TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የዶክተር አብይ ጉዞ ወደ አውሮፓ‼️

ጠ/ሚ ዶ/ር #ዐብይ ዛሬ ማምሻውን ለመጀመሪያ የአውሮፓ ጉብኝታቸው ከሀገር ይወጣሉ። ከፈረንሳዩ ፕሬዚደንት ማክ ሮን ጋር ላላቸው የሰኞ ጠዋት ቀጠሮ ጥቂት ሰዓታት ሲቀራቸው አውሮፕላናቸው #ፓሪስ ያርፋል። ከሳቸው ጋር የውጭ ጉዳይ፣የገንዘብና የሳይንስና ኢኖቬሽን ሚኒስትሮች አብረው ይጓዛሉ።

ዶክተር አብይ ማክሰኞ ጀርመን ይገባሉ። በርካታ የአፍሪካ መሪዎች በሚሳተፉበት መድረክላይም ይካፈላሉ። ከዛ በኋላ ከ20ሺ የማያንሱ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ጋር ይገናኛሉ። ዝግጅቱ ፍራንክፈርት ከተማ ነው የሚደረገው።

©ከአለምነህ ዋሴ(መጠነኛ የቃላት ለውጥ የተደረገበት)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዶክተር አብይ ፓሪስ ገብተዋል‼️

ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ክቡር ፕሬዚዳንት ማክሮን ባደረጉላቸው ጥሪ መሰረት #ፓሪስ ፈረንሳይ ገቡ።

ሁለቱ መሪዎች በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በተለይ በአፍሪካ ቀንድ የጸጥታ ሁኔታ፣ በኢትዮጵያ በመካሄድ ላይ ስላለው ሪፎርም፣ በንግድ እና ኢንቨስትመንት ዙሪያ እንደሚመክሩ ይጠበቃል።

ምንጭ፦ አቶ ፍፁም አረጋ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"...ከኢትዮጵያ ጋር የመዋጋት ፍላጎት የለንም ፥ የጦርነት ሁኔታ የማይታሰብ ነው" - አብድል ፈታህ አል-ቡርሃን

ፈረንሳይ ለሱዳን የሽግግር መንግሥት ዓለም አቀፍ ድጋፍ ለማድረግ #ፓሪስ ላይ ጉባዔ አዘጋጅታ ነበር።

ጉባኤው ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ የአፍሪካ ሀገራት እና ዓለም አቀፍ ተቋማት የተሳተፉበት ነው።

በዚሁ ጉባኤ ላይ የሱዳን ሉዓላዊ ም/ቤት ሊቀመንበር አብድል ፈተህ አል-ቡርሃን ከኢትዮጵያ ጋር ላለን ግንኙነት እና ትስስር በህዳሴ ግድብ ላይ ስምምነት ላይ መድረስ ያስፈልጋል ሲሉ መናገራቸውን አል ዓይን አስነብቧል።

አል-ቡርሃን በሱዳን እና በኢትዮጵያ ድንበር ጉደይ "ከኢትዮጵያ ጋር የመዋጋት ፍላጎት የለንም ፥ የጦርነት ሁኔታ የማይታሰብ ነው" ሲሉም ተደምጠዋል።

በኢትዮጵያ በኩል በፓሪሱ ጉባኤ ላይ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የተገኙ ሲሆን ንግግርም አድርገወል።

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ባደረጉት ንግግር ፥ በኢትዮጵያ እና ሱዳን መካከል ስላለው ዘመናትን የተሻገረ እና በደም የተሳሰረ ወዳጅነት እና የሕዝቦች ትስስር አንስተዋል።

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን በተመለከተ ግድቡ የሚያመነጨው የኤሌክትሪክ ኃይል ኢትዮጵያ የዜጎቿን የኃይል ፍላጎት ከሟሟላት ባሻገር የቀጠናውን ሀገራትን ተጠቃሚ ሊያደርግ በሚችል መልኩ እየተገነባ ስለመሆኑ አስረድተዋል።

በሌላ በኩል ከሱዳን ጋር በድንበር ጉዳይ የተፈጠሩ አለመግባባቶች ሆነ ማንኛውም ሊፈጠሩ የሚችሉ አለመግባባቶች ሊፈቱ የሚገባው በውይይት እና በመርሕ ላይ ተመሥርቶ ሊሆን እንደሚገባው አፅዕኖት ሰጥተው ተናግረዋል።

በፓሪሱ ጉባኤ ፥ የግብፁ ፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ ኤል ሲሲ እና የሩዋንዳው ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ ንግግር አድርገዋል።

መረጃው የተሰባሰበው ከአል-ዓይን እና ኢቲቪ ነው።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT