TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከመቐለ ዩኒቨርሲቲ⬇️

በመቐለ ዩኒቨርስቲ የሰው ህይውት #አልፏል ተብሎ በድብቅ /በሽፋን/ በተከፈቱ በውስን ማኅበራዊ ሚዲያዎች (በTwitter እና Facebook) እየተገለፀ ያለው መረጃ የሃሰት እና ሙሉ በሙሉ ከእውነት የራቀ መሆኑን #እናረጋግጣልን

በመቐለ ከተማም ሆነ በዩኒቨርስቲያችን በተማሪ ላይ ምንም አይነት ጥቃት እና አደጋ ያልደረሰ መሆኑን በድጋሜ እናረጋግጣልን

ባደረግነው ማጣረት የውሸት መረጃዎቹ እየተሰረጩ ያሉት በድብቅ /በሽፈን/ በተከፈቱ ውስን የማኅበራዊ ሚዲያዎች ሲሆን፣ በአገረችን የተጀመረውን ሰላማዊ የመማር እና ማስተማር ሂደት #ለማወክ
/ለማበላሸት/ ዓላማ ያደረገ ነው።

በዚሁ አጋጣሚ ባደረግነው ዳሰሳ በትግረይ ክልል በሚገኙ በሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሙሉ በሙሉ የመማር ማስተማር ኢደቱ ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንደቀጠለ ነው።

እነዚህን የውሸት መረጃዎች በጋራ በመከላከል እና ትክክለኛ መረጃዎችን ብቻ በመስጠት እና በማሰረጨት ሃላፊነታችንን እንወጣ።

ይህን መልዕክት Share በማድረግ ለሌሎች እናስተላልፍ!
፨፨፨
The safety of our students and providing quality academic service are utmost priority of our university. We Really Care!

መቐለ ዩኒቨርሲቲ
ጥቅምት 25/2011
@tsegabwolde @tikvahethiopia