#update ፌደራል ፖሊስ⬇️
በአዲስ አበባ ከጸጥታ ችግር ጋር ተያይዞ በቁጥጥር ስር ውለው በጦላይ ስልጠና ሲከታተሉ የቆዩ ወጣቶች በያዝነው ሳምንት #እንደሚለቀቁ ተገለፀ።
ወጣቶቹ ከመስከረም 2 እስከ መስከረም 8 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ከነበረው የፀጥታ ችግር ጋር ተያይዞ ነበር በቁጥጥር ስር የዋሉት።
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ዘይኑ ጀማል ለFBC እንደተናገሩት፥ በመንግስት በኩል በቁጥጥር ስር ለዋሉት ወጣቶቹ እስካሁን የተለያዩ ስልጠናዎችን ሲወስዱ ቆይተዋል።
በጦላይ ለአንድ ወር እራስን ከወንጀል ስለማራቅ እና ተያያዠ ስልጠናዎችን ለመስጠት የተያዘው የጊዜ ሰሌዳም የፊታችን #ሀሙስ ይጠናቀቃል ብለዋል ኮሚሽነር ጀነራል ዘይኑ ጀማል።
አስፈላጊው ሎጀስቲክስ ሚሟላ ከሆነ ወጣቶቹ የፊታችን ሀሙስ ካልሆነ ደግሞ እስከ መጪው ቅዳሜ ድረስ የሚለቀቁ መሆኑን ገልጸዋል።
አቶ ዘይኑ ወጣቶችን አስተምሮ ከመልቀቅ ባለፈ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጋር በመነጋገር ስራ አጥ የሆኑትን በጥቃቅንና አነስተኛ አደራጅቶ ወደ ስራ ለማስገባት ዝግጅት መደረጉንም ተናግረዋል።
በከተማዋ በነበረው የጸጥታ ችግር በቁጥጥር ስር ውለው ስልጠና ሲከታተሉ የነበሩ 1 ሺ 204 ወጣቶች ሲሆኑ፥ ከነዚህ ውስጥ በወንጀል የተጠረጠሩት 83 ወጣቶች በህግ የሚጠየቁ ናቸው ብለዋል።
ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia

ተረጋግተን በጥንቃቄ ብናሽከረክር ምናለበት ?
" በአደጋው ከሞቱት ሦሥቱ የግብርና ባለሙያዎች የተቀሩት ነዋሪዎች ናቸው " - የስልጤ ዞን አስተዳደር
ትላንትና #ሀሙስ ጥዋት በስልጤ ዞን ሁልባራግ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ8 ወገኖቻችን ህይወት አልፏል።
አደጋው የደረሰው ከአዲስ አበባ ተሳፋሪዎችን ጭኖ ወደ አርባ ምንጭ ሲጓዝ የነበረ ሀገር አቋራጭ አውቶቢስ ከቢለዋንጃ ወደ ሁልባራግ ኬራቴ ተሳፋሪዎችን ይዞ ሲጓዝ ከነበረ ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪ/ባጃጅ በመጋጨቱ ነው።
የስልጤ ዞን አስተዳደር " በአደጋው ህይወታቸውን ካጡት ውስጥ ህዝብና መንግሥት የጣለባቸውን ኃላፊነት ለመወጣት ደፋ ቀና የሚሉ ሦስት የግብርና ባለሙያዎች አሉበት ሌሎች የአካባቢው ነዋሪዎች ናቸው " ብሏል።
የወረዳው ፖሊስ ጽህፈት ቤት ፥ በባጃጅ ሲጓዙ የነበሩ 8 ተሳፋሪዎች በሙሉ ህይወታቸው ማለፉን ገልጾ " አደጋው ዘግናኝ ነው " ብሎታል።
የሟቾቹ አስክሬን በመቆራረጡና በደም በመጨማለቁ ፊታቸውን በማጠብ ነው ማንነታቸውን መለየት የተቻለው።
ፖሊስ " ጉዳት አድራሹ አውቶብስ በከፍተኛ ፍጥነት ይሽከረከር እንደነበር መረጃዎች አሉ ነገር ግን ተጨማሪ የማጣራት ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ " ሲል ለዶቼ ቨለ ሬድዮ ገልጿል።
@tikvahethiopia