TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ወንጀል ነክ መረጃ‼️

የስራ ባልደረባውን #የገደለው የፖሊስ አባል #በጽኑ_እስራት ተቀጣ፡፡ በጋምቤላ ክልል ልዩ ቦታው ደንቦስኮ በተባለው አካባቢ ከምሽቱ 3፡00 በስናይፐር ጠመንጃ ተኩሶ የስራ ባልደረባውን የገደለው የፌዴራል ፖሊስ አባል የፌዴራል ዐቃቤ ሕግ በመሰረተው 3 ክስ በእስራት ተቀጣ፡፡

ተከሳሽ ወንጀል ህግ አንቀጽ 540 የተመለከተውን በመተላለፍ በ1ኛ እና በ2ኛ ክስ ተከሳሹ የፌዴራል ፖሊስ አባል ሲሆን ከሌሎች አስራ ሁለት አባላት ጋር ለግዳጂ ከአዲስ አበባ ወደ ኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ሙኒ ከተባለ ቦታ የፌዴራል ፖሊስ ካምፕ ለማደር ተገኝው ባሉበት ወቅት ሰው ለመግደል አስቦ በስናይፐር ጠመንጃ ተኩሶ ሁለት የስራ ባልደረቦችን አንደኛውን ሆዱ እና ሁለተኛውን ጭንቅላቱ ላይ በመምታት ደም ፈሷቸው ህይወታቸው እንዲያልፍ በማድረጉ እና በ3ኛ ክስ ከላይ በተገለጸው ቀንና ሰዓት በሌላ ሰው አካል ወይም ጤና ላይ ጉዳት ለማድረስ በማሰብ 3ኛውን የስራ ባልደረባውን ተኩሶ ግራ ታፋውን በመምታት እንዲቆስልና የህመም ስሜት እንዲሰማው በማድረጉ በፈጸመው አካል ጉዳት ማድረስ ወንጀል ተከሷል፡፡

ዐቃቤ ህግም የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን በማደራጀት ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል፡፡የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ ወንጀል ችሎትም ጥር 7 ቀን 2011 ዓ.ም በዋለው ችሎት በ19 ዓመት ከ6 ወር ጽኑ እስራት እንዲቀጣ በማለት ወስኗል፡፡

ምንጭ፦ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia