TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ባህር ዳር⬆️

በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ የአማራ ክልል ተማሪዎችን ምሁራን #ሸለሙ፡፡

ዛሬ በባህር ዳር ከተማ በነበረው የሽልማት ስነ ስርዓት ላይ ተማሪዎቹ የበለጠ #ውጤታማ እንዲሆኑ ምሁራኑ አበረታተዋል፡፡

ከምሁራኑ መካከል ፕሮፌሰር #ዳንኤል_ቅጣው ባስተላለፉት መልዕክት ተማሪዎች ለሚቀጥለው ትውልድ መንገድ ማሳየትን፣ ቅን መሆንን፣ ለነገሮች ትኩረት መስጠትን እና በቀጣይም ፈተና እንደሚኖር ሊገነዘቡ እንደሚገባ መክረዋል፡፡

ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ በሚቀላቀሉበት ወቅትም የጊዜ አጠቃቀምን፣ ደጋግሞ መሞከርን እና #የንባብ ባህልን ማዳበር እንዳለባችው
መክረዋል።

©AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia