TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ‼️

ማሳሰቢያ፦

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የ2011 ዓ.ም የመደበኛ ተማሪዎች ቅበላ ከጥቅምት 10 እስከ 14/2011 ዓ.ም ድረስ ማካሄዱ ይታወሳል፡፡

ዩኒቨርሲቲው የምዝገባ ስርዓቱን አጠናቆ መደበኛ የመማር ማስተማር ሂደት ውስጥ የገባ ሲሆን ለሠላማዊ የመማር ማስተማር መስፈን ከውጫዊና ውስጣዊ ባለድረሻ አካላት ጋር በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል፡፡

ነገር ግን ዩኒቨርሲቲው በሚገኝበት አካባቢ ምንም አይነት የፀጥታ እና የደህንነት ስጋት ሳይኖር ተማሪዎችን ሆን ብሎ ለማወክና በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ውስጥ #ረብሻ እንደተከሰተ ተደርጎ በማህበራዊ ድረ ገፅ #እየተወራ ይገኛል፡፡

በመሆኑም ይህ መሰረተ ቢስ #ወሬ እንደ ሆነ ታውቆ ተማሪዎችና የተማሪ ወላጆች አንዳች #ስጋት እንዳይገባቸሁ ተቋሙ #ያሳስባል፡፡

መደበኛ የመማር ማስተማር ስራው ሳይስተጓጎል ተጠናክሮ እንዲቀጥል ባለድርሻ አካላት የተለመደ ትብብራቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ እና አስፈላጊውን ትብብር ሁሉ እንዲያደርጉ ዩኒቨርሲቲው ያሳስባል፡፡

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ
ጥቅምት 23/2011 ዓ.ም.
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የተመን ማሻሻያ‼️

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አዲስ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተመን #ማሻሻያ
ማድረጉን አስታወቀ።

የአገልግሎቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ #ሽፈራው_ተሊላ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት፥ አዲሱ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተመን ከፊታችን ታህሳስ ወር ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ ነው።

የዋጋ ንረትና አለም ላይ ያለው የሃይል ተመን ለማሻሻያው ምክንያት መሆናቸውንም ዋና ስራ አስፈጻሚ ተናግረዋል።

አሁን በተደረገው ማሻሻያ መሰረትም ተጠቃሚው ከ12 አመት በፊት በነበረው የሃይል ዋጋ ተመን መሰረት የሚከፍል ይሆናል ነው ያሉት።

በተመኑ መሰረት ተጠቃሚው የወጭውን 25 በመቶ ሲሸፍን ቀሪው 75 በመቶ ደግሞ በመንግስት ድጎማ የሚደረግበት ነው ተብሏል።

ማሻሻያው በሰባት እርከኖች የተከፈለ ሲሆን፤

እርከን 1: እስከ 50 ኪሎ ዋት ለሚጠቀሙ ከዚህ ቀደም በነበረው ክፍያ በኪሎ ዋት 0 ነጥብ 2730 ብር ይቀጥላል፤

እርከን 2: እስከ 100 ኪሎ ዋት ለሚጠቀሙ ከዚህ ቀደም በኪሎ ዋት 0 ነጥብ 6644 ብር የነበረው በአዲሱ ተመን 0 ነጥብ 7670 ብር፤

እርከን 3: እስከ 200 ኪሎ ዋት ለሚጠቀሙ ከዚህ ቀደም በኪሎ ዋት 1 ነጥብ 3436 ብር የነበረው በአዲሱ ተመን 1 ነጥብ 6250 ብር፤

እርከን 4: እስከ 300 ኪሎ ዋት ለሚጠቀሙ ከዚህ ቀደም በኪሎ ዋት 1 ነጥብ 6375 ብር የነበረው በአዲሱ ተመን 2 ብር፤

እርከን 5: እስከ 400 ኪሎ ዋት ለሚጠቀሙ ከዚህ ቀደም በኪሎ ዋት 1 ነጥብ 7917 ብር የነበረው በአዲሱ ተመን 2 ነጥብ 2000 ብር፤

እርከን 6: እስከ 500 ኪሎ ዋት ለሚጠቀሙ ከዚህ ቀደም በኪሎ ዋት 1 ነጥብ 9508 ብር የነበረው በአዲሱ ተመን 2 ነጥብ 4050 ብር እንዲሁም

እርከን 7: ከ500 ኪሎ ዋት በላይ ለሚጠቀሙ ከዚህ ቀደም በኪሎ ዋት 2 ነጥብ 0343 የነበረው በአዲሱ ተመን 2 ነጥብ 4810 ብር ይሆናል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Update በጋምቤላ ክልል አበቦ ወረዳ ከኢንቨስትመንት ስራዎች ጋር በተያያዘ አለ በሚባለው #የንቅዘትና #የሌብነት ጉዳይ ላይ የምርመራ ጋዜጠኝነት ሥራ ለመስራት በሄድንበት ተደብድበናል፣ ታስረናል ያሉት ጋዜጠኞች ወደ ኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ጉባኤ አቤት አሉ፡፡

ምንጭ፦ ሸገር 102.1
@tsegabwolde
#Update በ555 ሚሊዮን ብር ወጪ እየተገናባ የሚገኘው የሸጎሌ ዲፖ ከ95 በመቶ በላይ ስራው #ተጠናቋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ምክት ከንቲባ ዶክተር #ሰለሞን_ኪዳን የዲፖውን የግንባታ አፈጻጸም ጎብኝተዋል፡፡ ዲፖው ከ3 ወር ብኋላ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር የዲፖው ስራ አስካጅ አቶ ናትናኤል ጫላ በጉብኝቱ ላይ ገልጸዋል ፡፡ ዲፖው ወደስራ ሲገባ ለ3 መቶ ሰዎች የስራ እድል እንደሚፈጥርም ስራ አስካጁ ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአማራ ክልል ምክር ቤት ዛሬ መደበኛ ስብሰባውን ማካሄድ ጀመረ፡፡ ምክር ቤቱ ዛሬ ማካሄድ የጀመረው አምስተኛ የስራ ዘመን፣ አራተኛ ዓመት አስራ አንደኛ መደበኛ ጉባዔውን ነው፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update አዳማ ከተማ ላይ ዛሬ ሀገር ዐቀፍ የተማሪ ወላጆች ኅብረት #ተመስርቷል፡፡ የትምህርት ሚንስቴር ደዔታ መሐመድ አሕመድ ሀገር ዐቀፉን ኅብረት ይመራሉ፤ ከዘጠኙ ክልሎች እና ከአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ የተውጣጡ 11 የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት እና ወደፊት ምክር ቤትም ይኖረዋል ተብሏል፡፡ አላማው የተማሪ ወላጆችን ከመንግሥት መዋቅሮች ጋር በቀጥታ በማገናኘት ለትምህርት ጥራት በጋራ
መስራት ነው፡፡

©ኢዜኣ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ንቁ! #ሰውነት_ከምንም_ይበልጣል!
ሀገር
ብሄር
ዜግነት
ባንዲራ...ሁሉም ነገር እኛ እንደሰው ልጅ ካልተከበርን #አይጠቅሙንም። ሰው ሲገደል፣ ሰው ሲደበደብ፣ ሰው ሲፈናቀል ልባችን #ሊደማ የሚገባው የኛ #ብሄር ተወላጅ ስለሆነ አይደለም እንደኛ ሰው #ብቻ ስለሆነ መሆን አለበት። ያን ጊዜ ለሰማይም ለምድርም መልካም ስራን ሰርተን ማለፍ እንችላለን። ከሁሉም የሚበልጠው ሰውነት ብቻ ነው። ትግሬው የአማራው፤ አማራው የትግሬው ሞት ካላስለቀሰው፣ ኦሮሞው የአማራው፤ አማራው የኦሮሞው ሞት እና ስቃይ ካልተሰማው፣ ኦሮሞው የጋሞው ጋሞውም የኦሮሞው ችግር እና መከራ ካልተሰማው፣ ሲዳማው የወላይታው፤ ወላይታው የሲዳማው ሞት እና ስቃይ ካላስለቀሰው ችግሩ #የፖለቲካ ሳይሆን የሰውነት ስሜት መጥፋት ነው። የሰውነት ስሜት መጥፋት ደግሞ በቁም #መሞት ነው።

መፍትሄው....

እኔም አንተም አንቺም በገባን ልክ ስለሰው ክቡርነት እናስተምር። በየቤታችን ስለሰውነት እንነጋገር። ታች ወርደን ስለሰውነት እናስተምር። ሁላችንም ትልቅ ሀላፊነት አለብን! መጀመሪያ ሰው ሁሉ እንዲከበር፣ እንዲወደድ፣ እንዲፈቀር እንስራ!


ፀጋአብ ወልዴ
#ETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሼር⬆️ከላይ ያለውን ፅሁፍ ማውጣት ያለባችሁን ቃላት አውጥታችሁ(ስሙን ይጨምራል) በፌስቡክ ገፃችሁ ላይ ለጥፉት። #ንቁ በሚል በየዕለቱ ዘመቻ እናካሂዳለን።

ከፖለቲካው በፊት ስለሰው ክቡርነት ጠንቅቀን ማወቅ አለብን!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሁሉም ውስጡ #ስጋና #ደም
ቀለም መልኩ ቢለያይም
ወላጁ #አንድ ነው አባቱ አንድ ነው
ዞሮ ዞሮ #አዳም
.
.
ሰውነት ይከበር!
ሰውነት ይቅደም!
#ETHOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ላለፉት 5 ቀናት #ዝግ ሆኖ የቆየው አማራ ክልልን ከትግራይን ክልል የሚያገናኘው መንገድ መከፈቱን ነዋሪዎች ገልፀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የአማራ ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዙር ፤4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 11ኛ መደበኛ ጉባኤ የሁለተኛ ቀን ውሎውን ጀምሯል፡፡ አሁን ላይ የጠቅላይ አቃቢ ህግ ጉዳዮችን እየተመለከተ ነው፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አርቲስት ፍቃዱ ተ/ማርያም‼️

"በአርቲስት ፍቃዱ ተ/ማርያም ስም በጎፈንድሚ የተሰበሰበውን 73 ሺህ 9 መቶ ዶላር ወደ አካውንት #ለማስገባት ፈቃደኛ አይደለሁም። ምክኒያቱም በኮሚቴው እምነት የለኝም።" አርቲስት #ቴዎድሮስ_ተሾመ

"በአርቲስት ፍቃዱ ተ/ማርያም ስም በጎ ፈንድሚም ሆነ በማናቸውም መልኩ የተሰበሰበው ገንዘብ በስሙ ወደተከፈተው የባንክ አካውንት መግባት አለበት።" የአርቲስት ፍቃዱ ተ/ማርያም የህክምና ገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴ

ይህ እሰጣ ገባ የተካሄደው ትላንት በአፍሮዳይት ሆቴል የአርቲስት ፍቃዱ ተ/ ማርያም የህክምና ገቢ ለማሰባሰብ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጠው ኮሚቴ በጠራው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው።

ኮሚቴው ለሁለት የተከፈለበትን ጉዳይ አንስቶ ባቀረበው ሪፖርት ላይ እንደገለጹት በአርቲስት ፍቃዱ ተ/ማርያም ስም የተሰበሰበው ገንዘብ ጉዳይን አስመልክቶ የተጓዘባቸውን ርቀቶች ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን ከአርቲስት ፍቃዱ የህክምና ገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴ አማካኝነት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተው አካውንት ላይ በአሁኑ ወቅት 1,200,895.69 (አንድ ሚልዮን ሁለት መቶ ሺህ ስምንት መቶ ከስልሳ ዘጠኝ ሳንቲም) ብር በአካውንቱ ላይ እንደሚገኝ ገልጸው ቀሪውን በጎፈንድሚ የተሰበሰበውን 73,900 ዶላር ወደ አካውንት እንዲያስገባ ለቴድሮስ ተሾመ ተደጋጋሚ ጥያቄዎችን ለመቀበል እንዳልቻለና በኮሚቴው አባላት ላይ እምነት #የለኝም በማለቱ ልዩነት እንደተፈጠረ ገልጸዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ጥቅምት 23 ቀን 2011 ዓ.ም በጊዮን ሆቴል ተሰብስቦ የወሰነውን ቃለ ጉባኤ በንባብ አስደምጧል። ይህንን አስመልክቶም ምላሽ የሰጠው አርቲስት ቴዎድሮስ ተሾመ "ህዝብ ገንዘቡን የሰጠኝ የእኔን ስም አይቶ ነው። በአርቲስት ፍቃዱ ተ/ማርያም ስም የተሰበሰበውን ገንዘብ በኮሚቴው የአስተዳደር ችግር ምክንያት እምነት ስለሌለኝ ገንዘቡን ወደ ተባለው አካውንት ገንዘቡን አላስገባሁም። ወደፊትም በዚህ ገንዘብ ላይ ሙሉ ሀላፊነቱን የምወስደውም ሆነ እየወስድኩ ያለሁት እኔ ነኝ። ጠበቃዬም ገንዘቡን ገቢ እንዳላደርግ አማክሮኛል። ለዚህም ለህሊናዬም ሆነ ለፈጣሪ ታማኝ በመሆን ገንዘቡን ህጋዊ ወራሽ ይሆናሉ ብዬ ለማስባቸው ቤተሰቦቹ ጥቅምና ለሀውልቱ ማሰሪያ እንዲሆን እየተንቀሳቀስን ነው" ብሏል።

ሌሎች የኮሚቴ አባላት ደግሞ በአጠቃላይ የተሰበሰበውን ገንዘብ ወደ አንድ ቋት እንዲገባና ፍርድ ቤት የሚያሳውቃቸውን ህጋዊ ወራሾች መጠበቅ አለበት የሚል አቋም ይዘዋል።

ለአርቲስት ፍቃዱ ተ/ማርያም ስም ከህዝብ የተሰበሰበው ገንዘብ መጨረሻ ምን ይሆን? አሁንም ምላሽ የለውም። በአርቲስት ፍቃዱ ተ/ማርያም ስም በተሰበሰበው ገንዘብ ላይ የተነሳው ንትርክ ከዚህ በኋም የጤና እክል የሚያገጥማቸው የኪነጥበብ ባለሙያዎችን ህዝብ በአግባቡ እንዳያግዝ የራሱን አሉታዊ ተጽዕኖ እንዳያሳርፍ ስጋት አጭሯል።

ምንጭ፦ ጴጥሮስ አሸናፊ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት በኤርትራ ላይ ጥሎ የቆየውን ማእቀብ #ሊያነሳ ነው። ማእቀቡ የሚነሳው ከ11 ቀናት በሁዋላ በሚደረግ ስብሰባ ላይ ሲሆን ይህም የሚሆነው አሜሪካ በኤርትራ ላይ ይዛው የቆየችውን አቋም በመቀየሯ ነው ተብሏል። ማእቀቡ ከተነሳ በሁዋላ ኤርትራ እንደፈለገች የጦር መሳርያ መግዛት ትችላለች።

ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት(AP)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና‼️

በአዲስ አበባ በመኪና አደጋ ሁለት ሰዎች ሞቱ። ዛሬ ጥቅምት 24/2011 ዓ/ም ከጠዋቱ 1:00 ገደማ ፈረንሳይ አንቆርጫ በተለምዶ #ጥንስስ ወንዝ ተብሎ በሚጠራው ቦታ አካባቢ ዳገት
እየወጣ እያለ ፒካፕ መኪና ግራቸውን ይዘው ወደ አታክልት ተራ ይሄዱ የነበሩ ሁለት የ28 አመት ወጣቶች #ህይወታቸው አለፈ፡፡ መኪናውም ከአስፓልቱ መቶ ሜትር እርቆ ገደሉ ውስጥ ገብቷል፡፡ የአሽከርካሪው ሹፌርም ለግዜው ተሰውሯል፡፡

ነብስ ይማር!!

ምንጭ፦ ዋልተንጉስ አብነህ
@tsegabwolde @tikavhethiopia
አባያ ሀይቅን እንታደግ‼️በአባያ ሀይቅ ላይ እየደረሰ ያለውን ጉዳት ለህዝብ ለማስገንዘብ እና ትኩረት እንዲሰጠው ለማድረግ የ3 ቀን የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ዛሬ ተጀምሯል።

"የእንቦጭ አረምን ከሃይቁ እናስወግድ"
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጀማል አስክሬን እንዲሟሟ ተደርጓል‼️

ጋዜጠኛ #ጀማል_ካሾጊ ከተገደለ በኋላ አስከሬኑ ተቆራርጦ #እንዲሟሟ ተደርጓል አሉ የፕሬዚዳንት #ኤርዶሃን ኣማካሪ።

የአሁኑ የአማካሪው መግለጫ “የጋዜጠኛው አስከሬን በአሲድ እንዲጠፋ ተደርጓል መባሉን ለማጣራት ምርመራ እየተካሄደ ነው” በማለት
አንድ ከፍተኛ የቱርክ ባለስልጣን ለዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ የሰጡትን መረጃ እውነትነት #ያረጋግጣል ተብሏል።

አማካሪው ያሲን አክታይ ቱርክ ውስጥ ለሚታተመው ሁርየት የተባለ ጋዜጣ እንደተናገሩት የካሾጊ አስከሬን ተቆራርጦ ብቻ ሳይሆን ሟሙቶ እንዲወገድ መደረጉን ነው ማወቅ የቻልነው ብለዋል።

እጃችን ላይ እንደደረሰው መረጃ ከሆነ ገዳዮቹ አስከሬኑን የቆራረጡት በቀላሉ ለማሟሟት እንዲመቻቸው ነው ብለዋል አማካሪው።

የቱርክ ዋና ዐቃቢ ህግ ባለፈው ረቡዕ ለመጀመሪያ ጊዜ በሰጡት መግለጫ ካሾጊ ኢስታንቡል ወደሚገኘው የሳዑዲ ቆንስላ እንደገባ በተደራጀ ሁኔታ #ግድያ ተፈጽሞበት አስከሬኑም ተቆራርጦ እንዲወገድ መደረጉን አረጋግጠዋል።

“አንድም የሰውነቱ አካል እንዳይገኝ አልመው ያደረጉት ነገር ነው። ንጹህ ሰው መግደል አንድ ወንጀል ሆኖ ሳለ አስከሬኑ እንዲጠፋ የተደረገበት መንገድ ደግሞ ሌላ አስከፊ ወንጀል ነው ብለዋል ያሲን አክታይ።

ምንጭ፦ ARTS TV WORLD
@tsegabwolde @tikvahethiopia