TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#አማዞን

የብራዚል ፕሬዚዳንት ጄይል ቦልሶናሮ የሀገሪቱ ጦር በአማዞን ደን ላይ የተከሰተውን የእሳት አደጋ የመከላከሉን ስራ እንዲቀላቀል ትእዛዝ ማስተላለፋቸው ተነገረ።

ፕሬዚዳንቱ ያስተላለፉት ትእዛዝም የሀገሪቱ ጦር በአፋጣኝ ወደ ስፍራው በመጓዝ ደኑን ከጥፋት ለማዳን የሚደረገውን ርብርብ ለማፋጠን አንደሚረዳም ነው የተነገረው።
ፕሬዚዳንት ጄይል ቦልሶናሮ ትእዛዙን ያሳለፉት የአውሮፓ ሀገራት መሪዎች ጫና ማሳረፋቸውን ተከትሎ እንደሆነም ነው የተገለፀው።

የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን እና የጀርመን መራሄተ መንግስት አንጌላ ሜርክል በአማዞን ጥቅጥቅ ደን ላይ ለተነሳው ሰደድ እሳት አስቸኳይ መፍትሄ እንደሚያስፈልገው መግለጻቸው ይታወሳል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በብራዚል በተለይም በአማዞን ክልል የሚነሳው የእሳት አደጋ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን መረጃዎች ያመላክታሉ።

በደኑ ከቀናት በፊት የተነሳውን እሳት ለመቆጣጠር ጥረት ቢደረግም አድማሱን እያሰፋ ከፍ ያለ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል። የምድራችን ሳንባ በመባል የሚታወቀውና የዓለማችን ትልቁ ደን አማዞን የአየር ንብረት ሚዛንን ለመጠበቅ ይረዳል።

ምንጭ፦ www.bbc.com / #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አማዞን

ብራዚል በአማዞን የተከሰተውን ሰደድ እሳት ለመቆጣጠር ከቡድን 7 ሀገራት የተደረጋለትን የ22 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ውድቅ ልታደርግ መሆኑ ተሰምቷል።

የቡድን ሰባት ሀገራት መሪዎች በፈረንሳይ እያደረጉት ባለው ስብሰባ በአማዞን የተከሰተውን ሰደድ እሳት ለመቆጣጠር የ22 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ለማድረግ መስማማታቸውን የፈረንሳዩ ፕሬዘዳንት ኢማኑኤል ማክሮን መግለፃቸው ይታወሳል። በአንፃሩ የብራዚል ባለስልጣናት የእሳት አደጋውን ለመቆጣጠር ከቡድን 7 ሀገራት የተደረገላቸውን የ22 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ መቃወማቸው ነው የተገለጸው።

ይሁን እንጂ በለስልጣናቱ ድጋፉን የተቃወሙበትን ምክንያት ከመግለጽ ተቆጥበዋል ነው የተባለው። በሌላ በኩል የብራዚል ፕሬዚዳንት ቦልሶናሮ ጉዳዩን አስመልክተው በሰጡት አስታያየት፥ ፈረንሳይ ብራዚልን እንደ ቅኝ ግዛት የምታይበትን መንገድ ኮንነዋል።

የብራዚል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፈርናንዶ አዝቬዶ ኢ ሲልቫ በበኩላቸው ፥ በአማዞን ደን ላይ የተከሰተው ሰደድ እሳት ከሀገሪቱ ቁጥጥር ውጭ አለመሆኑን ተናግረዋል። በደኑ ላይ የተከሰተውን ሰደድ እሳት ለመቆጣጠርና በአካባቢው የሚሰሩ ወንጀሎችን ለመከላከልም 44 ሺህ በላይ ወታደሮች በቦታው መሰማራታቸውን አንስተዋል።

ሀገራቱ ድጋፍ ለማድረግ #መስማማታቸውን ያመሰገኑት ሚኒስትሩ፥ ድጋፉን በአውሮፓ የሚገኙ ደኖችን መልሶ #ለማልማት ያውሉት ዘንድ አሳስበዋል። ሚኒስትሩ አክለውም ብራዚል ማንኛውንም ሀገር ደኖችን እንዴት መንከባከብ፣ መጠበቅ እንዲሁም ከጉዳት መካላከል እንደሚቻል የማስተማር አቅም ያላት መሆኑን አስገንዝበዋል።

Via fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia