TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Election2012

የኢዜማ የአዲስ አበባ ምርጫ ወረዳ 11 ከአባላት፣ ደጋፊዎች እና የአካባቢው ነዋሪ ጋር የሚያደርገው ውይይት በስብሰባዎች ማዕከል እየተካሄደ ይገኛል።

ስብሰባውን በአካባቢው በሚኖሩ የሀገር ሽማሀግሌዎች ምርቃት የተጀመረ ሲሆን የምርጫ ወረዳው ሥራ አስፈጻሚ እስካሁን የተከናወኑ ሥራዎችን እና እቅዶቻቸውን ለተሰብሳቢው አሳውቀዋል።

የኢዜማ ሊቀመንበር የሺዋስ አሰፋ፣ ምክትል መሪው አንዱዓለም አራጌ እና የምርጫ ስትራቴጂ እና ማኔጅመንት ካውንስል አባል አማንይኹን ረዳ በስብሰባው ላይ ተገኝተው የፓርቲውን ሀገራዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ማብራሪያ ይሰጣሉ።

#EZEMA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#EZEMA

ብልጽግና ፓርቲ የህዝብና የመንግስት ሃብትን ለምርጫ ቅስቀሳ እየተጠቀመ መሆኑን የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ኢዜማ አስታወቀ። የፓርቲው መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በወቅታዊ እና ሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ በአዲስ አበባ መግለጫ በመስጠት ላይ ናቸው።

ፕሮፌሰር ብርሃኑ በዚህ ጊዜ እንደተናገሩት ብልጽግና ፓርቲ የህዝብን እና የመንግስትን ገንዘብ ለምርጫ ቅስቀሳ እያዋለ ነው ብለዋል።

በመሆኑም የብልጽግና ፓርቲ ድርጊት ሌሎች ፓርቲዎችን ወደ አላስፈላጊ መንገድ የሚመራ ከማድረጉ በተጨማሪ የአገሪቱን የዲሞክራሲ ግንባታ ስለሚጎዳ ከዚህ ድርጊቱ እንዲታቀብ አሳስቧል። ምርጫ ቦርድም ይሄንን ህገወጥ እንቅስቃሴ እንዲያስቆም ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ጠይቀዋል።

#ኢትዮኤፍኤም107.8 #ሔኖክአስራት
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ሒሩት ክፍሌ በዋስ እንዲለቀቁ ተወሰነ!

በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) የብሔራዊ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የሙያ ማኅበራት ተጠሪ ሒሩት ክፍሌ ለ3ተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀርበው የነበር፡፡

ፖሊስ የምርመራ ስራውን እንዳልጨረሰ በመግለፅ ተጨማሪ ጊዜ እንዲሰጠው የጠየቀ ሲሆን የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የቀጠሮ መዝገቡን ዘግቶ በ6,000 ብር ዋስትና ከእስር እንዲፈቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል - #EZEMA

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#EZEMA

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) ዛሬ ነሐሴ 22/2012 ዓ/ም በአዲስ አበባ ከተማ የሚካሔዱ የመሬት ወረራዎችን እና ኢ-ፍትሀዊ የሆነ የመኖሪያ ቤቶችን ክፍፍል በሚመለከት በራስ ሆቴል ሊሰጥ የነበረው መግለጫ በፖሊስ መበተኑን አዲስ ማለዳ ጋዜጣ ዘግቧል።

የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት ናትናኤል ፈለቀ እንደተናገሩት ከቀናት በፊት ስለስብሰባው ለሰላም ሚኒስቴር ከዚህ ቀደም እንደሚደረገው ሁሉ በደብዳቤ ያሳወቁ ቢሆንም ዛሬ ነሐሴ 22/2012 በራስ ሆቴል ሊሰጥ ነበረው መግለጫ ግን የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ስለ መግለጫው መረጃ የለኝም በሚል መግለጫው እንዳይካሔድ መከልከሉ ታውቋል።

Via Addis Maleda
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#EZEMA

ግንቦት 28 እና ሰኔ 5 የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)ን ወክለው ለሕዝብ ተወካዮች እና ለክልል ምክር ቤቶች የሚወዳደሩ ዕጩዎች ከዛሬ ጥር 1 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ መታወቅ እንደሚጀምሩ ፓርቲው በፌስቡክ ገፁ አሳውቋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
የኢዜማ አባላቶቼ ተደበደቡብኝና ታሰሩብኝ ክስ የመንግስት ምላሽ ፦

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ ከአስራ አንድ በላይ የሚሆኑ የፓርቲው አባላት በደቡብ ክልል ኮንሶ ዞን የምርጫ ቅስቀሳ በማድረግ ላይ እያሉ ድብደባ እንደተፈፀመባቸውና ለቀናት መታሰራቸው በኃላም ከእስር መፈታታቸውንአስታውቋል።

ኢዜማ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ናትናኤል ፈለቀ፥ "ባለን መረጃ የካቲት 4 የመንግስት የድጋፍ ሰልፍ ይደረግ ነበር በኃላም ይህ ሰልፍ ተሰርዞ ምርጫ ቅስቀሳ እንዲደረግ በተያዘለት ጊዜ ሲደረግ ኢዜማ የምርጫ ቅስቀሳ ከማድረግ ተቆጥቦ ሰልፉ ከተካሄደ በኃላ ነው ወደ ቅስቀሳ የገቡት ከዚህ በኃላ ነው እስርና ድብደባው በአባላቶቻችን ላይ የደረሰው" ብለዋል።

የፓርቲው አባላት ሲታሰሩ የኢዜማን አርማ መያዛቸውን፣ የፓርቲውን የምርጫ ምልክት ያለበት ቲሸርትም ለብሰው እንደነበር በኮንሶ ዞን የኢዜማ ምክትል ሊቀመንበር ገልፀዋል።

ምክትል ሊቀመንበሩ ፥ የአካባቢው ፀጥታ አካላት የኢዜማን ቲሸርት የለበሱ አካላትን እየቀጠቀጡ እና እየደበደቡ ነበር ብለዋል ፤ አንደኛው የኢዜማን ቲሸርት የለበሰ ሃኪምም በሳንጃ ሁሉ ተወግቷል ሲሉ ገልፀዋል።

መንግስት በኢዜማ አባላት ላይ በማህበራዊ ኑሮ ላይ ሳይቀር ከፍተኛ ጫና እያዳደረ መሆኑንም አብራርተዋል። ሁኔታው አሳሳቢ መሆኑ አሳውቀዋል።

"እነሱ በየአዳራሹ ቅስቀሳ ያደርጋሉ ፣ ቀበሌዎች ላይም በመንግስት ሃብት (ሞተር እና መኪና) እንደልባቸው እየተንቀሳቀሱ ቅስቀሳ ያደርጋሉ እኛ ግን በራሳችን ፅ/ቤታችን እንኳን እንዳንሰበሰብ ሊያደርጉን ነው" ብለዋል።

የታሰሩት የኢዜማ አባላት ማክሰኞ እለት ተፈተዋል።

የኮንሶ ዞን የሰላም እና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ሃሰን ወላሎ ፥ በኢዜማ ምርጫ ቅስቀሳ ምክንያት የታሰረ ሰው የለም ብለዋል። ነገር ግን መንግስት ፈርሷል እያሉ ኢ-ህገመንግስታዊ የሆነ ሰንደቅ ዓላማ በመያዝ በአደባባይ ሲያውጁ/ሁከትና ብጥብጥ ለመቀስቀስ ሲጥሩ የነበሩ ግለሰቦች እንደነበሩ ገልፀዋል።

#EthiopiaElection2013

https://telegra.ph/EZEMA-02-25
#EZEMA #FreedomandEqualityParty

በኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) አዘጋጅቶታል የተባለውና “የሃገሪቷ ወቅታዊ የደህንነት ስጋት ትንተና” የሚል ርእስ ያለው ሰነድ ከትላንት ጀምሮ በተለያዩ የማህበራዊ የትስስር ገጾች እየተዘዋወረ ነው።

በዚሁ ሰነድ መነሻነትም ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በማህበራዊ ትስስር ገጹ የፓርቲው ስም አሉታዊ በሆነ መንገድ በመጠቀሱ ማብራሪያ እንዲሰጠው በደብዳቤ ጠይቋል።

በጉዳዩ ላይ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) ህዝብ ግንኙነት ከደቂቃዎች በፊት መግለጫ አውጥቷል። በዚህም ከትላንት ጀምሮ ሲዘዋወር የነበረውን ሰነድ'' ኢዜማን የማያወክል እና ኢዜማ የማያዉቀዉ'' ነው ሲል ምላሽ ሰጥቷል።

ፓርቲው ፥ ''...በወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ ያለውን አረዳድ እና የወደፊት ተስፋ በመፅሀፍት አሳትሞ እና ህዝብ እንዲያዉቅ አድርጎ የሚንቀሳቀስ ፓርቲ ነው ...ለዚህም መፅሃፊት ፩ እና ፪፣ የፓርቲውን ፕሮግራም፣ የዜጎች መድረክ እትሞች እንዲሁም ምርጫ 2013 የቃልኪዳን ሰነድ ማየት ይቻላል'' ሲል ገልጿል።

@tikvahethmagazine @tikvahethiopia
#EZEMA : በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ጠቅላላ ጉባዔ የመጀመሪያ አስቸኳይ ስብሰባ እያካሄደ ይገኛል።

ጉባዔው በዛሬ ውሎው ፦

1. የፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ ላይ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማሻሻያ የተጠየቀባቸው አንቀፆች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ያሳልፋል።

2. በፓርቲው ፕሮግራም ላይ የቀረቡ የማሻሻያ ሀሳቦች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ያሳልፋል።

3. ከግጭት ቀጠና የመጡ የጉባዔ አባላት በአካባቢያቸው ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ለጉባዔ ተሣታፊዎች ግንዝቤ እንዲረዳ ያቀርባሉ።

ጉባዔው ነገ እሑድ መስከረም 23 ቀን 2014 ዓ·ም ተጨማሪ ውሳኔዎችን አሳልፎ እንደሚጠናቀቅ ፓርቲው በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፁ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#EZEMA : በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ጠቅላላ ጉባዔ የመጀመሪያ አስቸኳይ ስብሰባ እያካሄደ ይገኛል። ጉባዔው በዛሬ ውሎው ፦ 1. የፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ ላይ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማሻሻያ የተጠየቀባቸው አንቀፆች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ያሳልፋል። 2. በፓርቲው ፕሮግራም ላይ የቀረቡ የማሻሻያ ሀሳቦች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ያሳልፋል። 3. ከግጭት ቀጠና የመጡ…
#EZEMA : የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ጠቅላላ ጉባዔ የመጀመሪያ አስቸኳይ ስብሰባ ዛሬም ቀጥሎ እያካሄደ ይገኛል።

በዛሬው መርሃ ግብር ጉባኤው በፓርቲው መሪ [ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ] ሪፖርት እና ምክረ ሀሳብ ቀርቦለት ካዳመጠ በኋላ ከብልፅግና ፓርቲ የቀረበው «የአብረን እንሥራ» ጥያቄ ላይ ውይይት እያደረገ እንደሚገኝ ተገልጿል።

ውይይቱን ተከትሎ ፓርቲው የሚወስነው ውሳኔ እየተጠበቀ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#EZEMA : የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ጠቅላላ ጉባዔ የመጀመሪያ አስቸኳይ ስብሰባ ዛሬም ቀጥሎ እያካሄደ ይገኛል። በዛሬው መርሃ ግብር ጉባኤው በፓርቲው መሪ [ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ] ሪፖርት እና ምክረ ሀሳብ ቀርቦለት ካዳመጠ በኋላ ከብልፅግና ፓርቲ የቀረበው «የአብረን እንሥራ» ጥያቄ ላይ ውይይት እያደረገ እንደሚገኝ ተገልጿል። ውይይቱን ተከትሎ ፓርቲው የሚወስነው ውሳኔ እየተጠበቀ…
#EZEMA : ኢዜማ ከገዢው ፓርቲ ብልፅግና የቀረበለትን "የአብረን እንስራ" ጥያቄ ተቀብሏል።

ጉባዔው ውይይት ካደረገ በኃላ አሁን ሀገሪቱ ካለችበት ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር ጥያቄውን ተቀብሎ አብሮ ለመስራት በ536 ድጋፍ፣ 79 ተቃውሞ እና 25 ድምጸ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምጽ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ጠቅላላ ጉባዔ የመጀመሪያ አስቸኳይ ስብሰባ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል። መግለጫው ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia