ትክክለኛው መስመር ሊመልሳቸው ይገባል ብለዋል።
ከውጪ የገቡ ሃይሎች በሠላማዊ መንገድ እንዲታገሉ ግፊት ሊያደርግ እንደሚገባም ርዕሰ መስተዳድሩ አሳስበዋል።
ምንጭ፦ ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia

ሰበር ዜና‼️
ሻለቃ አትሌት ሃይሌ ገብረስላሴ ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንትነቱ በፍቃዱ #ለቀቀ።
አትሌት ሃይሌ መልቀቂያ ደብዳቤውን ለጠቅላላ ጉባኤ አባላት ማዘጋጀቱን ዛሬ ቦሌ በሚገኘው የራሱ ቢሮ ለስፖርት ጋዜጠኞ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።
በደብዳቤው እንዳመለከተውም እስከ ቀጣዩ የምርጫ ወቅት ድረስ ኮሎኔል አትሌት #ደራርቱ_ቱሉ የፕሬዚዳንትነቱን ቦታ ተክታ እንድትሰራ መወከሉንም ገልጿል።
ምንጭ፦ fbc

አዴፓ እና አዴኃን ተዋሀዱ‼️
የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ(አዴፓ) እና የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ንቅናቄ(አዴኃን) #ውህደት መፍጠራቸውን በሰጡት መግለጫ አስታወቁ፡፡
አዴፓ በመግለጫው እንዳስታወቀው የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ንቅናቄ(አዴኃን) ወደ በረሀ ወርዶ የታገለላቸው ሀሳቦች አዴፓም አቋም ይዞ የሚታገለው ሀሳብ ነው፤ ስለሆነም ሁለቱ ድርጅቶች መዋሃዳቸው ለአንድ ዓላማ መቆማቸውን ያሳያል፡፡
ከዛሬ ጀምሮም የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ(አዴፓ) እና የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ንቅናቄ(አዴኃን) ውህደት ፈጥረናል ብለዋል፡፡
አዴኃን በቅርቡ የተፈጠረውን ለውጥ ተከትሎ በሰላም ለመታገል ከኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ የገባ ድርጅት ነው፡፡
ምንጭ፦ አብመድ

"የሰኔ 16ቱ የአዲስ አበባው የቦምብ ጥቃት የብሄራዊ መረጃ ደህንነት አገልግሎት የቀድሞ #ሀላፊ የተመራ ነው"
የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መግለጫ በመስጠት ላይ ይገኛል።
በመግለጫው እስካሁን በሰብዓዊ መብት ጥሰት ወንጀል 36 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው እና ሰባት ድብቅ እስር ቤቶች በአዲስ አበባ ተገኝተዋል።
በሽብር ወንጀል የተጠረጠሩ የተጠረጠሩበት ወንጀል ዜጎችን በድብቅ ማሰር፣ መደብደብ፣ አስገድዶ መድፈር፣ ብልት ላይ ውሃ ማንጠልጠል
የመሰሉ ወንጀሎች ይገኙበታል።
ምንጭ፦ ፋና

የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ‼️
በቁጥጥር ስር ስለ ዋሉ ግለሰቦች የፌደራል አቃቤ ህግ በመግለጫው ካነሳቸው #አንኳር ነጥቦች መካከል፦
• ምርመራው ከ5 ወር በላይ ፈጅቷል። የዚህ ምክንያቱም በቁጥጥር ስር የዋሉ ግለሰቦችን አስረን ከማጣራት አጣርተን ለማሰር ስለሞከርን ነው። ማንንም ተጠርጣሪ ሳንይዝ ነው ያጣራንው።
• በቁጥጥር ስር ከዋሉ ገለሰቦች መሀል የተሰጣቸውን ሃላፊነት ወደ ጎን በመተው ያለአግባብ ሀብት ያከማቹ፣ ሀብት ያሸሹ፣ በሰብአዊ መብት ጥሰቶች ላይ የተሳተፉ፣ በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች ላይ የተከሰቱ ብጥብጦች ያስተባበሩ ይገኙበታል።
• በብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት አባላት መካከል በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በስውር እስር ቤት ግለሰቦችን በማሰር እና በማሰቃየት ተጠርጥረው የተያዙ አሉ። በአዲስ አበባ ብቻ ከሰባት በላይ እስር ቤቶች ተገኝተዋል።
• በሰብአዊ መብት ጥሰት ጠጠርጥረው ከተያዙ ግለሰቦች መሀል ግለሰቦችን ከፖለቲካ ፓርቲ አባልነት እራሳቸውን እንዲያገሉ ማድረግ እና ማሰቃየት፣ በአንቡላንስ እያፈኑ ሰዎችን መሰወር፣ ህገወጥ መሳሪያዎችን የራሴ ነው ብሎ እንዲፈርሙ ማድረግ፣ የብልት ቆዳዎችን በፒንሳ መሳብ፣ ጫካ ማሳደር፣ ከአውሬ ጋር ማሰር፣ አፍንጫ ውስጥ እስክርቢቶ መክተት፣ ግብረሰዶማዊ ጥቃት መፈፀም፣ ሴቶችን መድፈር የመሳሰሉ አረመኔያዊ ድርጊቶችን ፈፅመዋል
• የሰኔ 16ቱ የቦንብ ጥቃት በዋናነት የተቀነባበረው የብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት አባል በሆኑ ግለሰብ ነው።ኬንያ ከምትገኝ ገነት ቶሎሺ ከተባለች ግለሰብ ጋር በመሆን ነበር፡፡
• ሜቴክን በተመለከተ፤ የውጪ ሀገር ግዥዎችን ያለጨረታ መስጠት፣ ግዥ አፈፃፀሙ ከኮርፖሬሽኑ የበላይ አመራሮች ጋር የጥቅም ትስስር ያላቸው ሰዎች የድለላ ስራ ሰርተው የሚከፈላቸውና እነዚህ የውጪ ኩባንያዎችን የሚያመጡት ደላሎች በስጋ ዝምድና ለአመራሩ ቅርብ የሆኑ ናቸው። እነዚህ በድለላ ያሉ ሰዎች በሀገር ውስጥ ካካበቱት ሃብት በላይ ወደ ዉጪ ሃብት አሽሸዋል። ከመደበኛው ዋጋ እስከ 400% ተጨማሪ ዋጋ እየተጨመሪ ግዢ ይፈፀም ነበር።
• የሀገር ውስጥ ግዢም በግልፅ ጨረታ መፈፀም ሲገባው እስካሁን በዚህ መልኩ የተፈፀመ የለም። ከኮርፓሬሽኑ አመራሮች ጋር የዝምድናና የጥቅም ትስስር ካላቸው ሰዎች በብዙ እጥፍ በተጋነነ ዋጋ ይገዛ ነበር። ከአንድ ድርጅት 21 ጊዜ፣ ከሌላው ደግሞ 15 ጊዜ ግጭ ተፈፅሟል። ከአንድ ድርጅት በአንድ ጊዜ ብቻ የ2015 ሚሊዮን ብር ግዢ ያለጨረታ ተፈፅሟል።
• ከተቋሙ ተልዕኮ ውጪ የተፈፀሙ ግዥዎችም አሉ። ከዚህም ውስጥ የመርከብ ግዢ ይገኝበታል። በማይመለከተውም ስራ ገብቶ ወደ
ንግድ ስራ አስገብቷቸዋል።
ምንጭ፦ EPRDF

አዲስ አበባ ወይስ ጓንታናሞ⁉️
* ጠላት ሀገር እንኳን በዚህ መልኩ አይዘረፍም! ~ ጠቅላይ አቃቢ ህግ ብርሃኑ ጸጋዬ
* አዲስ አበባ ውስጥ 7 ግፍ የሚፈፀምባቸው ድብቅ እስር ቤቶች ተገኙ
* የሰኔ 16ቱ የአዲስ አበባው የቦምብ ጥቃት የብሔራዊ መረጃ ደህንነት አገልግሎት የቀድሞ ኃላፊ የተመራ ነው
*
«በአዲስ አበባ ዜጎች ከሰባት ወደማያንሱ ስውር ማሰቃያ ስፍራዎች ‘በአምቡላንስ እየተጓጓዙ!’ ኢ- ሰብአዊ ድርጊት ይፈጸምባቸው ነበር » በእነዚህ እስር ቤቶች ዉስጥ፦
- ሴቶች ይደፈራሉ
- ወንዶች ግብረሰዶም ይፈፀምባቸዋል
- ወንዶች ብልታቸዉ ላይ ሀይላንድ ይንጠለጠልባቸዋል
- አይናቸውን ታስረው በጫካ ይጣላሉ
*
ፖሊስ ጣቢያ፣ ማረሚያቤት እና ስውር እስር ቤቶች ውስጥ የነበሩ ተጠርጣሪዎችን በአሌክትሪክ ሾክ ማድረግ፣ ብልትን በፒንሳ መሳብ፣ ዛፍ
ላይ ሰቅሎ ለረጅም ጊዜ ማቆየት፣ ጫካ ውስጥ እርቃንን ማሳደር፣ ጥፍር መንቀል፣ በብልት ላይ ውሃ ማንጠልጠል፣ አይናቸው ከታሰረ በኋላ
ከከተማ አውጠቶ ጫካ ውስጥ መጣል፣ አልፎ አልፎ ከአውሬ ጋር በማሰር ማሰቃየት ሲደረግ ነበር
*
የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽንን በተመለከተ፦
ከ2004 እስከ 2010 ድረስ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን 37 ቢሊየን ብር የውጭ ግዢ ፈፅሟል።
እነዚህ ግዢዎች ዓለም አቀፍ ጨረታ ሳይፈፀምባቸው የተከናወኑ ናቸው።
ግዢዎቹ በጥቅም በተሳሰሩ ግለሰቦችና ተቋማት መካከል የተከናወነ ነው።
*
"የሰኔ 16 ቱ የቦምብ ጥቃት የተቀናበረው በብሔራዊ መረጃና ደህንነት ቢሮ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኦሮሞ ስለሆኑ በኦሮሞ ቢገደሉ ተብሎ ነው በሙከራው ኦሮሞዎች እንዲሳተፉ የተደረገው።"
*
ሜቴክ ከ2004-10 ዓ.ም ከ 37 ቢሊዬን (2.5 ቢሊዬን ዶላር) የውጭ ግዢ ያለጨረታ ከውኗል።
የሃገር ውስጥ ግዢ ሙሉ ለሙሉ ያለጨረታ ተከናውኗል።
የሀገር ውስጥ ግዢም በግልፅ ጨረታ መፈፀም ሲገባው እስካሁን በዚህ መልኩ የተፈፀመ የለም። ከኮርፓሬሽኑ አመራሮች ጋር የዝምድናና የጥቅም ትስስር ካላቸው ሰዎች በብዙ እጥፍ በተጋነነ ዋጋ ይገዛ ነበር። ከአንድ ድርጅት 21 ጊዜ፣ ከሌላው ደግሞ 15 ጊዜ ግጭ ተፈፅሟል። ከአንድ ድርጅት በአንድ ጊዜ ብቻ የ2015 ሚሊዮን ብር ግዢ ያለጨረታ ተፈፅሟል።
*
ከተቋሙ ተልዕኮ ውጪ የተፈፀሙ ግዥዎችም አሉ። ከዚህም ውስጥ የመርከብ ግዢ ይገኝበታል። በማይመለከተውም ስራ ገብቶ ወደ
ንግድ ስራ አስገብቷቸዋል
*
በሰብዓዊ መብት ጥሰት ወንጀል 36 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል
*
በአጠቃላይ እስካሁን በቁጥጥር ስር የዋሉ የሜቴክና ደህንነት አመራሮች ቁጥር 63 ሲሆን እስካሁንም ያልተያዙ በአገር ውስጥና ከአገር ውጭ የተደበቁ አሉ።
*
የሰኔ 16ቱ የአዲስ አበባው የቦምብ ጥቃት የብሔራዊ መረጃ ደህንነት አገልግሎት የቀድሞ ኃላፊ የተመራ ነው
*
የመረጃ ደህንነት ኃላፊው ማን እንደሆኑ እያወቃችሁ አታድርቁኝ።
*
ወንጀለኛ የማንም ብሔር ተወካይ አይደለም፡፡
*
በሙስና 27 ሰዎች፣ በሰብዓዊ መብት ጥሰት ደግሞ 36 ሰዎች በአጠቃላይ ከ 63 በላይ ተጠርጣሪዎች መያዛቸውን ነው በመግለጫው የተመለከተው፡፡ ~ ( ከአቃቤ ሕግ መግለጫ

Forwarded from Tomi
https://t.iss.one/joinchat/AAAAAEeU40c64wa6jb9FQg
#Join 👆👆us to get #brands & #quality things at #discount👇👇 ⌚️📱💻🎸👚👖👗👔👟👞👢👠👡👜🎒💄...📦💯
Welcome 🤗🙏 @LovingTomi
join & share

Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ታዋቂ እና አነጋጋሪ መፅሃፍት በገበያ ላይ ዋሉ‼️መፅሀፍቱን በሁሉም መፅሀፍት ቤቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ያገኛሉ። ተጨማሪ በዚህ ስልክ በመደወል መፅሀፍቱን ማግኘት ይቻላል፦ +251911650882
የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ‼️
የኢፌዴሪ ጠቅላይ አቃቤ ህግ አቶ ብርሀኑ ጸጋዬ አሁን በሰጡት መግለጫ መሰረት እስካሁን በቁጥጥር ስር የዋሉት በጥቅሉ 126 አካባቢዎች ናቸው፡፡ ከእነዚህም 63 በሽብር ድርጊት፣ 27 በሙስና፣ 36 ደግሞ በሰብዓዊ መብት ጥሰት ናቸው። ሊብሬ፣ የአክስዮን ደብተር፣ የቤት ሽያጭ ውሎች፣ ጦር መሳሪያዎች ወዘተ በኤግዚብትነት ተይዘዋል። በቁጥጥር ስር የማዋሉ ሂደት ዴሞክራሲያዊ የሆነና የዜጎች መብት ላይ ጥሰት እንዳይፈፀም በጥንቃቄ የተከወነ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ጠቅላይ አቃቤ ህጉ <<አሁንም #የምንጠረጥራቸው ነገር ግን በሃገር ውስጥና በውጪ ተሸሽገው ያሉ አሉ። በውጪ ያሉትን መንግስታቶቹ #አሳልፈው እንዲሰጡን በመነጋገር ላይ ነን። ሀገር ውስጥ ያሉት ደግሞ ራሳቸውን ወደ ሕግ እንዲያቀርቡ እና ሰላማዊ በሆነ መልኩ የፍትህ ሂደታቸውን እንዲከታተሉ ጥሪ እናቀርባለን>> ብለዋል። በቁጥጥር ስር ያልዋሉ ግለሰቦች ለመያዝና የፍርድ ሂደቱ ግልፅነት የተሞላ እንዲሆን በርካታ ስራዎች እንደሚሰሩ ጠቅሰዋል።

ሜቴክ‼️
ሰሞኑን ከታሰሩት የሜቴክ እና ደኅንነት አመራሮች እና አባላት መካከል የተወሰኑት ሥም ዝርዝር ይፋ ወጥቷል፡፡ ከእነዚህም መካከል፦
🔹የሰሜን ጎንደር ደኅንነት ሃላፊ አቶ #አሸናፊ_ተስፋሁን፣
🔹እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የአማራ ክልል ደኅንነት ሃላፊ የነበረው አቶ #ነጋ_ኑሩ፣
🔹በሱማሌ ክልል የደኅንነት ሥራዎችን ሲያስተባብር የነበረው አቶ #ቢኒያም_ማሙሸት፣
🔹በደኅንነቱ ሥር የግንቦት 7 ክትትል ዴስክ ሃላፊ የነበረው አቶ #ሸዊት_በላይ፣
🔹የሐረሬ ክልል ደኅንነት ሃላፊ የነበረው አቶ #ተከተል (የአባት ሥም አልተጠቀሰም)፣
🔹የክትትል መምሪያ ሃላፊ እና የአፋኝ ቡድን ቁልፍ አባል የነበረው አቶ #አጽብሃ_ግደይ እና
🔹የጸረ-ስለላ መምሪያ ሃላፊ የነበረው አቶ #ሳሙዔል (የአባት ሥም አልተጠቀሰም) ይገኙበታል፡፡
በተያያዘ ዜና...
በሙስና ተከሰው የታሰሩት የሜቴክ እና ደኅንነትና መረጃ አመራሮች ዛሬ ከሰዓት በኋላ ፍርድ ቤት #ቀርበዋል። ተጠርጣሪዎቹ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ ልደታ ምድብ 10ኛ ወንጀል ችሎት ነው የቀረቡት፡፡ ፍርድ ቤት ከቀረቡት ውስጥ 36ቱ በሰብዓዊ መብት ጥሰት የተጠረጠሩ ሲሆኑ በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩት ደሞ 27 ናቸው፡፡ አቃቤ ሕግ በሁለቱም ምድብ ተጠርጣሪዎች ላይ የጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው ጠይቋል፡፡
ምንጭ፦ ዋዜማ ራድዮ

የምስራች!!
ውድ የ“TIKVAH-ETHIOPIA” ቤተሰቦች እንደሚታወቀው ቻናላችን ከአንድ አመት በላይ በቴሌግራም መረጃዎች፣ ዜናዎች፣ እንዲሁም መልዕክቶችን ሲያቀርብላችሁ ቆይቷል።
አሁን ደግሞ ተደራሽነቱን በተሻለ ሁኔታ ለማሳደግ ከ“Golden Gear" ጋር በመተባበር የሞባይል መተግበሪያ(Application) ለእናንተ ለማቅረብ ዝግጅት ላይ ነው።
በዚህ Application የሃገር ውስጥ እና የሃገር ውጭ ዜናዎች፣ የቢዝነስ ዘገባዎች፣ የስፖርትና የመዝናኛ ወሬዎች በቀላሉ ማግኘት ትችላላችሁ።
🔹መተግበሪያው(APPLICATION) በቀናት ውስጥ ይለቀቃል!!

#Update ኢሳት የተሰኘው የቴሌቭዥን ጣብያ በቢቢሲ በአመቱ #የሀሰት_ዜና ካሰራጩ ድርጅቶች ዝርዝር ውስጥ ገብቷል። ኢሳት የኦሮሞ ተወላጆች ሶማሌዎችን ጉድጓድ ውስጥ ሲከቱ የሚያሳይ ብሎ የለቀቀው ቪድዮ የሀሰት እንደነበርና ይህም በወቅቱ በኦሮሞዎች ላይ ጥቃት እንዲደርስ ምክንያት ሆኖ እንደነበር ዘግቧል።
🔹በወቅቱ ኢሳት ያሰራጨው የሀሰት ቪድዮ እንደሆነ እና ይቅርታ እንደጠየቀ አይዘነጋም።
A year in fake news in Africa:
https://www.bbc.co.uk/news/world-africa-46127868?fbclid=IwAR3-iV_hmwcfkRd9_hFFhDrYuvWSUynsLGPWoy0wWIFwLky1lZQYIC7MAJw
@Tsegabwolde @tikvahethiopia

BBC News
A year in fake news in Africa
We break down five stories blamed for spreading fear, confusion and even sparking ethnic violence.
ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ‼️
የቀድሞዋ የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ አመራር የነበሩት ወ/ት #ብርቱካን_ሚዴቅሳ ቅንጅት የፈረሰበትን ትክክለኛ ምክንያት ለማናገር አልፈልግም አሉ። ወደ አገር ቤት ከተመለሱ በሁዋላ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ሰፋ ያለ ቃለ መጠይቅ ያደረጉት ወ/ት ብርቱካን፤ “ቅንጅት የፈረሰበት ትክክለኛ ምክንያት ምንድን ነበር?” ተብለው ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ፤ “እውነት ለመናገር አሁን ይሄንን ጥያቄ ልመልስ አልፈልግም፡፡ ልመልስ የማልፈልገው መልስ ስለሌለኝ ወይም ደግሞ ምክንያቱን ስላማላውቀውና ስለማልችል አይደለም” በማለት ምክንያቱን ከመግለጽ ተቆጥበዋል።
ወ/ት ብርቱካን አያይዘውም፤ “እስካሁንም የተነሱትን ነገሮች ሚዲያ ላይ አይቻለሁ፡፡ አሁን አገራችን ከሁላችንም አፋጣኝ ምላሽ የምትፈልግበት ወቅት ነው፤ ከዚያ ይልቅ ሌሎች በጣም አንገብጋቢ ጥያቄዎች አሉ” በማለት የግል አቋማቸውን ግልጽ አድርገዋል። ከዚህ በፊት በነበረን ነገር ማን ጥፋተኛ ነው ፤ ማን የበላይ ነው? ማን የበታች ነው? ማንነው ያፈረስው? ለምን ፈረሰ? የሚለውን ነገር የአካዳሚክ ጥናትም ለሚያደርጉ ሰዎች በጣም ጥሩ የጥናት መስክ ሊሆን ይችላል ያሉት ወ/ት ብርቱካን “አሁን እኔ በዚያ ንትርክ ላይ የመሰማራት ፍላጎትም የለኝም። ለህብረተሰባችንም ዋና ጉዳይ ነው ብዬ አልወስደውም” ሲሉ ገልጸዋል።
ምንጭ፦ Sheger Times

ስውር እስር ቤቶች በአዲስ አበባ‼️
በአዲስ አበባ ከሰባት(7) በላይ የሚደርሱ #የስውር እስር ቤቶች እንዳሉ ተሰምቷል። በሌሎችም የክልል ከተሞች የድብቅ ማሰሪያ ቤት እንዳሉ አቃቤ ህግ ተናግሯል፡፡
ወንጀል ሰርተዋል ተብለው የሰብዓዊ መብት የተጣሰባቸው ሰዎች #በአምቡላንስ ተጭነው እንደሚያዙ አይናቸውም ታስሮ በስውር ማረሚያ ቤት በድብደባ እንዲያምኑ እንደተደረገ በምርመራ መደረሱን የፌዴራል አቃቤ ህግ ተናግሯል፡፡
ይህም ከህገ መንግስቱ ጋር ሙሉ ለሙሉ የተጣረሰ እንደሆነ አቃቤ ህግ #ብርሃኑ_ፀጋዬ ተናግረዋል፡፡
የፖለቲካ ፓርቲ አባላት ተገደው እንዲወጡ ይህንንም ካላደረጉ ከፍተኛ ድብደባ እንደሚፈፀምባቸው ተሰምቷል፤ መሳሪያ እላያቸው ላይ ተተኩሷል፡፡
በሚስጥራዊ እስር ቤት የቆዩ ሰዎችም የተለያዩ ሰብዓዊ መብት #ጥሰት እና #የማሰቃየት ስራ ተደርጓል።
አካልን በኤሌክትሪክ ማንዘር የብልት ቆዳን በፒንሳ መሳብ፣ እስክሪቢቶ አፍንጫ ውስጥ መክተት፣ ጫካ ውስጥ ከአውሬ ጋር እርቃን ማሳደር፣ ምግብ መከልከል እና ሌሎችም የሰው ልጅ ለራሱ ዝርያ ማድረግ የማይገባውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት መደረጉን የጠቅላይ አቃቤ ህግ በአምስት ወር የምርመራ ጊዜ አረጋግጫለው ብሏል፡፡
በዚህም ምክንያት ሴቶች እንደተደፈሩ በወንዶች ላይም የግብረሰዶም ጥቃት እንደተፈፀመ ጨለማ ውስጥም የቆዩ አይናቸው እንደጠፋ የተለያዩ መረጃዎች አስረድተዋል፡፡
ተጠርጥረዋል የተባሉት ኢትዮጵያውያን የራሳቸው ያልሆኑ የጦር መሳሪያዎች እና ሰነዶች ላይ በግድ እንዲፈርሙ በዚህ ሂደትም የተገደሉ እና የተሰወሩ መኖራቸው ታውቋል።
በዚህ መሰረትም ይህንን በደል የፈፀሙ ከፍተኛ የደህንነት መስሪያ ቤት ኃላፊዎች ለምርመራ ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ሻለቃ አትሌት ሀይሌ‼️
ሻለቃ አትሌት ኃይሌ እራሱን ከሃላፊነት ያነሳው ከትላንት በስቲያ በሱሉልታ አትሌቶች በፌደሬሽኑ ላይ ያነሱትን #ቅሬታ ተከትሎ ነው። የኢትዮጵያ አትሌትክስ ፌዴሬሽን አስቸኳይ ጠቅላላ #ጉባኤ በመጥራት ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል። የአትሌት ኃይሌ ገብረሰላሴ የመልቀቂያ ጥያቄም በጉባኤው ውሳኔ ይሰጠዋል ተብሎ ይጠበቃል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሻለቃ አትሌት ኃይሌ እራሱን ከሃላፊነት ያነሳው ከትላንት በስቲያ በሱሉልታ አትሌቶች በፌደሬሽኑ ላይ ያነሱትን #ቅሬታ ተከትሎ ነው። የኢትዮጵያ አትሌትክስ ፌዴሬሽን አስቸኳይ ጠቅላላ #ጉባኤ በመጥራት ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል። የአትሌት ኃይሌ ገብረሰላሴ የመልቀቂያ ጥያቄም በጉባኤው ውሳኔ ይሰጠዋል ተብሎ ይጠበቃል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቦንጋ እየተረጋጋች ነው‼️
በካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ ከቡና መገኛነት ጋር ተያይዞ በድረ-ገጽ በተላለፈ መረጃ የተፈጠረው ችግር በመቃለሉ ወደ #መረጋጋት መመለሱን የዞኑ ባህል፣ ቱሪዝምና መንግስት ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ አስታወቀ፡፡
የመምሪያው ኃላፊ አቶ #አስረስ_አዳሮ ለኢዜአ እንደገለጹት በተፈጠረው ችግር ምክንያት በከተማዋ ላለፉት አምስት ቀናት ትራስንፖርትና ማህበራዊ አገልግሎቶች ተቋርጠው ነበር፡፡
ይህም የአካባቢውን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴ እንደሚጎዳ የዞኑ አስተዳደር ከወጣቱንና ከሌላውም የህብረተስብ ክፍል ጋር ተወያይቶ መግባባት ላይ በመድረሱ ከትናንት ማምሻውን ጀምሮ ከተማዋ ወደ መረጋጋት መመለሷን አስረድተዋል፡፡
የትራንስፖርት አገልግሎትም ጀምሯል፡፡
የቡና መገኛነት ጉዳይ መነሻ ሆኖ ለዓመታት የቆየው የቡና ሙዚየም ስራ አለመጀመር ህዝቡን እንዳስቆጣውም ኃላፊው ጠቁመዋል፡፡
ከኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ልማትና ግብይት ባለስልጣን የተሰጠው ይቅርታና የቡና ሙዚየም ግንባታ ስራው እንደሚጀምር የሰጠው መግለጫ ህዝቡን እንዳረጋጋው ተናግረዋል፡፡
ከህዝቡ የተነሱ ጥያቄዎች ከክልልና ከፌደራል መንግስት ጋር በመነጋገር ምላሽ እንዲያገኙ ለመስራት መስማማት ላይ በመድረሳቸው የግልና የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ወደቀድሞ ስራቸው መግባታቸውን ገልጸዋል፡፡
አካባቢውን ወደ ሰላማዊ ሁኔታ ለመመለስና መንገዱን ለማስከፈት በተደረገው ጥረት የወጣቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ድርሻ ከፍተኛ እንደነበረ አስታውቀዋል፡፡
ከከተማዋ ነዋሪዎች መካከል አቶ ገብረሚካኤል ወልደማርያም በሰጡት አስተያየት በታሪክ የሚታወቀው የከፋ ቡና መገኛነት በተለያዩ ተቋማት የተሳሳተ መረጃ በመሰጠቱ ህዝቡን ማስቆጣቱን ተናግረዋል፡፡
ህዝቡ ያነሳቸውን ጥያቄዎች የዞኑ አስተዳደር ኃላፊነት ወስዶ እንደሚያስፈጽም ሃላፊነት በመውሰዱ ተፈጥሮ የነበረው አለመረጋጋት ወደ ነበረበት መመለሱን ገልጸዋል፡፡
መንግስት የሀዝቡን ጥያቄ በፍጥነት መመለስ እንዳለበትና ጉዳዩ ዳግም ጥያቄ የሚያስነሳ መሆን እንደሌለበት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ሌላኛው የከተማው ነዋሪ አቶ ረጋሳ ጸጋዬ በበኩላቸው ባለፉት ቀናት የተካሄደው ሰልፍ ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ መጠናቀቁን ገልጸው ጥያቄው ተገቢነት ያለው በመሆኑ በመንግስት በኩል ምላሽ ያገኛል ብለው እንደሚጠብቁ ተናግረዋል፡፡
“ቡናና ከፋ ከስያሜው ጀምሮ ጥብቅ ቁርኝት ያለው እና ታሪካዊ የሰነድ ማስረጃዎች የሚያረጋግጡ ሆኖ ሳለ የተላለፈው መረጃ መዛባት ለችግሩ ምንጭ ሆኗል “ያሉት ደግሞ አቶ ብርሃኑ ገብሬ ናቸው፡፡
የዞኑ አስተዳደር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ጉዳዩ የመጨረሻ እልባት እንዲያገኝ ማድረግ እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡
ምንጭ፦ ኢዜአ