TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ጠ/ሚ ጁሴፔ⬆️

ጠቅላይ ሚኒስትር #ጁሴፔ_ኮንቴ መኪና በመገጣጠም የሚታወቀውን የአምቼ ኩባንያን ጎብኝተዋል።

ኩባንያው 70 በመቶ በጣሊያን መንግስት 30 በመቶ ደግሞ በኢትዮጵያ መንግስት ድርሻነት የተቋቋመ ነው፡፡

የጣሊያኑ ጠ/ሚኒስትር የኢትዮጵያ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ወደ #ኤርትራ አቅንተዋል፡፡

ጠ/ሚኒስትር ጁሴፔ ኮንቴ በጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድና በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየው በቦሌ አየር ማረፊያ ሽኝት ተደርጎላቸዋል፡፡

ፎቶ፦ ጠቅላይሚንስትር ፅ/ቤት
ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ምክትል ጠ/ሚ ደመቀ⬇️

በ2011 ዓመት የትምህርት ዘመን በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት ለማስፈን የተቀናጀ ጥረት መደረግ እንድሚያስፈልግ  ምክትል  ጠቅላይ ሚኒስትር  አቶ #ደመቀ_መኮንን ገለፁ።

በዛሬው ዕለት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት #ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው።

የዘንድሮውን  የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመማር ማስተማር ሂደት ሰላማዊ እና የተረጋጋ ለማድረግ ሁሉም ተዋናይ የበኩላቸውን ሊወጡ እንደሚገባ  ነው ምክትል  ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያስታወቁት።

ከተለያዩ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና ከማህበረሰብ የተውጣጡ 1500 ተሳታፊዎች በጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት በሚካሄደው የውይይት መድረክ ላይ ታድመዋል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አጋሮ ከተማ የሚገኙ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ከጥዋት ጀምሮ ከተማይቱ ውስጥ ውጥረት መኖሩን እየገለፁ ናቸው። ከሰሞኑ የከተማው ነዋሪ በአስተዳደሩ ላይ ያለውን ቅሬታ ሲያሰማ እንደነበር ጠቅሰዋል።

ዝርዝር መረጃ አደራጅቼ አቀርባለሁ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ትኩረት ለአጋሮ‼️

በአጋሮ ያለውን ሁኔታ የኦሮሚያ ክልል መንግስት ትኩረት እዲሰጠው ነዋሪዎች እየጠየቁ ናቸው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የአሠልጣኝ ስዩም አባተ የቀብር ስነ-ስርዓት በዛሬው ዕለት ከቀኑ 9:00 ሰዓት ሳሪስ በሚገኘው የፃድቁ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ (ሳሪስ አቦ) ቤተክርስቲያን ይፈፀማል።

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከጥቁር አንበሳ ተማሪዎች⬆️

"በጥቁር አንበሳ የ4ኛ(C-1) ዓመት ህክምና ተማሪዎች በተቋቋመው Care Charity እና የተማሪ ተወካዮች አስተባባሪነት 13,330 ብር ተሰብስቦ ለእህታችን ተማሪ ማሪያም ተስፋዬ በተከፈተው የሂሳብ ደብተር ቁጥር አስገብተናል። እህታችንን ፈጣሪ ሙሉ በሙሉ ድና ወደ ትምህርቷ ተመልሳና ወገኖቿን በሞያዋ ስትረዳ ለማየት እንዲያበቃን እንመኛለን። #Care_Charity_Black_Lion"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀዋሳ⬆️የሀዋሳ ከተማ ወጣቶች እና የቅርብ ጓደኞቿ ለማርያም ተስፋዬ ያሰባሰቡትን 31,822 ብር ገቢ አድርገዋል።

ወጣቶቻችን እድሜውን ከጤና ጋር አብዝቶ ይስጣችሁ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የታዳጊዋ የህክምና ተማሪ ማርያም ተስፋዬ የህክምና ወጪን በተመከት ያለውን አጠቃላይ ገንዘብ በደቂቃ ውስጥ አሳውቃላሁ።

ባለኝ መረጃ ሙሉ የህክምና ወጪዋን የሚሸፍን ገንዘብ ተገኝቷል!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዶክተር አብይ ዛሬ የሰሩት ስራ⬆️

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ለአንድ ቀን የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ የነበሩትን የጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጁሴፔ ኮንቴ በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ከሸኙ በኋላ የብሔራዊ የክብር ዘብ አባል የደንብ ልብስ #ሲያስተካክሉ ታይተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሌሎች የአገሪቱ ላመሥልጣኖች ጋር ሆነው ወደ መኪናቸው እየተመለሱ ሳለ በድንገት ከቀይ ምንጣፍ ወጥተው የአንድ የክብር ዘበኛ አባል የደንብ ልብስ አለባበስን ሲያስተካክሉ አብረዋቸው የነበሩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁን (ዶ/ር) ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች #ሲደመሙ ተስተውለዋል፡፡

ምንጭ፦ ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ከትናንት በስቲያ ቤተ መንግስት በመሄድ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጥያቄ ያቀረቡ የመከላከያ ሰራዊት አባላት #ይቅርታ ጠየቁ።

የሰራዊት አባላቱ ጥያቄውን ያቀረቡበት መንገድ ህግና ስርዓትን ያልተከተለ በመሆኑ መንግስትና ህዝብን ይቅርታ ጠይቀዋል።

አባላቱ ባለፉት ሁለት ቀናት ከኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር አቶ ሞቱማ መቃሳ እና ከኢፌዴሪ ጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጀኔራል ሰአረ መኮንን ጋር ተወያይተዋል።

በዚህ ወቅት ጥያቄያቸውን ለበላይ አካል መቅረብ ሲገባቸው ቤተ መንግስት ድረስ በመሄድ ማቅረባቸው ህግን ያልተከተለ መሆኑን ገልጸዋል።

ምንጭ፦ ፋና
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የቴዎድሮስ ካሳሁን የሙዚቃ ኮንሳርት ጥቅምት 24 በሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ማሳሰብያ‼️

የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የከፍተኛ ትምህርት ምደባ ካካሄደ በኋላ ቅይይር የማይሰራ መሆኑ እያታወቀ ከዩንቨርሲቲ ዩንቨርሲቲ ቅይይር ማድረግ ለምትፈልጉ ተማሪዎች ዝውውር ማድረግ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን የሚል ሀሰተኛ መረጃ የኤጀንሲውን የፌስ ቡክ ገጽ አስመስለው በመክፈት እየለቀቁ ይገኛሉ፡፡ በመሆኑም ኤጀንሲው ማንኛውንም ዓይነት ከዩኒቨርስቲ ዩኒቨርስቲ የማዘዋወር ስራ የማይሠራ መሆኑን እየገለጽን ተማሪዎችና የተማሪ ወላጆች ከሐሰተኛ መረጃዎች እራሳችሁን እንድትጠብቁ መልዕክት እናስተላልፋለን፡፡

ምንጭ፦ የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተዎች ኤጀንሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update በአጋሮ ከተማ እስካሁን የአንድ ሰው ህይወት እንዳለፈ የከተማው ነዋሪዎች ገልፀውልኛል። ከተማይቱ ውስጥ እንቅስቃሴ የለም። መንግስት ችግሩን እንዲፈታና ውጥረቱን እንዲያረግብ ነዋሪዎች ጠይቀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia