TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ሀዋሳ⬇️

በሀዋሳ በተለምዶ አሮጌው ገበያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በደረሰው ድገተኛ የእሳት ቃጠሎ ንብረት የወደመባቸው ተጎጂዎችን መልሶ ለማቋቋሙ የሚደረገው የግንባታ ስራ ተጀመረ፡፡

እንደ አቶ #ፍቅሩ_ተስፋዬ የሀዋሳ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ አስተዳደሩ አደጋው ከተከሰተበት እለት ጀምሮ ከተጎጂዎች ጎን በመቆም የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን መግለፅን ጨምሮ መልሶ የማቋቋም ስራውን በተጠናከረ መልኩ ከዳር ለማድረስ ቃል በገባው መሰረት አራት ኮሚቴዎችን የያዘ ግብረሀይል በማዋቀር ወደ ስራ ተገብቷል ፡፡

እኚህም፦
1. በአደጋው ተጎጂዎችን የሚለይ፣
2. መልሶ ለማቋቋም ድጋፍ የሚያሰባስብ፣
3. የህዝብ ግንኙነት ስራዎች የሚያከናውን እና
4. የአደጋው መንስኤ እና ተባባሪ የሆኑ አካላትን በመለየት የህግ የበላይነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ተግባራን የሚያከናውኑ ኮሚቴዎች መሰየም እንደሆነ ነው ስራ አስኪያጁ በገለጻቸው ያከሉት፡፡

ከተዋቀረው ግብረ ሀይል በአደጋው ንብረት የወደመባቸው ተጎጂዎችን የመለየት ተልዕኮ የተሰጠው ኮሚቴ በአጭር ጊዜ ውስጥ በአካባቢው በተከሰተው ድገተኛ የእሳት ቃጠሎ

• 690 ሙሉ ለሙሉ የመሸጫ መደብ የወደመባቸው፣
• 124 በአደጋው ወቅት ዘረፋ የተፈጸመባቸው መሸጫ መደብሮች፣
• 64 ጥገና የሚፈልጉ መሸጫ ቤቶች፣
• 36 ተለጣፊ ሆነው በሌላው የመሸጫ መደብር ላይ በንግድ ተሰማርተው የሚገኙ እና
• 48 የሚሆኑት ደግሞ ክፍት የጉሊት መሸጫዎች ላይ የሚገኙ እንደሆኑ በልየታው ማረጋገጡን ስራ አስኪያጁ ተናግረዋል፡፡

እኚህ በልየታው ተጎጂ እንደሆኑ የታወቁ አካላትን አስተዳደሩ ቃል በገባው መሰረት በአፋጣኝ ወደ ቀድሞው ስራቸው እንዲገቡ ለማድረግም በስፍራው ደረጃውን የጠበቀ ግንባታን በ7 ቀናት ውስጥ በማከናወን ለማስከብ ጥረት እያደረገም ይገኛል ብለዋል አቶ ፍቅሩ፡፡

ለዚህም ማዘጋጃ ቤቱ ሁለት አይነት የግንባታ ዲዛይኖች በማዘጋጀት ስራውን ከወዲሁ ማከናወን መጀመሩን ያስረዱት አቶ ፍቅሩ ለአልባሳት እና ጨርቃጨርቅ ስራ ሙሉ ለሙሉ በብሎከት እና ላዩ በቆርቆሮ የተሸፈነ እንዲሁም ለአትክልት እና ፍራፍሬ መሸጫ መደብሮች የሚውል እንደ ተጎጂዎቹ ፍላጎት ላዩ በቆርቆሮ የተሸፈ እና ጎንና ጎኑ ክፍት የሆነ ሆኖ የቀረበ ነውም ብለዋል፡፡

በአጭር ጊዜ ውስጥ ማጠናቀቅ ስለመቻሉም ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ የሰጡት አቶ ፍቅሩ ግባታው በብሎኬት ጥንካሬ እንዲኖረውም በብረት በመታገዝ የሚከናወን መሆኑን እና ለግንባታው የተመረጡት ማህበራት ብቃት ያላቸው መሆናቸው በተባለው የጊዜ ገደብ ማስረከብ የሚያስችል እንደሚሆን በማስገንዘብ ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለም አስተዳደሩ በግንባታውም ሆነ ተጎጂዎችን መልሶ ለማቋቋም እያደረገ ያለውን ጥረት በሚዲያዎች የታገዘ የህዝብ ግንኙነት ስራን በማጠናከር በየጊዜው መረጃን ተደራሽ ከማድረግ አንጻር እንደሚሰራም ስራ አስኪያጁ አስረድተዋል፡፡

ምንጭ፦ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር
@tsegabwolde @tikvahethiopia