TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አሳዛኝ ዜና‼️

በመተማ ዮሐንስ ትላንት ረፋዱ ላይ ቤት ውስጥ #ተደብቀው ተኩስ በከፈቱ አካላት በ23 ሰዎች ላይ #የሞትና የአካል #መቁሰል አደጋ መድረሱን የምዕራብ ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።

የመምሪያው ሃላፊ ኮማንደር #ጌትነት_አልታሰብ ማምሻውን ለኢዜአ እንደገለፁት ከረፋዱ 4 ሰዓት አካባቢ በቤት ውስጥ መሽገው በተከቀመጡ ግለሰቦች በተከፈተ ተኩስ የ3 ሰዎች ህይዎት ሲያልፍ በ20 ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት  ደሷል።

የቅማንት ማህበረሰብ ተቆርቋሪ ነኝ በሚሉ አካላት በከተማው ባለ የመኖሪያ ቤት ውስጥ በመመሸግ በመንገድ ይጓዙ በነበሩ ሰላማዊ ሰዎች ላይ በከፈቱት ተኩስ ጉዳቱ ሊደርስ መቻሉን ገልፀዋል።

ጉዳቱ ከደረሰባቸው መካከልም አንድ የፀጥታ አካልን ጨምሮ ሴቶችና ወጣቶች ይገኙበታል ብለዋል።

ጉዳቱን ካደረሱት አካላት መካከልም አራቱ እጃቸውን የሰጡ ሲሆን ቀሪዎቹ በሰላማዊ መንገድ ለፀጥታ ሃይሉ እጃቸውን እንዲሰጡ እየተጠየቁ ነው  ብለዋል።

ጉዳት ካደረሱት ግለሰቦችም 9 የክላሽንኮቭ፣ አንድ ኤፍ ኤን መሳሪያ፣አንድ ሽጉጥ፣ አንድ ቦንብና በርካታ ጥይት ተይዟል ሲሉም ኮማንደር ጌትነት አስታውቀዋል።

በደረሰው ጉዳት ህይወታቸው ያለፈ ግለሰቦች አስከሬን ወደ ቤተሰቦቻቸው የተላከ ሲሆን የቆሰሉት ሰዎች ደግሞ በመተማ ዮሐንስ ጤና ጣቢያ፣ በገንዳ ውሃ ሆስፒታልና በጎንደር ሪፈራል ሆስፒታል ህክምና እየተደረጋላቸ ነው ብለዋል።

ለዘመናት ተሳስሮ በኖረው የአማራና የቅማንት ማህበረሰብ መካከል ግጭት ለመፍጠር የሚንቀሳቀሱ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ያሳሰቡት ከማንደሩ፤ ችግሩ አስኪበርድ የአካባቢው የሃይማኖት አባቶችና የሃገር ሽማግሌዎች ህብረተሰቡን በማስተማር የድርሻቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል።

ወጣቱ የአካባቢውን ሰላም በመጠበቅ  ከፀጥታ ሃይሉ ጎን በመሰለፍ ጥፋተኞችን የመለየትና በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ በማደረግ ማገዝ እንዳለበትም ጥሪ አቅርበዋል።

በመተማ ዩሐንስ ከተማ ረፋዱ አካባቢ በተፈጠረው  ግጭትም የፌደራል መከላከያ ሰራዊት፣ የክልሉ ልዩ ሃይል፣ የፖሊስ አባላትና የአካባቢ ሚሊሻዎች በጋራ በመሆን ወደ  አካባቢው እንዲረጋጋ ጥረት አድርገዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia