TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የከፍተኛ አመራሮች ስልጠና እና ውይይት #ተጠናቋል

በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ:-

ከ20ውም የሚኒስቴር መ/ቤት የሚጠበቁ ያሏቸውን ዋና ዋና የውጤት አመልካቾችን ባጭሩ ገልጸው እነዚህ ተዘርዝረው በየሚኒስቴር መ/ቤቱ የ100 ቀናት ዕቅድ ውስጥ እንዲካተቱ አመራር ስጥተዋል። የተዋሃዱ የሚንስቴር መ/ቤቶች ወይም ተጠሪዎች ወይም ሌላ የተልዕኮ ወይም የአደረጃጀት ለውጥ የተደረገባቸው ተቋማት ፈጥነው በማስተካከልና ለሰራተኞቻቸው በቂ ኦረንቴሽን በመስጠት ወደ ተግባር እንዲገቡ አሳስበዋል። በቢሮና ንብረት ርክክብ ብዙ ጊዜ መባከን እንደሌለበትም አስገንዝበዋል::

ምንጭ፦ EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update በ555 ሚሊዮን ብር ወጪ እየተገናባ የሚገኘው የሸጎሌ ዲፖ ከ95 በመቶ በላይ ስራው #ተጠናቋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ምክት ከንቲባ ዶክተር #ሰለሞን_ኪዳን የዲፖውን የግንባታ አፈጻጸም ጎብኝተዋል፡፡ ዲፖው ከ3 ወር ብኋላ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር የዲፖው ስራ አስካጅ አቶ ናትናኤል ጫላ በጉብኝቱ ላይ ገልጸዋል ፡፡ ዲፖው ወደስራ ሲገባ ለ3 መቶ ሰዎች የስራ እድል እንደሚፈጥርም ስራ አስካጁ ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና‼️

"ወንጀል ሰርተው ከሀገር የወጡ የሱማሌ ክልል #ባለስልጣናትን በህግ ተጠያቂ ለማድረግ ዝግጅት #ተጠናቋል"- ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ
.
.
.
በሱማሌ ክልል በተፈጠረው ግጭት እጃቸውን በማስገባት ወንጀል ሰርተው ከሀገር የወጡ ባለስልጣናትን ወደሀገር #በመመለስ በህግ ተጠያቂ ለማድረግ ከተሸሸጉባቸው ሀገራት ጋር ስምምነት ላይ መደረሱን የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አስታወቀ።

የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ #ዝናቡ_ቱኑ ዛሬ ከሰዐት በፅ/ቤታቸው በሰጡት መግለጫ 46 ያህል ተጠርጣሪዎች በሱማሌ ክልል በተፈጠረው ግጭት የሰው ህይወት #እንዲጠፋ፣ ህገመንግስታዊ ስርዐትን ለመናድ በመንቀሳቀስ ንብረት እንዲወድምና በተያያዥ ወንጀሎች መጠርጠራቸውን የተናገሩ ሲሆን ስድስት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል ሌሎቹ 40 ግን በሀገር ውስጥና በውጪ ሀገር ተሸሽገዋል ብለዋል።

እንደ አቶ ዝናቡ ገለፃ ከሀገር የወጡ ባለስልጣናትን ወደሀገር በመመለስ በህግ ተጠያቂ ለማድረግ ከተሸሸጉባቸው ሀገራት ጋር ስምምነት ላይ መደረሱን በሀገር ውስጥ የተደበቁትንም አፈላልጎ በህግ ተጠያቂ ለማድረግ እየተሰራ ነው።

የተወሰኑ ተጠርጣሪዎች #ያለመከሰስ መብት ያላቸው በመሆኑ መብታቸውን #በማንሳት በቁጥጥር ስር ለማዋል ስራዎች እየተሰሩ ነው ተብሏል።

ወንጀለኞችን በቁጥጥር ስር ለማዋል ትልቅ ዝግጅት ተደርጓል ያሉት አቶ ዝናቡ ህዝቡ የተሸሸጉ ግለሰቦችን አሳልፎ በመስጠት ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ አስተላልፈዋል።

ምንጭ፦ ኢ.ፕ.ድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETH ማጠቃለያ🗞ጥር 19/2011 ዓ.ም.

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያስገነባው ስካይ ላይት ሆቴል ዛሬ ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት በይፋ ተመርቆ ተከፍቷል፡፡
.
.
#ሐሰተኛ_የማስተርስና_የዶክትሬት ዲግሪዎች እንዲሰጡ አድርገዋል የተባሉት የሜቴክ ኃላፊዎች ላይ ክስ ተመስርቷል።
.
.
በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ #የድሬዳዋ ተወላጆች በዛሬው ዕለት በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተገኝተው ያላቸው ተቃውሞ እና ቅሬታ አሰምተዋል። የፌደራሉ መንግስት ለድሬዳዋ ከተማ ልዩ ትኩረት እንዲሰጥና ያሉ ችግሮችን እንዲፈታ ጠይቀዋል።
.
.
#የሰላሌ_ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ትናንት ቅዳሜ "አንድ ቀን ለማህበረሰቤ" በሚል መሪ ሀሳብ #ፍቼ ከተማን ሲያፀዱ ውለዋል።
.
.
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ #ደመቀ_መኮንን በደቡብ ክልል በጋሞ ዞን ቆላማ አካባቢ የስንዴ ግብርና ልማት የሙከራ ፕሮጀክትን ጎብኝተዋል።
.
.

4ኛው የኢህአዴግ የወጣቶች ሊግ ድርጅታዊ ጉባዔ #በሃዋሳ_ከተማ ዛሬ ተጀምሯል። ጉባዔው "በተጠናከረ የወጣቶች ትግል ሀገራዊ ለውጡን ወደፊት" በሚል መሪ ቃል እስከ ጥር 19 እስከ 21 በተለያዩ ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ እየመከረ ይቆያል፡፡
.
.
በቤኒሻንጉል ጉሙዝና ኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን አጎራባች ወረዳዎች በተከሰተው #ግጭት ምክንያት የተፈናቀሉ ወገኖች መልሶ በሚቋቋሙበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሂዷል።
.
.
በጅማ ከተማ "ንግዳችንን እናዘምን" በሚል መሪ ቃል የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር በዛሬ ዕለት ተካሂዷል።
.
.
ትውልደ ኢትዮጵያዊው ቢሊየነር ሼህ መሃመድ ሁሴን አሊ አላሙዲ ከእስር መፈታታቸው ተሰምቷል።
.
.
የቀድሞ ጦር ማህበር #የምስረታ_ጉባዔ ዛሬ #በደብረማርቆስ ፖሊስ ኮሌጅ ተካሂዷል።
.
.
ለአራት ቀናት በመቀለ ሲካሄድ የቆየው የትግራይ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት የአምስተኛው ዘመን 14ኛው መደበኛ ጉባኤ አዋጆችንና ሹመቶችን በማጽደቅ #ተጠናቋል
.
.
የድሬዳዋን ሰላምና ፀጥታ #አስተማማኝ በማድረግ የህዝብ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች እንዲፈቱ እንደሚሰራ #በምስራቅ_ዕዝ_መከላከያ የሚመራው ጊዜያዊ የፀጥታ ጥምር ኮሚቴ አስታውቋል።
.
.
ምንጭ፦ ኢዜአ፣ DW፣ ኢ.ፕ.ድ.፣ የጠ/ሚ ፅ/ቤት፣ የምክትል ጠ/ሚ ፅ/ቤት፣ etv፣ ዋልታ፣ ፋና፣ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት
.
.
ሰላም እደሩ!!
የነገ ሰው ይበለን!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የደኢህዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ልዩ ስብሰባ #ተጠናቋል። ዝርዝር #መግለጫ ይሰጣል ተብሏል። #ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ተጠናቋል

የቁስቋም-እንጦጦ መንገድ ተገንብቶ ተጠናቋል

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ጫካውን በመሰንጠቅ በአጭር ጊዜ ፣ በከፍተኛ ጥራት ግንባታውን ያከናወነው የባለስልጠን መሥሪያ ቤቱ ራስ ኃይል መንገድ ግንባታ ክፍል ነው ሲል አሳውቋል።

3.6 ኪ.ሜ. የሚረዝመው ይህ የጫካ ውስጥ ውበት አስቸጋሪውን አሮጌ መንገድ በመተካት የእንጦጦን ጉዞ አቅልሎታል ተብሏል።

ምንጭ፦ የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን

@tikvahethiopia
#ተጠናቋል

የሐዋሳ አውሮፕላን ማረፊያ ቢሻን ጉራቻ የመንገድ ግንባታ ተጠናቋል

35 ኪሎ ሜትር የሚረዝመው የሐዋሳ አውሮፕላን ማረፊያ ቢሻን ጉራቻ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።

የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቱ ሁለት ክፍሎች ያሉት ሲሆን፥ የመጀመሪያው 14 ኪሎ ሜትር ከቢሻን ጉራቻ በመነሳት ወደ ሐዋሳ አውሮፕላን ማረፊያ የሚሄድ ነው።

መንገዱን ገንብቶ ለማጠናቀቅ የወሰደው 592 ሚሊየን 84 ሺህ ብር ወጪ በኢትዮጵያ መንግስት የተሸፈነ ሲሆን፥ የመንገዱን ግንባታ አለም አቀፉ የስራ ተቋራጭ ቻይና ኮሙኒኬሽን ኮንስትራክሽን ኩባንያ አከናውኖታል።

በማማከርና በቁጥጥር ስራው የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ሱፐርቪዥን ኮርፖሬሽን መሳተፉን ከኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የህዝብ ግንኙነት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር

@tikvahethiopia
#ተጠናቋል

የእንጦጦ ፖርክ የመኪና ማቆሚያ የግንባታ ስራ መጠናቀቁ ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በቅርቡ ስራ የጀመረው የእንጦጦ ፖርክ የመኪና ማቆሚያ የግንባታ ስራ ሙሉ በሙሉ ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት መሆኑን አሳውቋል።

ይህ ኘሮጀክት በአጠቃላይ ሶስት የመኪና ማቆሚያ ግንባታዎችን የያዘ ሲሆን ሁለቱ በእንጦጦ ፖርክ ዋና መግቢያ በር እንዱሁም ሶስተኛው በሱሉልታ መግቢያ በኩል የተገነቡ ናቸው፡፡

እነዚህ የመኪና ማቆሚያዎች 14,063 ሜትር ስኩዌር ስፋት ያላቸው ሲሆን በአንድ ጊዜ 450 መኪኖችን ማቆም የሚችሉ ናቸው፡፡

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ተጠናቋል

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የመጀመሪያ ዙር የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ  የማህበራዊ ሳይንስ ፈተና መጠናቀቁን አሳውቋል።

አገልግሎቱ ፤ " የፈተና ኩረጃና ስርቆት ከፍተኛ የፈተና ደንብ ጥሰት ናቸው። ህግ ይከበራል። " ብሏል።

ለስራው መጠናቀቅ አወንታዊ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ምስጋና አቅርቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ተጠናቋል

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ እና በጦርነት ምክንያት ተቋርጦ የነበረው 5ኛ ዓመት የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የመፅሀፍ ማሰባሰብ ዘመቻ ተጠናቆ መፅሀፍቱ ታሽጎ ተልኳል።

ካለው የተማሪ ቁጥር አንፃር  ማድረግ የቻልነው እጅግ ጥቂት ቢሆንም በቀጣይ ወራት ተጨማሪ ዘመቻ በማድረግ ከቤተሰባችን አባላት ቤት መፅሀፍ በመውሰድ ተጨማሪ ለመላክ ጥረት እናድረጋለን።

በዚህ ስራ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ያለማንም የጀርባ አጋዥ / አካል በራሳቸው መፅሀፍ ያበረከቱ ፣ ያስላኩ፣ መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን።

የአዲስ አበባ አባላት በዚህ ዙር ከ7 ሺህ መፅሀፍ በላይ አበርክተዋል።

@tikvahethiopia