አዲስ አበባ⬆️የአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ አመራሮችና የምክር ቤት አበላት ሰሞኑን በቡራዩና አካባቢው በተፈፀመው #ጥቃት ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች በመድሐኒአለም ትምህርት ቤት ተገኝተው አፅናንተዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አምቦ ዩኒቨርሲቲ⬆️የ2011 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የነባር ተማሪዎች ምዝገባ ጥቅምት 5 እና 6 መሆኑን የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ይገልፃል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አዲስ አበባ⬆️
የጋሞ ብሔረሰብ ተወካይ የሆኑ #አባቶች፣ ሴቶችና ወጣቶች ከቡራዩ እና አካባቢዋ #ተፈናቅለው በአዲስ አበባ በተለያዩ መጠልያዎች ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ቦታው ድረስ በመገኘት ጎበኙ፡፡
የጋሞ አባቶች የተከሰተውን ችግር በሠላምና በፍቅር መፍትሔ የሚያገኝበትን መንገድ ለማመቻቸት የጋሞን #ወርቃማ ባህል በመከተል ዕርቅ መፍጠር ይገባል ብለዋል፡፡
#ወጣቱ ትውልድም ባህሉን በማይወክል መልኩ ለሌላ በቀል እንዳይነሳሳ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
©fbc

ምዝገባ⬆️የዳግማዊ ምኒልክ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በመደበኛ መርሃ ግብር ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል። መስፈርቱን የምታሟሉ መመዝገብ ትችላላችሁ።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳሳቢ አዲስ ጉዳይ:- ላፍቶ ክፍለ ከተማ ውስጥ ቻይና ካምፕ አካባቢ ተጨማሪ ከ500 በላይ ተፈናቃይ ወገኖቻችን ማርያም ቤቴክርስቲያን ውስጥ ተጠልለዋል። የተኙበት ክፍል የቆርቆሮ ቤት ጭቃ ረግረግ መሬት ነው። ምንም ፍራሽና አልባሳት የላቸውም። ምግብም የለም። በሌሎቻ ካምፖች ላይ ያሉ እርዳታዎች ለግዜው በቂ በመሆናቸው እባካችሁ ፈጣን ትኩረት ለቻይና ካምፕ ተፈናቃይ ወገኖቻችን።
©ያሬድ ሹመቴ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
©ያሬድ ሹመቴ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update "በሀገሪቱ ካለው #የፀጥታ ችግር ጋር ተያይዞ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመግቢያ ቀን ተራዘመ" እየተባለ የሚሰራጨው መረጃ ፍፁም ከእውነት የራቀና የሀገራችን ሰላም መሆን እንቅልፍ የሚነሳቸው ሰዎች የሚያስወሩት ነው።
🕊እኛ ሁላችንም የኢትዮጵያ ሀገራችን ሰላም አስከባሪ ወታደሮች ነን። በሰላማችን ጉዳይ ከማንም ጋር አንደራደርም🕊
@tsegabwolde @tikvahethiopia
🕊እኛ ሁላችንም የኢትዮጵያ ሀገራችን ሰላም አስከባሪ ወታደሮች ነን። በሰላማችን ጉዳይ ከማንም ጋር አንደራደርም🕊
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ⬆️የ2011 ዓ.ም. የመደበኛ ተማሪዎች የመመዝገቢያ ቀን ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ይገልፃል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በሰኔ 16 የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የድጋፍ ሰልፍ ላይ በራሱ መኪና በመጫን ተጠርጣሪዎችን ቦምቡ የፈነዳበት ቦታ ድረስ በመሸኘት የተጠረጠረው #ብርሃኑ_ጃፋር ላይ ጠቅላይ አቃቢ ህግ እስከ መስከረም
16 ቀን ክሱን እንዲመሰርት ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰጥቷል፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia
16 ቀን ክሱን እንዲመሰርት ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰጥቷል፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አይደለም #ዴሞክራሲ እና #ነፃነትን ልንሸከም ቀርቶ ፌስቡክን እንኳን በአግባቡ #መሸከም አልቻልንም። 10,000,000 የላይሞላ የፌስቡክ ተጠቃሚ የ100,000,000 ሰዎችን ኑሮ እያናጋ ነው። ከጥላቻ እና ከስድብ ተቆጠቡ!
#ETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አዲስ አበባ⬆️
የኢፌዴሪ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአዲስ አበባና አካባቢው ተከስቶ የነበረው ግጭት ወደ #ሰላማዊ ሁኔታ በመመለሱ ምንም የፀጥታ ስጋት እንደሌለ ለድፕሎማትክ ማህበረ-ሰብ ገለፀ።
የኢፌድሪ ዉጭ የጉዳይ ሚኒስቴር ዴታ ወ/ሮ ህሩት ዘመነ ተፈጥሮ የነበረዉ ግጭት ለዉጥን በሚቃወሙ ቡድኖች የተቀነባበረ ነዉ ብለዋል።
ቡራዩ አካባቢ በነበረው ግጭት 25 ሰዎች መሞታቸውን ገልፀዋል።
ግጭቱን መነሻ አድርጎ አዲስ አበባ ላይ በነበረው ሰልፍ ላይም 5 ሰዎች የፀጥታ ኃይሉን መሳሪያ ለመንጠቅ ሲሞከሩ በተወሰደው #እርምጃ መሞታቸውን ተናግረዋል።
መንግስት የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ይሰራል ሲሉ ለድፕሎማትክ ማህበረሰብ አስረድተዋል።
©አብረሓም ብሩ(OMN)

#update የአሜሪካ ኤምባሲ⬇️
ረቡዕ መስከረም 9 ቀን 2011 ዓ.ም. ‹‹በአዲስ አበባ ከተማ ታላቅ ሕዝባዊ ሠልፍ እንደሚኖር ተገምቷል፤›› ብሎ የኤምባሲው ሠራተኞች ከቤታቸው እንዳይወጡ፣ በተጠቀሰው ቀንም ኤምባሲው ሥራ እንደማይኖረው ገልጾ የአሜሪካ ኤምባሲ ያወጣው ማሳሰቢያ በርካቶችን ግር አሰኝቷል፡፡ ኤምባሲው ከአስተማማኝ መረጃ አረጋግጫለሁ ያለለት ሠልፍም #አልተካሄደም፡፡
ኤምባሲው በድረ ገጹ ሁሉም የቪዛ አገልግቶችና የአሜሪካ ዜጎች አገልግሎት ቀጠሮዎች ሙሉ በሙሉ መሰረዛቸውንና አሜሪካዊ ዜግነት ያላቸው ሰዎች በድረ ገጹ አማካይነት ሌላ ቀጠሮ እንዲይዙ ገልጿል፡፡ የኢሚግሬሽን ቪዛ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ሌላ ቀጠሮ ተዘጋጅቶ እንደሚጠሩና ከዚህ ውጪ ያሉ የቪዛ አገልግሎት የሚጠይቁ ሰዎች በኤምባሲው ድረ ገጽ ቀጠሮ እንዲያሲዙ አሳስቦ ነበር፡፡
ኤምባሲው ይህን ካለ በኋላ በሠልፉ የሚሳተፉ ዜጎች ሰላማዊ በሆነ መንገድ መልዕክታቸውን እንዲገልጹ እንደሚያበረታታም አስታውቋል፡፡
ይሁን እንጂ የአሜሪካ ኤምባሲ ያወጣውን መግለጫ ያየው የእንግሊዝ ኤምባሲ፣ ‹‹የአሜሪካ ኤምባሲና የኢንተርናሽናል ኮሙዩኒቲ ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸውን እናውቃለን፡፡ ነገር ግን የእግሊዝ ኤምባሲ ሌላ ማሳሰቢያ እስካልወጣ ድረስ መደበኛ ሥራውን ያከናውናል፤›› ሲል በትዊተር ገጹ ላይ አስታውቋል፡፡ የኤምባሲው መረጃ የደረሳቸው ዓለም አቀፍ ተቋማትም ሠራተኞቻቸው ሥራ እንዳይገቡ ያደረጉ ሲሆን፣ ሌሎች ከኤምባሲው ጋር ግንኙነት ያላቸው የአገር ውስጥ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሠራተኞችም በተመሳሳይ ሥራ እንዳልገቡ ሪፖርተር ማረጋገጥ ችሏል፡፡
አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ቃል አቀባይ ኒክ ባርኔት ከሪፖርተር ጋር በነበራቸው የስልክ ቆይታ፣ በተጠቀሰው ቀን ሠልፍ እንደሚኖር አስተማማኝ መረጃ እንደደረሳቸውና በዚህ መረጃ መሠረት ኤምባሲው እንደወሰነ ገልጸው፣ ይኼንን ዓይነት ውሳኔ ለሕዝብ ይፋ ማድረግ ኤምባሲው #በሕግ ስለሚገደድ በይፋ እንዳጋራው ተናግረዋል፡፡
ነገር ግን ሰዎች ኤምባሲው #ድብቅ አጀንዳ እንዳለው አድርገው እንደተመለከቷቸውና ይህ ማሳሰቢያ የዜጎችን ደኅንነት ከማስጠበቅ የዘለለ ሌላ ሚና እንደሌለው ተናግረዋል፡፡
‹‹ሠልፉ #ሰላማዊ ቢሆን እንኳን ተፅዕኖ ሊኖረው ይችላል፡፡ ሰዎች ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ ላይችሉና በቤታቸውና በመሥሪያ ቤታቸው መካከል ሆነው መንቀሳቀስ ሊሳናቸው ይችላል፡፡ እኛም አገልግሎቶችን ለመስጠት እንቸገራለን፤›› ሲሉ ባርኔት አስታውቀዋል፡፡ ስለዚህ አስተማማኙ ውሳኔ ሠራተኞቻችን ቤት እንዲቆዩ መምከር ነው ብለዋል፡፡
ይሁንና በአዲስ አበባ ምንም ዓይነት ሠልፍ በሌለበት ጊዜ ኤምባሲው ይኼንን መግለጫ በማውጣቱ በርካቶች በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ሲተቹና የሐሰት መረጃ አሠራጭ ሲሉ ወቅሰዋል፡፡
ይሁን እንጂ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በአዲስ አበባ ለረቡዕ መስከረም 9 ቀን 2010 ዓ.ም. የተጠራ ምንም ዓይነት ሠልፍ አለመኖሩን አስታውቋል። መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ አንዳንድ ዓለም አቀፍ ተቋማት በአዲስ አበባ የተጠራ ሠልፍ አለ በማለት ያወጡት መረጃ ሙሉ በሙሉ #የተሳሳተም ነው ብሏል።
©ሪፖርተር