TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#አብዛን_ንግድ20 ሺ ሰው

"እኔም በአካል ቦታው ድረስ ሄጄ ነበር በፖሊስ ተይዞ ሄደ ብለውናል። በሩ ላይ #ፖሊስ ነበር።" #David

ይህን መልዕክት የላከልኝ የቤተሰባችን አባል የሆነ ወጣት የዩኒቨርሲቲ ምርቁ ነው። ከ30 ደቂቃ በፊት ቦታው ላይ ነበር። ወጣቱ ከክፍለ ሀገር ድረስ ይህን የስራ እድል አገኛለሁ ብሎ ነው የመጣው። አሁን ግን ወደመጣበት ሊመለስ ነው።

ብዙ ሰዎች ማስታወቂያውን #የሰሙት "ቃና ቴሌቪዥን" ከተባለው የሚዲያ ተቋም እንደሆነ ነግረውናል። የቴሌቪዥን ጣቢያው ስለሁኔታው አጣርቶ ለህዝብ ማሳወቅ ያለበትን ሊያሳውቅ ይገባል።

20 ሺ ሰው ፈልጋለሁ ያለው ድርጅት ህጋዊ ነው? ስለድርጅቱ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እሞክራለሁ። የድርጅቱ ተወካዮችም ስልካቸው ከሰራልኝ ስለጉዳዩ ጠይቄ የሚሉኝን ነግራችኃለሁ።

ምላሽ ለሚሰጥ አካል በራችን ሁሌም ክፍት ነው @tsegabwolde

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አብዛን_ንግድ_ስራ

"ቦታው በፖሊስ ተከቧል ሰውየውም ታስሯል ምንም አይነት ምዝገባ የለም ማንም እንዳይመጣም ብለዋል።" #emy

20,000 ሰው እንፈልጋለን ለተባለው የስራ ማስታወቂያ ለመመዝገብ ወደ ስፍራው የሄዱት የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ይህን ፎቶ አንስተው ልከዋል...

"...በድርጅታችን ቢሮ ቁጥር 560 ላይ ተከራይቶ ይሰራ የነበረው ለጊዜው ምዝገባው እንደሌለ በትህትና እንገልፃለን!"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አብዛን_ንግድ

"ዛሬ ከጠዋት እስከማታ ድረስ የነበረውን ሁኔታ ስንከታተል ነው የዋልነው የስራው ባለቤት ዕድሜው ከ 24-26 የሚገመት በጣም ወጣት የሚባል አይነት ነው ዛሬ ከቀኑ 10:00 ሰዓት አካባቢ በፖሊስ ታጅቦ ልደታ በሚገኘው የፍሊንትስቶንስ ህንፃ ወደተከራየው ቢሮ መጥቶ ነበር ወደ 1400 ያክል ተመዝጋቢ እንደነበር እና ወደ 3.4 ሚሊዮን ብር አካባቢ እንደሰበሰበ ሰምተናል አንዲት አብራው የምዝገባውን ስራ የምትሰራ ፀሀፊም ታስራ መጥታ ነበር የቅጥር ውል ብቻ እንዳላት እና ሌላውን ነገር እንደማታውቅ ተናግራለች ብዙ ግርግር ነበር ፖሊሶችም ክፍያውን በባንክ የፈፀመ እና ሲፒኦ እጁ ላይ የሚገኝ ተመዝጋቢ ፖሊስ ጣቢያ መጥቶ እንዲያመለክት እና ገንዘቡ ተመላሽ የሚሆንበትን መንገድ እንደሚፈልጉ አስረድተዋል!" Abi ነኝ~የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባል

🏷20 ሺ ሰው ይፈለግበታል ለተባለው ለዚህ የስራ ቅጥር ማስታወቂያ ከአዲስ አበባ ራቅ ካሉ ከተሞች /ከጎንደር እና ከነቀምቴ ሳይቀር/ ወጣቶች ለማመልከት መጥተው ነበር።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አብዛን_ንግድ

20 ሺ ሠራተኞችን #ለመቅጠር ገንዘብ እያስከፈለ በመመዝገብ ላይ የነበረው ግለሰብ ከእነ ጓደኞቹ ታስሮ ፍርድ ቤት ቀርቧል። አብዛን የተሰኘ የንግድ ሥራ ድርጅት ባለቤት መሆኑ የተገለጸ ግለሰብ 20 ሺሕ ሠራተኞችን ለመቅጠር በነፍስ ወከፍ 2,477 ብር በማስከፈል፣ በርካታ ወጣቶችን በመመዝገብ ላይ እያለ ከጓደኞቹ ጋር በቁጥጥር ሥር ውሎ ታሰረ፡፡ግለሰቡ አቶ አብርሃም ዘሪሁን የሚባል ሲሆን፣ የሥራ ማስታወቂያውን በቃና ቴሌቪዥንና በሌሎች ሚዲያዎች በማስተዋወቅ፣ ከሐምሌ 1 እስከ 18 ቀን 2011 ዓ.ም. ድረስ እያንዳንዱ ተመዘጋቢ የ2,477 ብር ሲፒኦ አሠርቶ እንዲመዘገብ ጥሪ ማድረጉ ታውቋል፡፡
.
.
ተጠርጣሪዎቹ ሐሰተኛ ሰነድ በመጠቀምና በተለይ የ2011 ዓ.ም. ተመራቂ ወጣቶችን በማማለል ከሦስት ሺሕ ብር በላይ ደመወዝ እንደሚከፍል፣ #ሐሰተኛ ማስታወቂያ በማስነገር ከእያንዳንዱ ተመዝጋቢ 2,744 ብር መቀበላቸውን ፖሊስ ገልጿል፡፡ ስለማስታወቂያውና ስለሥራው የተጠራጠረው ፖሊስ ከአሥር ተመዝጋቢዎች ጋር ባደረገው ቃለ መጠይቅ ጥርጣሬውን ይበልጥ ስላጎላው፣ ግለሰቦቹን ሐምሌ 13 ቀን 2011 ዓ.ም. በቁጥጥር ሥር አውሎ እየመረመረ መሆኑንና ለተጨማሪ ምርመራ 14 ቀናት እንዲፈቀድለት ጠይቋል፡፡

ተጨማሪ የንብቡ👇
https://telegra.ph/ABZAN-07-24

Via #reporter
@tsegabwolde @tikvahethiopia