TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ለተማሪዎች📌በትዕግስት ጠብቁ ኤጀንሲው ይፋ ይደረጋል ያለው 8:00 ነው። ማየት ያልቻላችሁት በሲስተም ችግር ሊሆን ይችላል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና‼️ዶክተር አብይ አህመድ አሊ የኢህአዴግ ሊቀ መንበር ሆነው #መመረጣቸው ተሰማ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አስቸኳይ ማስታወቂያ‼️

መስከረም 25 ቀን 2011 ዓ.ም ለሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሙሉ የዩኒቨርሲቲያችን ነባር ተማሪዎች ምዝገባ ጥቅምት 2 እና 3 ቀን 2011 ዓ.ም ለአዲስ ተማሪዎች ደግሞ ጥቅምት 9 እና 10 2011 ዓ.ም መሆኑን በመግለፅ በእነዚህ ቀናት በዩኒቨርሲቲው ተገኝታችሁ እንድትመዘገቡ በተለያዩ ሚዲያዎች ጥሪ ማስተላለፋችን ይታወቃል፡፡

ሆኖም ግን የዩኒቨርሲቲያችን የ2011 የትምህርት ዘመን የቅድመ ምረቃማ ሆነ የድህረ ምረቃ ተማሪዎች ምዝገባ ላልተወሰነ ጊዜ የተራዘመ በመሆኑ በሌላ ማስታወቂያ ጥሪ እስኪደርግላችሁ
ድረስ ባላችሁበት እንድትቆዩ እናሳውቃለን፡፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የሕዝብና ዓለም ዓቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
025 553 0355

ምንጭ፦ HU FM 91.5
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አርሲ ዩኒቨርሲቲ⬆️የነባር ተማሪዎች የምዝገባ ቀን ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን ተቋሙ ዛሬ ባወጣው ማስታወቂያ ገልጿል። 25/01/2011

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና‼️አቶ #ደመቀ_መኮንን የኢህአዴግ ምክትል ሊቀ መንበር ሆነው #መመረጣቸው ተሰማ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከዚህ ሰዓት አንስቶ ምደባችሁን ማየት ትችላላችሁ!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለተማሪዎች‼️የዩኒቨርሲቲ እና የትምህርት ዘርፍ ምደባችሁን በ https://app.neaea.gov.et/Home/Student ገብታችሁ ማየት ትችላላችሁ።

መልካም እድል!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ይህን #የቴሌግራም ቦት በመጠቀም በቀላሉ የ12ኛ ክፍል ውጤታችሁን እና የተመደባችሁትን ዩንቨርሲቲ በቀላሉ ማወቅ ትችላላቹ ።

👉To use the bot
> join @grade_12_placement_bot
> click on start
> put your registration number
> results will be displayed.

🙏ብሩክ ጥላሁን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

@tikvahethiopia @tsegabwolde
AAU⬆️የነባር ተማሪዎች የምዝገባ ቀን ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን ተቋሙ ዛሬ ባወጣው ማስታወቂያ ገልጿል። 25/01/2011

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ትብብር📌ከዚህ በታች ያሉት ኢትዮጵያዊያን ኔትዎርክ ለሚያስቸግራችሁ ተማሪዎች ምደባችሁን ያዩላችኋል፦

የAd. No. ላኩላቸው!

@Dan_Leinad
@benismart76
@Regina_phalangeeeee
@kiru04
@Fila24
@bettyt7
@Bekayejc14
@Azfsh2
@mgswt
@Baelak
@twenty47here
@Henoktes72
@Mube11
@Muk_te
@Ye_habshea_lij
@nalifa
@Gibtar
@Zolina22
@abtimab123
@JasmineMoh
#Update ድምጽ አልተሰጠም፡፡ እስካሁን የኢህአዴግ ሊቀመንበር እና የምክትል ሊቀመንበር ምርጫ አልተካሄደም፡፡ ከምሳ መልስ ጉባኤው ከ 9፡00 ጀምሮ ቀጥሏል፡፡ አሁን የኦዲት ሪፖርት እየተደመጠ ነው፡፡ ቀጥሎ የኢህአዴግ ሊቀመንበር እና ምክትል ሊቀመንበር ምርጫ ድምጽ እንደሚሰጥ ይጠበቃል፡፡ 11ኛው የኢህአዴግ ጉባኤ በሀዋሳ እየተካሄደ መሆኑ ይታወሳል፡፡
ከላይ ያለው የአማራ መገናኛ ብዙሀን ድርጅት ዘገባ ነው።

#TIKVAH_ETHIOPIA

የኢህአዴግ - ሊቀ መንበር ዶ/ር አብይ አሀመድ
የኢህአዴግ - ምክትል ሊቀ መንበር አቶ ደመቀ መኮንን

መረጃው በመንግስት ሚዲያዎች ይፋ እስኪደረግ እንጠብቃለን።
@tsegbwolde @tikvahethiopia
ይህ ደግሞ የፋና ዘገባ ነው፦

11ኛውን ድርጅታዊ ጉባኤውን በማድረግ ላይ የሚገኘው ኢህአዴግ ሊቀመንበሩንና ምክትል ሊቀመንበሩን #በመምረጥ ላይ ይገኛል። በእስካሁኑ ሂደት ሶስት አመራሮች በእጩነት ተጠቁመዋል። ምርጫውንም የሚመራ 12 አባላት ያሉት ኮሚቴም መዋቀሩ ነው የተመለከተው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ይህ ደግሞ የetv ዘገባ ነው፦

ዶክተር ዐቢይ አህመድ፣
አቶ ደመቀ መኮንንና
ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል
ኢህአዴግን ለመምራት #በእጩነት ቀረቡ።

ምርጫውን የሚመራ 12 አስመራጭ ኮሚቴ ተሰይሞ የምርጫ ሂደቱ እየተከናወነ መሆኑንም የኢህአዴግ ፌስ ቡክ ገፅ ይፋ አድርጓል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዲላ ዩኒቨርሲቲ⬆️የነባር ተማሪዎች የምዝገባ ቀን ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን ተቋሙ ዛሬ ባወጣው ማስታወቂያ ገልጿል። 25/01/2011

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አስቸኳይ‼️ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ዩኒቨርሲቲዎች የ2011 ዓ.ም. የተማሪዎች የምዝገባ ቀን በድጋሜ መራዘሙን በይፋዊ #ፌስቡክ ገፃቸው እና በተቋማቸው ግቢ ውስጥ በለጠፉት ማስታወቂያ ላይ ገልፀዋል፦

. አክሱም ዩኒቨርሲቲ
. ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ
. ዲላ ዩኒቨርሲቲ
. ጎንደር ዩኒቨርሲቲ
. ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ
. አዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ
. ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ
. ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ
. ወለጋ ዩኒቨርሲቲ
. ጅማ ዩኒቨርሲቲ
. ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ(esp.)
. ሀረማያ ዩኒቨርሲቲ
. ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ
. ወሎ ዩኒቨርሲቲ
. ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ
. አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
. አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
. አምቦ ዩኒቨርሲቲ

ማሳሰቢያ፦ የተለወጠ ወይም የተሳሳተ መረጃ ካለ በፍጥነት አሳውቃችኋለሁ ወይም ማስተካከያ ሰጥበታለሁ።

#ETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ይኸው ዜናው⬆️

ዶክተር አብይ - ሊቀ መንበር
አቶ ደመቀ - ምክትል ሊቀ መንበር

ምንጭ፦etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ወ/ሮ ሙፈሪያት በምርጫው ላይ አልተሳተፉም። የኢህአዴግ ለቀ መንበር ዶክተር አብይ አህመድ እና ምክትል ሊቀ መንበር አቶ ደመቀ መኮንን ሆነው ተመርጠዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኢህአዴግን በአመራርነት ለመምራት #እጩዎች ሆነው የቀረቡት፦

▪️ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከኦዴፓ
▪️አቶ ደመቀ መኮንን ከአዴፓ
▪️ዶ/ ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ከህወሓት

ድምፅ በመስጠት 177 ሰው ተሳትፏል፡፡
ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከተሰጠው ድምፅ 176 ድምፅ አግኝተዋል፡፡ አቶ ደመቀ መኮንን ደግሞ 149 ድምፅ በማግኘት በምክትል ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል፡፡ ዶክተር ደብረ ፅዮን ገ/ሚካኤል ለምክትል ሊቀመንበርነት ቀርበው 15 ድምፅ አግኝተዋል፡፡

የደኢህዴን ሊቀመንበር የሆኑት ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል በምርጫው አለመሳተፋቸው ተመልክቷል፡፡
ምርጫውን የሚመራ 12 አስመራጭ ኮሚቴ ተሰይሞ የምርጫ ሂደቱ ተከናውኗል፡፡

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የመግቢያ ጊዜ⬇️

የ2011 የትምህርት ዘመን የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ በትምህርት ፍኖተ- ካርታ ውይይት ምክንያት #መራዘሙን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

በአዲሱ የትምህርት ፍኖተ-ካርታ በሚደረገው ውይይት ምክንያት የ2011 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ጊዜ ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን የሚኒስቴሩ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር ወይዘሮ #ሀረግ_ማሞ አስታውቀዋል።

መንግሥት በቅርቡ አዲስ ባዘጋጀው ረቂቅ የትምህርት ፍኖተ-ካርታ ላይ የተጀመረው ውይይት ላይ ተጨማሪ ግብዓት ማሰባሰቢያ ውይይት ስለሚደረግ ቀደም ብሎ ተላልፎ የነበረው የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጥሪ መራዘሙን ዳይሬክተሯ አስታውቀዋል።

ዩኒቨርሲቲዎች ከመምህራኖቻቸው እና ከአስተዳደር ሠራተኞቻቸው ጋር በረቂቅ ፍኖተ-ካርታው ላይ ውይይት አድርገው ሲያበቁ ከጥቅምት ወር መጀመሪያ አንስቶ እንደ የዩኒቨርሲቲዎቹ መርሀ-ግብር የተማሪዎች መግቢያ ጥሪ ይደረጋል ተብሎ የቆየ ቢሆንም ውይይቱ እየተካሄደ በመሆኑ ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሟል።

ባለፉት ሁለት ወራት ውይይት ሲደረግበት የቆየው የትምህርት ፍኖተ-ካርታ ረቂቅ ጥናት ግብዓት ማሰባሰብ ሂደት ከአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ማኅበረሰብ አባላት ጋርም በዛሬው ዕለት በመላ አገሪቱ ውይይት እየተደረገበት ይገኛል።

በመሆኑም ውይይቱ ሲጠናቀቅ በማዕከል በኩል ለሁሉም የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች #ጥሪ እንደሚደረግ ተናግረዋል።

በአገር አቀፍ ደረጃ የተዘጋጀው የትምህርትና ስልጠና ፍኖተ-ካርታ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ያለመ ሲሆን ለተግባራዊነቱ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር #ውይይት እየተደረገ መሆኑ ይታወቃል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
etv zena live! የ11 ኛው የኢህአዴግ ጉባኤ ማጠቃለያ መርሃ ግብር!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ማስታወሻ📌የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ነገ በሀዋሳ አለም አቀፍ ስታዲየም የኢህአዴግን ድርጅታዊ ጉባኤ መጠናቀቅን አስመልክቶ ልዩ መርሃ ግብር ተዘጋጅቷል። ሁላችሁም #ተጋብዛችኋል!

ከጥዋቱ 2 ሰዓት ጀምሮ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia