TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"አሰላ ከተማ ችግር ላይ ናት ነገሩ #ሳይባባስ መንግስት #አስቸኳይ መፍትሄ ይፈልግ።" #አሰላ #Asella

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ማዕከላዊ ኮሚቴ በዛሬው ዕለት #አስቸኳይ ስብሰባውን ያካሂዳል። ማዕከላዊ ኮሚቴው ወቅታዊ ጉዳዮችን ምክንያት በማድረግ ዛሬ አስቸኳይ ስብሰባ የሚያካሂድ መሆኑን ፅህፈት ቤቱ አስታውቋል። በአስቸኳይ ስበሰባውም በተለያዩ ሀገራዊና ክልላዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል።

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሕወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ #አስቸኳይ ስብሰባ ማድረግ ጀምሯል፡፡ #ደኢሕዴንም ስብሰባ እያካሄደ ነው፤/የደኢህዴን ስብሰባ ለ3 ቀናት ተብሎ ነበር የተጀመረው ስብሰባው ዛሬም #እንደቀጠለ ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert የህወሃት /T.P.L.F/ ማዕከላዊ ኮሚቴ ሲያደርግ የነበረውን #አስቸኳይ ስብሰባ ባለ 7 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል።

መግለጫው እንደደረሰን የሚቀርብ ይሆናል!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የደቡብ ክልል የ2012 በጀት አለመጽደቅ ውዝግብ አስነሳ!

የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ላለፉት ስምንት ወራት መሰብሰብ ባለመቻሉ የክልሉን በጀት ያላፀደቀ ሲሆን የ2011 በጀት ላይ በመመስረት የአንድ ወር በጀት ብቻ ታስቦ መለቀቁ የዋጋ ግሽበትን ያላማከለ እና የዞን አመራሮችን ጫና ውስጥ የከከተ ነው ተባለ።

‹‹የተለቀቀው አንድ አስራ ሁለተኛ በጀት ያለፈው አመት ቀመር ላይ በመመስረቱ መደበኛ ስራዎችን ለማከናወንም ሆነ ለአስቸኳይ ወጪዎች በቂ አይሆንም፡፡ በተጨማሪም ገንዘቡ የግብር ከፋዩ ገንዘብ እንደመሆኑ ይህንን መከልከል አግባብነት የለውም›› ሲሉ የወላይታ ብሄራዊ ንቅናቄ (ወብን) የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ተከተል ላቤና ገለፀዋል።

የክልሉ ፕሬስ ሴክሪታሪያት ኀላፊ ፍቅሬ አማን በበኩላቸው የመንግስት ሰራተኞችን ደመወዝ ለመክፈል፣ መደበኛ ስራዎችን ለማስኬድ እንዲሁም #አስቸኳይ ስራዎችን ለማከናወን ጊዜያዊ በጀቱ በቂ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ አክለውም ክልሉ የገቢ ግብር ማሰባሰብ ስራውን በማካሄድ ላይ መሆኑን ገልጸው የገንዘብ እጥረት አይኖርም ብለዋል፡፡

ምክር ቤቱ በየትኛውም አይነት ሁኔታ ተሰብስቦ መደበኛ ስራውን መስራት በአዋጅ የተሰጠው ተግባሩ ነው ያሉት የወብን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ይህንን ስራውን በተቀመጠለት ጊዜ ገደብ ማከናወን አለመቻሉም አግባብ አይደለም ሲሉ ይተቻሉ፡፡

#አዲስማለዳ

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ET-08-19-2
#አስቸኳይ

"ከእስታይሽ ወደ ወልዲያ በሚወስደው መንገድ አንድ መኪና መንገድ ስቶ ገደል ውስጥ ገብቶ አደገኛ አደጋ ደርሷል። የሚመለከተው አካል አውቆ አፋጣኝ እርዳታ እንዲያደርግ እንጠይቃለን። በአካባቢው አምቡላስ የለም!!" - በአካባቢው የሚገኙ የቲክቫህ ቤተሰቦች

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አስቸኳይ

ክፍት የስራ ማስታወቂያ ለህክምና ባለሙያዎች!

የጅማ ዩኒቨርሲቲ ጤና ኢኒስቲትዩት ለኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ወረርሽኝ ቁጥጥርና ህክምና ስራ ተጨማሪ የህክምና ባለሙያዎችን በአፋጣኝ አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል፡፡ ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ ባለሙያዎች መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

• የመመዝገቢያ ቀናት ፦ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጀምሮ 5 የስራ ቀናት

• የመመዝገቢያ ቦታ፦ የሆስፒታሉ የሰዉ ሃብት ቢሮ ቁጥር 124

ከጅማ ዩኒቨርሲቲ!
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#አስቸኳይ_መልዕክት !

በሓፀቦ አከባቢ የአንበጣ መንጋ እየታየ ስለሆን በሰብል ላይ ጉዳት እንዳያደርስ ቦታው በመገኘት የአርሶ አደሩ የመከላከል ስራ እንድትቀላቀሉ ተጠይቋል - (AXUM UNIVERSITY)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#አስቸኳይ

የጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ጤና ፅ/ቤት በላከልን ደብዳቤ ከጥቅምት 13 እስከ ጥቅምት 20 ደረስ በወልቂጤ ከተማ ሁሉም ክ/ከተማዎች ፣ ቀበሌዎችና አጎራባች ቀበሌዎች የቢጫ ወባ መከላከያ ክትባት /Yellow fever Vaccine/ እድሜያቸው ከ6 ወር እስከ 60 ዓመት የሆናቸው የህብረተሰብ ክፍሎች በሙሉ እየተሰጠ እንደሚገኝ ገልጾልናል።

ስለሆነም ከላይ እድሜያቸው የተጠቀሰ የህብረተሰብ ክፍሎች በሙሉ በአስቸኳይ ክትባቱን እንዲያገኙ መልዕክት ተላልፏል።

@tikvahethiopiaBOT
#NewsAlert

ነገ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት #አስቸኳይ_ጉባኤ እንደሚካሄድ ተገለጸ።

የክልሉ ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ አለምነሽ ይባስ እንዳሉት ምክር ቤቱ በነገው ዕለት በአሶሳ ከተማ አስቸኳይ ጉባኤውን ያካሂዳል።

በጉባኤው የመተከል ዞን የሠላም እና ጸጥታ ችግር ዋነኛው የምክር ቤቱ ትኩረት እንደሚሆን ምክትል አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ አለምነሽ አስታውቀዋል፡፡

ሌሎችም ክልላዊ እና ሃገራዊ ወቅታዊ ጉዳዮችን የውይይቱ አጃንዳ አድርጎ ይወያያል ብለዋል። (ENA)

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia