TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በማይናማር እየተካሄደ ባለው በሚስ ግራንድ ኢንተርናሽናል አለም አቀፍ የቁንጅና ውድድር ላይ ሀገራችንን #ኢትዮጵያን ወክላ እየተወዳደረች ላለችው #ሳምራዊት_አዝመራው ከታች ባለው ዌብሳይት ላይ በሶስት ዘርፍ ኢትዬጵያን በመምረጥ ድምፅ ይስጡ።

Www.missgrandinternationalvote.com

ምንጭ፦ ኢዮሲያስ ምትኩ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ከማህበራዊ ህይወታቸው ሳይርቁ የቤት ባለቤት እንዲሆኑ የሚያስችል የመኖሪያ አፓርታማዎች ግንባታ እቅድ እየተዘጋጀ መሆኑ ተገለፀ።

የከተማዋ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር #ታከለ_ኡማ ‘‘በነቃ የወጣቶች ተሳትፎ ያጋጠሙንን ፈተናዎች በማለፍ ዕድገታችንን እናስቀጥላለን’’ በሚል መሪ ቃል ዛሬ ከኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወጣቶች ጋር ውይይት አካሂደዋል።

በዚህ ወቅት እንደገለጹት የከተማዋን ነዋሪ ከማህበራዊ ህይወቱ ሳይርቅ የቤት ባለቤት ማድረግ የሚያስችል የቤት ልማት እቅድ በሁሉም ክፍለ ከተሞች በቅርቡ ስራ ይጀምራል።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አምስተኛው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የህዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን ነገ ፕሬዝዳንት ዶ/ር #ሙላቱ_ተሾመ በሚያደርጉት ንግግር በይፋ እንደሚጀምር የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታውቋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Update ጋምቤላ⬆️

በጋምቤላ ከተማ ተከስቶ የነበረውን ሁከት #ለማረጋጋት በሚደረገው ጥረት የድርሻቸውን እንደሚያበረክቱ የከተማዋ ወጣቶች ተናግረዋል። በከተማይቱ ህዝባዊ ሰልፍ ተደርጓል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
*ከዚህ በላይ አሳሳቢ ጉዳይ የለም*

(ሼር ይደረግ)

ጫካ ያደሩ ህፃናትና እናቶች አረጋውያንና ደካሞች ከምንም በላይ "የኢትዮጵያዊያን ያለህ!" እያሉ ነው።

ነገ ሰኞና ማክሰኞ መስከረም 28-29
በሀገር ፍቅር ቴአትር ከጠዋቱ 3:00 እስከ ምሽቱ 11:30 የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በመቂስ ወጥተው ከቤኒሻንጉል የተፈናቀሉ ከ90 ሺህ በላይ ወገኖቻችንን ለመርዳት ወደ #ሀገር_ፍቅር_ቴአትር ያመራሉ ተብሎ ይጠበቃል። እርስዎም የበኩልዎን ድጋፍ እንዲያደርጉ ሙሉ ቀን ቆመን እንጠብቅዎታለን።

ለማስታወስ ያህል፦

#የማይበላሹ_ምግቦች
መኮረኒ
ሩዝ
ፉርኖ ዱቄት
ዘይት
ሴሪፋም /ፋፋ/
ብስኩት /ጋቤጣ/

#የንጽህና_ቁሳቁሶች
ሳሙና
ኦሞ
ሳኒታይዘር
የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ /ሞዴስ/

#አልባሳት
ብርድ ልብስ
ነጠላ ጫማ
የተለያዩ አልባሳት (ያገለገሉም ቢሆን)
ለበለጠ መረጃ መሐመድ ካሳ ወይንም ያሬድ ሹመቴን በሚከተለው ስልክ ማግኘት ይችላሉ 0930 36 52 44

#ቅድሚያ_ለሰብዓዊነት !!

(ከአንድ ግዜ በላይ ሼር እንዲያደርጉ እንማፀናለን)

ከያሬድ ሹመቴ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ⬇️

"ሠላም ጸግሽ! በአዲሱ ፍኖተ ካርታ ዙሪያ የሚደረገዉ ዉይይት በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ከአካዳሚክ ስታፎችና ከአስተዳደር ሰራተኞች ጋር ዛሬ ጥዋት በተማሪዎች መመገቢያ አዳራሽ በይፋ ተጀምሯል። ዉይይቱም ለ3 ተከታታይ ቀናት የሚደረግ ይሆናል ተብለናል፡፡"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወራቤ ዩኒቨርሲቲ⬆️ለአዲሱ ትምህርት እና ስልጠና ፍኖተ ካርታ ዝግጅት የግብዓት ማሰባሰቢያ የውይይት መድረክ መካሄድ ጀምሯል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጨፌ ኦሮሚያ⬇️

ጨፌ ኦሮሚያ 3ኛ አስቸኳይ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመሯል። ስብሰባው የክልሉን አስፈጻሚ አካላት መልሶ ለማደራጀትና ስልጣንና ሃላፊነታቸውን ለመወሰን የወጣው ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ለማጽደቅ ነው ተብሏል።

ረቂቅ አዋጁ ችግር የሚስተዋልበትን የአስፈጻሚ አካላት አደረጃጀት፣ የሰው ሃይልና በጀት አጠቃቀም ላይ የሚስተዋለውን ሰፊ ክፍተት ይቀርፋል ተብሎ ይጠበቃል።

ከዚህ ባለፈም በቢሮ ደረጃ ተከማችተው የሚገኙ የአስፈጻሚ አካላት አደረጃጀቶች ታች ካለው ማህበረሰብ ጋር ቀርበው እንዲያገለግሉ ከማድረግ አኳያ ትልቅ ሚና ይኖረዋልም ነው የተባለው።

ጨፌው ከዚህ ባለፈም የክልሉን ጠቅላይ አቃቤ ህግ ለማቋቋም የወጣው ረቂቅ አዋጅ ላይ በመወያየት ያጸድቃል ተብሎም ይጠበቃል።

በተጨማሪም በቁጥር 61/1994 የወጣውን የሰራተኞች አዋጅ ለማሻሻል በወጣው ረቂቅ ላይ ተወያይቶ ማፅደቅም በጨፌው ስብሰባ ከመሚጠበቁት ውስጥ ነው።

©fbc

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለትምህርት ሚኒስቴር‼️የተማሪዎች መግቢያ በፍኖተ ካርታ ውይይት ምክንያት በድጋሜ መራዘሙ ተገልጿል። ይህ ነገር የተሰማው ከቀናት በፊት ነው። በተለይ በጥቅምት ወር የመጀመሪያዎቹ ቀናት ወደ ተቋማቸው የተጠሩት ተማሪዎች የአውሮፕላን እና የባስ ትኬት ቆርጠው ሲጠባበቁ ነበር። ይባስ ብሎም ከሩቅ አካባቢ ወደተቋማቸው ጉዞ የጀመሩም አሉ። ለመሆኑ ለነዚህ ተማሪዎች ምን የታሰበ ነገር አለ?? ትኬት የቆረጡ ተማሪዎችስ ገንዘባቸው ተመላሽ እንዲደረግ ይሰራል?? ከተለያዩ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ጋርስ ውይይት ተደርጓል??

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኩሪፍቱ ሪዞርት የውኃ መዝናኛ ማዕከል በቅርቡ ለአገልግሎት እንደሚያበቃ ተሰምቷል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
*ከዚህ በላይ አሳሳቢ ጉዳይ የለም*

(ሼር ይደረግ)

ጫካ ያደሩ ህፃናትና እናቶች አረጋውያንና ደካሞች ከምንም በላይ "የኢትዮጵያዊያን ያለህ!" እያሉ ነው።

ነገ ሰኞና ማክሰኞ መስከረም 28-29
በሀገር ፍቅር ቴአትር ከጠዋቱ 3:00 እስከ ምሽቱ 11:30 የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በመቂስ ወጥተው ከቤኒሻንጉል የተፈናቀሉ ከ90 ሺህ በላይ ወገኖቻችንን ለመርዳት ወደ #ሀገር_ፍቅር_ቴአትር ያመራሉ ተብሎ ይጠበቃል። እርስዎም የበኩልዎን ድጋፍ እንዲያደርጉ ሙሉ ቀን ቆመን እንጠብቅዎታለን።

ለማስታወስ ያህል፦

#የማይበላሹ_ምግቦች
መኮረኒ
ሩዝ
ፉርኖ ዱቄት
ዘይት
ሴሪፋም /ፋፋ/
ብስኩት /ጋቤጣ/

#የንጽህና_ቁሳቁሶች
ሳሙና
ኦሞ
ሳኒታይዘር
የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ /ሞዴስ/

#አልባሳት
ብርድ ልብስ
ነጠላ ጫማ
የተለያዩ አልባሳት (ያገለገሉም ቢሆን)
ለበለጠ መረጃ መሐመድ ካሳ ወይንም ያሬድ ሹመቴን በሚከተለው ስልክ ማግኘት ይችላሉ 0930 36 52 44

#ቅድሚያ_ለሰብዓዊነት !!

(ከአንድ ግዜ በላይ ሼር እንዲያደርጉ እንማፀናለን)

ከያሬድ ሹመቴ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የህዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች በዛሬው ዕለት ከ8 ሰዓት ጀምሮ የመክፈቻ ስነ ስርዓት ያካሄዳሉ፡፡ የጋራ ምክር ቤቶቹ 5ኛ የፓርላማ ዘመን፣ 4ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ፣ አንደኛ መደበኛ ጉባዔን ያካሄዳሉ፡፡

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጨፌ ኦሮሚያ⬇️

​ጨፌ ኦሮሚያ በክልል ደረጃ የነበሩ የቢሮ ቁጥሮችን ከ42 ወደ 38 ዝቅ እንዲሉ ውስኗል።

ጨፌ ኦሮሚያ የክልሉን አስፈጻሚ አካላት መልሶ ለማደራጀትና ስልጣንና ሃላፊነታቸውን ለመወሰን የወጣውን አዋጅ አፀደቀ።

የጨፌ ኦሮሚያ 4ኛ ዓመት 5ኛ የስራ ዘመን 3ኛ አስቸኳይ ጉባኤ በዛሬው እለት ማካሄድ ጀምሯል።

ጉባዔው በጥዋት ውሎውም የክልሉን አስፈጻሚ አካላት መልሶ ለማደራጀትና ስልጣንና ሃላፊነታቸውን ለመወሰን የወጣው ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ አፅድቋል።

ረቂቅ አዋጁ ችግር የሚስተዋልበትን የአስፈጻሚ አካላት አደረጃጀት፣ የሰው ሃይልና በጀት አጠቃቀም ላይ የሚስተዋለውን ሰፊ ክፍተት የሚቀርፍ መሆኑ በጉባዔው ላይ ተነስቷል።

ከዚህ ባለፈም በቢሮ ደረጃ ተከማችተው የሚገኙ የአስፈጻሚ አካላት አደረጃጀቶች ታች ካለው ማህበረሰብ ጋር ቀርበው እንዲያገለግሉ ከማድረግ አኳያ ትልቅ ሚና ይኖረዋልም ነው የተባለው።

ከዚህ በፊት በነበረው አደረጃጀት በክልል ደረጃ 42 የነበሩ ቢሮዎች በዛሬው እለት በፀደቀው አዋጅ መሰረት ወደ 38 ዝቅ እንዲደረጉም ተወስኗል።

በአዲሱ አደረጃጀት መሰረትም፦

1. የርእሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት
2. የእርሻ እና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ
3. የከተማ ልማትና ቤቶች ቢሮ
4. የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ
5. የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ
6. የትምህርት ቢሮ
7. የጤና ጥበቃ ቢሮ
8. የፀጥታ እና አስተዳደር ቢሮ
9. የውሃ እና ኢነርጂ ልማት ቢሮ
10. የመሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም ቢሮ
11. የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ
12. የንግድ ቢሮ
13. የሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ
14. የባህልና ቱሪዝም ቢሮ
15. የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ
16. የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ
17. የኢንተርፕራይዝና ኢንደስትሪ ልማት ቢሮ
18. የትራንስፖረት ባለስልጣን
19. የመንገዶች ባለስልጣን
20. የመንግስት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ባለስልጣን
21. የአካባቢ፣ የደን እና የአየር ንብረት ለውጥ ባለስልጣን
22. የኮንስትራክሽን ባለስልጣን
23. የማእድን ልማት ባለስልጣን
24. የግብርና ግብአቶች ቁጥጥር ባለስልጣን
25. የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና መገናኛ ባለስልጣን
26. የአርብቶ አደር አካባቢዎች ልማት አስተባባሪ ኮሚሽን
27. የእቅድና ኢኮኖሚ ልማት ኮሚሽን
28. የኢንቨስትመንት ኮሚሽን
29. ፖሊስ ኮሚሽን
30. የማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን
31. የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን
32. ስፖርት ኮሚሽን
33. የህብረት ስራዎች ማስፋፊያ ኤጀንሲ
34. የእንስሳት ሀብት ልማት ኮሚሽን
35. የገበያ ልማት ኮሚሽን
36. የግብርና ጥናት ኢንስቲቲዩት
37. የከተሞች ፕላን ኢኒስቲቲዩት
38. የመንግስት ህንፃዎች አስተዳደር በመሆን በአዲስ መልክ ተደራጅተዋል።

ምንጭ፦ ፋና
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ⬆️

"ሠላም ጸግሽ! በአዲሱ ፍኖተ ካርታ ዙሪያ የሚደረገዉ ዉይይት በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከአካዳሚክ ስታፎችና ከአስተዳደር ሰራተኞች ጋር ዛሬ ጥዋት ተጀምሯል። ዉይይቱም ለ3 ተከታታይ ቀናት የሚደረግ ይሆናል ተብለናል፡፡"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከደብረ ማርቆስ⬆️

"ይድነቃቸው አየለ ከወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት ፕሬዘዳንት የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎች ህብረት ፕሬዘዳንት በመሆን ለቀጣይ ሁለት አመት ተመርጧል።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በቅርቡ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በካማሺ ዞን በተከሰተዉ ግጭት ከ70,000 በላይ ሰዎች መፈናቀላቸዉ ይታወሳል። ተፈናቃዮቹ ወደ ኦሮሚያ ክልል፣ ማለትም፣ በምሥራቅ እና በምዕራብ ወለጋ ዞኖች መጠለያ ማግኘታቸው ተገልጿል። ለደህንነታቸው በመስጋት ንብረታቸዉን ጥለው ከተፈናቀሉት 70,000 ዉስጥ እስከ ትላንት ማታ ድረስ ከ28,000 በላይ ወደ ቀየያቸዉ #መመለሳቸዉን ፣ የተቀሩትንም ወደ ቀያቸዉ ለመመለስ ስራ እየተሰራ መሆኑን የኦዴፓ ጽህፈት ቤት የገጠር አደረጃጀት ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ ዛሬ ጥዋት በፌስቡክ ገፃቸዉ ያሰፈሩት ጽሁፍ አመልክቷል።

ምንጭ፦ ዶቼ ቨለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የፀረ ሽብር ህግ⬇️

ጠቅላይ አቃቤ ህግ በፀረ-ሽብር ህጉ ክፍተቶች ዙሪያ ሲያካሄድ የነበረውን #የጥናት ውጤት ይፋ አድርጓል።

የህግና ፍትህ ጉዳዮች አማካሪ ጉባዔ የፀረ-ሽብር ህግ እና ሲቪክ ማህበራት ህግ ላይ ባሉ ክፍተቶች ዙርያ ባለፉት ሶስት ወራት ጥናት ሲያካሂድ እንደነበረ የጠቅላይ አቃቤ ህግ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚኑኬሽን ዳይሬክተር አቶ #ታዬ_ደንደአ ለኢቲቪ ገልፀዋል፡፡

እነዚህ ሁለቱ ህግጋት ላይ ህብረተሰቡም ሆነ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች የሚያነሱትን ጥያቄ ከግምት በማስገባት መንግስት የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት ካለው ቁርጠኝነትም ጋር ተያይዞ ህግጋቱን ሲመረምር እንደነበረም ነው የገለፁት፡፡

በዚሁ መሰረት ጉባኤው በፀረ-ሽብር ህጉ ከለያቸው ክፍተቶች አንዱ የአዋጁ ይዘትና አተረጓጎም ነው፡፡

በመረጃ አሰባሰብ ረገድም ክፍተት እንዳለበት ተመልክቷል፡፡ በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የሚውሉ ሰዎች የዋስትና መብት አለማግኘታቸውና የፍርድቤትን ስልጣን መገደብም ህጎቹ ላይ የሚታዩ ክፍተቶች በሚል በጉባኤው ታይተዋል፡፡

የህጉ አተገባበርም የጐላ ክፍተት ያለበት መሆኑን ነው የተገለፀው፡፡ በዚህም መሰረት ጉባዔዉ ሶስት አማራጮችን አቅርቧል፡፡

ህጉ ያስፈልጋል አያስፈልግም የሚለው ከነዚህ ውስጥ ዋነኛው ነው፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይም በመጪው ረቡዕ የተመዘገቡም ሆነ ያልተመዘገቡ የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ሌሎች አካላት በሚገኙበት የጥናቱ ውጤት ላይ ግብዓት የሚሰበሰብ ይሆናል፡፡

የህግና ፍትህ ጉዳዮች አማካሪ ጉባዔ በሌሎች ህጐች ላይም የማሻሻያ ጥናቶች እያደረገ ነው፡፡

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UpdateSport ኢትዮጵያ እና ኬንያ በባሕር ዳር ለሚያደርጉት የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የስታድየም #መግቢያ ዋጋ ይፋ ሆኗል፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት እንዳስታወቀው የስታድየም መግቢያ ዋጋውን በአራት ደረጃ አስቀምጧል፡፡

በዚህም መሠረት፡-

1ኛ.ክቡር ትሪቡን 200 ብር
2ኛ.ከክቡር ትሪቡን ጎን ለጎን 50 ብር
3ኛ. ሶስተኛ ደረጃ 25 ብር
4ኛ.አራተኛ ደረጃ 10 ብር መሆኑን አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ማርኬቲንግ ዳይሬክተር አቶ ኢሳያስ ታደሰ ተመልካቾች ትኬቱን ረቡዕ ከቀኑ 6፡00 ጀምሮ በባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታድየም ማግኘት እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡ ጨዋታው ረቡዕ ከቀኑ 10፡00 ይጀምራል፡፡

ምንጭ፦ አ.ብ.መ.ድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia