TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የትምህርት ሚንስትሩ ዶክተር ጥላዬ ጌቴ እንደተናገሩት፤ በዘንድሮው የትምህርት ዘመን #የፀጥታ_ችግሮች እንዳይከሰቱ ጥቅምት 2 ቀን 2011 ዓ.ም ሁሉንም ባለድርሻ አካላት የሚሳተፉበት ህዝባዊ #ውይይት በተለያዩ የአገሪቷ አካባቢዎች ይካሄዳል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት⬇️

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚከሰቱ #የጸጥታ ችግሮችን አስቀድሞ መከላከል እንዲቻል በአገር አቀፍ ደረጃ ህዝባዊ ውይይት እንደሚካሄድ የትምህርት ሚንስትር ዶክተር #ጥላዬ_ጌቴ ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር #አብይ_አህመድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ሰላማዊና ደህንነታቸው የተረጋገጠ ለማድረግ ከዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶችና ከክልል ርዕሰ መስተዳድሮች ጋር መወያየታቸውንም አክለዋል።

ባለፈው የትምህርት ዘመን በተወሰኑ የመንግስት የከፍተኛ ተቋማት በተነሱ #ግርግሮች ምክንያት የሰው ህይወት ማለፉና ንብረት መውደሙ ይታወሳል።

የትምህርት ሚንስትሩ ዶክተር ጥላዬ ጌቴ በተለይ ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ በዘንድሮው የትምህርት ዘመን መሰል ችግሮች እንዳይከሰቱ ጥቅምት 2 ቀን 2011 ዓ.ም ሁሉንም ባለድርሻ አካላት የሚሳተፉበት ህዝባዊ #ውይይት በተለያዩ የአገሪቷ አካባቢዎች ይካሄዳል።

“በትምህርት ተቋማት ውስጥ የተማሪዎች ዋነኛ ተግባር መማርና መመራመር ነው” ያሉት ሚንስትሩ፤ መንግስት ተቋማቱ ከማንኛውም የጸጥታ ችግር ነጻ ሆነው አገልግሎት እንዲሰጡ ከመቸውም ጊዜ በላይ አበክሮ እንደሚሰራ ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከ11ኛው የኢህአዴግ ጉባኤ ጎን ለጎን የጸጥታ አካላትን ባሳተፈ መልኩ ከዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶች እና ከክልል ርዕሰ መስተዳድሮች ስለ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የጸጥታ ችግሮችና #መፍትሄዎቻቸው መወያየታቸውንም
አውስተዋል።

ይህም መንግስት ለጉዳዩ ትኩረት መስጠቱን እንደሚያሳይ ገልጸው፤ ዘንድሮ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚቀላቀሉ ተማሪዎች ወደ መደበኛ የመማር ማስተማር ሂደት ከመመለሳቸው በፊት ውይይት እንደሚያደርጉም ተናግረዋል።

በተያያዘ ዜና ዶክተር ጥላዬ ጌቴ በትምህርት ፍኖተ ካርታ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር የተካሄደው ውይይት በርካታ ጠቃሚ ግብአቶች የተገኙበት እንደነበረ ጠቁመዋል።

በቅርቡ ፍኖተ ካርታውን በተመለከተ “የተለያዩ ህብረተሰብ ክፍሎች የሚሳተፉበት ትልቅ ህዝባዊ ውይይት በአዳማ ከተማ ይዘጋጃል” ብለዋል።

እስካሁን ባለው ሂደት የተገኙ ግብዓቶችን በማካተት ፍኖተ ካርታው እንደሚሻሻልም ገልጸዋል።

በዘንድሮው የትምህርት ዘመን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን መግቢያ ያሟሉ 149 ሺህ ተማሪዎች በተለያዩ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች መመደባቸውን ከትምህርት ሚንስቴር የተገኘ መረጃ ያመለክታል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የአዳማ ኢንደስትሪ ፓርክ የምረቃ ስነ ስርዓት እየተካሄ ይገኛል። በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር #ዐቢይ_አህመድ፣ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት አቶ #ለማ_መገርሳና የአማራ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ #ገዱ_አንዳርጋቸው፣ ዶ/ር #አርከበ_ኤቁባይ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ተገኝተዋል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵየ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አዳማ⬆️

በ2ኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ በመንግስት ለመገንባት ከታቀዱት የኢንዱስትሪ ፖርኮች 2ኛው የሆነው የአዳማ የኢንዱስትሪ ፓርክ በዛሬው ዕለት በክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር #አብይ_አህመድ ተመርቋል።

©Fitsum Arega
@tsegabwolde @tikvahethiopia
OBN LIVE! የአዳማ ኢንድስትሪ ፓርክ ምረቃ ስነ ስርዓት!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኦነግ⬇️

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ሊቀመንበር አቶ #ዳውድ_ኢብሳ ድርጅታቸው #ትጥቁን ለመፍትት ከመንግስት ጋር አለመስማማቱን ተናገሩ። አቶ ዳውድ ከዋልታ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቆይታ"ኦነግ ወደ ሀገር ውስጥ የገባው ትጥቅ ፈተኖ ነው የሚለውን መረጃ አስተባብለዋል።

አቶ ዳውድ ለዋልታ ሲናገሩ "እኛ ትጥቅ እንድንፈታ የተስማማንበት ስምምነት የለም። #የታጠቀው አካል ትጥቅ #ይዞ እያለ እኛ ትጥቅ #የምንፈታበት ምክንያት የለም።" ብለዋል። አክለውም "ትጥቅ መፍታት የሚባል sensitivity ጥያቄ ነው። ትጥቅ ፈቱ መባልም አንፈልግም። ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚመጣው አንዱ ትጥቅ የሚፈታ አንዱ ትጥቅ የሚያስፈታ ይመስላል። የሀገሪቱ ሰላም እንዲጠበቅ ኦነግ ያለው ሚና ምን እንደሚሆን ነው የተስማማነው።" ሲሉ ለዋልታ ቴሌቪዥን ተናግረዋል። አቶ ዳውድ ሰኔ 16 በጠቅላ ሚንስትሩ ላይ በተደረገው #የግድያ ሙከራ ድርጅታቸው እንዳልተሳተፈ ገልፀዋል። በቡራዩና በአዲስ አበባ በተፈጠሩ ግጭቶችም ኦነግ አለመሳተፉን ሊቀመንበሩ ገልፀዋል።

አቶ ዳውድ በበደኖና በአርባ ጉጉ በአማራ ተወላጆች ላይ የደረሰው ጭፍጨፋ #በገለልተኛ አካል #እንዲጣራ የኦነግ ፍላጎት መሆኑን አንስተዋል።

#TIKVAHETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀዋሳ⬆️በአሁኑ ሰዓት በሀዋሳ ከተማ መስቀል አደባባይ ለሲዳማ አርነት ንቅናቄ(ሲአን) ከፍተኛ አመራሮች የአቀባበል ስነ ስርዓት በመደረግ ላይ ይገኛል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ክቡር ጠ/ሚ አብይ አህመድ በአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ምረቃ ስነ ስርዓት ላይ ካደረጉት ንግግር የተወሰዱ አንኳር ነጥቦች፡-

• ከንግዲህ ትኩረታችን ወጣቱን የስራ ባለቤት ማድረግ ነው

• ፊታችንን ወደ ስራ ለማዞር የማብሰሪያው ዕለት ነው #ዛሬ

• የልማት እንቅስቃሴ እንዲስፋፋ ማድረግ የመንግስት ዋነኛው ስራ ነው

• የኢንዱስትሪ ልማት ሲስፋፋ ቦታው ለትራንስፖርት ምቹ መሆኑ ይታያል፤ አዳማን የሚያህል ምቹ ስፍራ የለም፤ የባቡር መስመር፣ ፈጣን መንገድ፣ ወደፊት በቅርብ ርቀት የሚሰራው ትልቁ የአየር ማረፊያ

• የአዳማ ወጣትና ነዋሪ ላለፉት ጊዜያት በተካሄደው ትግሉ ካለአንዳች ጥፋት ተቃውሞውን በሰላማዊ መንገድ ሲገልፅ የቆየ ነው

• የባለሀብቶች ዋነኛው ጥያቄ መንገድ አለ ወይ ሳይሆን ሰላም አለ ወይ በመሆኑ ሰላማችሁን መጠበቃችሁን አትዘንጉ

• በተለመደው መንገድ በኦሮሞ ባህል ባለሀብቱን የመሳብ የማቀፍ ስራችሁን ቀጥሉ

• ከወራት ትግል በኋላ ወጣቱ አሁን ፊቱን በሙሉ ልብ ወደ ስራ ደወ ልማት ወደ እድገት ማዞር ይኖርበታል፡፡ የትግል ሱስ ያለበት የለምና፡፡

• ዶ/ር አርከበ ሰርቶ የሚያሳይ ብቃት ያለው ከፖለቲካ ሻጥር ራሱን አውጥቶ በስራ የተጠመደ ክቡር ሰው ነው

• ቀበቶአችሆን አጥብቃችሁ ለሚጠብቀን ቀጣይ ስራ ተዘጋጁ

• ዶ/ር መሰለ ኃይሌ በታላቅ ጥረት ውጤት እንድናመጣ እያገዘን ያለ በመሆኑ ታላቅ ምስጋና ይገባዋል

• አዳማ የሰላም የፍቅር አብሮ የመኖር አብነት በመሆኑ ባለሀብቶች ወደ አዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ፊታችሁን እንድታዞሩ እመክራችኋለሁ

• ዳያስፖራ ኢትዮጵያውያንም በተመሳሳይ ተግባራት ላይ ብትሰማሩ መንግስት ከፍተኛ እገዛ ያደርግላችኋል

• የኢትዮጵያ እውነተኛ የተሃድሶ በርግጥም ከፊታችን እየመጣ ነው

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ዶ/ር አርከበ #ሰርቶ የሚያሳይ ብቃት ያለው ከፖለቲካ ሻጥር ራሱን #አውጥቶ በስራ የተጠመደ ክቡር ሰው ነው።"

▪️▪️▪️ጠ/ሚ ዶክተር አብይ▪️▪️▪️
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ክቡር አቶ ለማ መገርሳ የኦሮሚያ ፕሬዝዳንት በአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ምረቃ ስነስርዓት ላይ ካደረጉት ንግግር የተወሰዱ አንኳር ነጥቦች፡-

• የኢንዱስትሪ ልማት የአገራችንን ጎስቋላ ገፅታ የሚለውጥ ነው

• ግብርና እንዲዘምንና በሂደትም ለኢንዱስትሪ መሪነቱን እንዲለቅ ከፍተኛ አስተዋፅዖ አለው

• መንግስት ለኢንዱስት ልማት ትኩረት ሰጥቷል

• በዘርፉ ተጨባጥና ፍሬያማ ስራዎች እየተሰሩ ነው

• የተመቻቸ የኢንዱስትሪ ፓርክ ባለሀብቶች በአጭር ጊዜ ስራ እንዲጀምሩ ያስችላል

• የአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ፋና ወጊ ከሆኑት መካከል ነው

• በጠርቃጨርቅና አልባሳት ስፔሺያላይዝ ያደረገ ፓርክ ነው

• ለባቡር፣ አየር፣ የብስ ትራንስፖርተ ቅርበት ያለው ከተማ ነው አዳማ

• ከውጭ የሚመጡ ምርቶችን በአገር ውስጥ ለማምረት የሚያስችል፣ የአርሶ አደሩን ገቢም የሚያሻሽል ፓርክ ነው

• በሙሉ አቅሙ መንቀሳቀስ ሲጀምር ለበርካታ ዜጎች የስራ ዕድል ይፈጥራል

• የቴክኖሎጂ ሽግግርኽ የጥናትና ምርምር ማዕከል ይሆናል ፓርኩ

• የላቀ የብቃት ማዕከል እንዲሆን እንሰራለን

• ወጣቶች በአነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት ተደራጅተው ለኢንዱስትሪ ፓርኩ ግብዓት እንዲያቀርቡ ይመቻችላቸዋል

• የክልሉ መንግስት ለአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ዶ/ር አርከበ ዕቁባይ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የቦርድ ሊ/መንበር በአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ምረቃ ስነስርዓት ላይ ካደረጉት ንግግር የተወሰዱ አንኳር ነጥቦች፡-

• የአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ከ2000
ሄክታር በላይ መሬት ላይ ያረፈ ፓርክ ነው

• ከሃዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክና ከሌሎች ቀደም ሲል ከተሰሩት ፓርኮች ልምድ ተቀምሮ የተሰራ ነው

• በዋናው የኢትዮ-ጅቡቲ የኤክስፖርት ኮሪዶር ላይ የሚገኝ ፓርክ ነው

• ትላልቅ ዓለም አቅፍ ኩባንያዎች የሚስተናገዱበት ፓርክ ነው

• ከአፍሪካ ትላልቅ የኢንዱስትሪ ፓርኮች አንዱ ነው

• ኢትዮጵያ በ2012 በድምሩ 30 ፓርኮች ይኖሯታል

• በኢንዱስትሪ ፓርኮች የኃይል አቅርቦት እጥረት ስላለ መንግስት ችግሩን ለመፍታት ትኩረት ሰጥቶ መስራት አለበት

• በዘርፉ የሰው ኃይል ልማትም ሌላው ወሳኝ ጉዳይ ነው

• የአዳማና አካባቢው ወጣቶችና ነዋሪዎች ፓርኩን እንደ ዓይናቸው ብሌን ሊጠብቁት ይገባል

• ለዚህ ፓርክ ልማት ተነሺዎች የስራ ዕድል መፍጠር መንግስት ያስቀመጠው አቅጣጫ በመሆኑ ይህንኑ አቅጣጫ ይዘን እንሰራለን

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia