TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከሰጡት መግለጫ የነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች:-

• ኢትዮጵያ ውስጥ ሁሉም #አሸናፊ የሚሆንበት አውድ እንዲፈጠር እንፈልጋለን፡፡

• የአሸናፊዎች ስብስብ አሸናፊ አገር ይፈጥራል፡፡

• አንዱ አሸናፊ አንዱ #ተሸናፊ የሚሆንበት የፖለቲካ ስርዓት ኢትዮጵያ ውስጥ አያስፈልገንም ይበቃናል፡፡

• ባንድራ የሀሳብ መግለጫ፣ የፓርቲዎች አርማ ነው፤ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ የሚፈልገው ከሆነ ባንድራ በውይይት ሊቀየር ይችላል፣ በጉልበት ማስቀየር የሚፈልግ ካለ እሱ ጉልበት እንዳለው ሌለውን ጉልበት ስላለው አያዋጠም፡፡

• የትኛውም ጫፍ የፖለቲካ አመለካከት ያለው የፖለቲካ ኃይል ካለ የኢትዮጵያ ህዝብ መቀበል አለበት፣ የማግለል ፖለቲካ መቆም አለበት፡፡

• ወንድም ወንድሙን ገድሉ ማሸነፍ አይችልም፤ በሀሳብ ግን አሸናፊ መሆን ይቻላል፡፡

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሜቴክ‼️

ሰሞኑን ከታሰሩት የሜቴክ እና ደኅንነት አመራሮች እና አባላት መካከል የተወሰኑት ሥም ዝርዝር ይፋ ወጥቷል፡፡ ከእነዚህም መካከል፦

🔹የሰሜን ጎንደር ደኅንነት ሃላፊ አቶ #አሸናፊ_ተስፋሁን

🔹እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የአማራ ክልል ደኅንነት ሃላፊ የነበረው አቶ #ነጋ_ኑሩ

🔹በሱማሌ ክልል የደኅንነት ሥራዎችን ሲያስተባብር የነበረው አቶ #ቢኒያም_ማሙሸት

🔹በደኅንነቱ ሥር የግንቦት 7 ክትትል ዴስክ ሃላፊ የነበረው አቶ #ሸዊት_በላይ

🔹የሐረሬ ክልል ደኅንነት ሃላፊ የነበረው አቶ #ተከተል (የአባት ሥም አልተጠቀሰም)፣

🔹የክትትል መምሪያ ሃላፊ እና የአፋኝ ቡድን ቁልፍ አባል የነበረው አቶ #አጽብሃ_ግደይ እና

🔹የጸረ-ስለላ መምሪያ ሃላፊ የነበረው አቶ #ሳሙዔል (የአባት ሥም አልተጠቀሰም) ይገኙበታል፡፡

በተያያዘ ዜና...

በሙስና ተከሰው የታሰሩት የሜቴክ እና ደኅንነትና መረጃ አመራሮች ዛሬ ከሰዓት በኋላ ፍርድ ቤት #ቀርበዋል። ተጠርጣሪዎቹ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ ልደታ ምድብ 10ኛ ወንጀል ችሎት ነው የቀረቡት፡፡ ፍርድ ቤት ከቀረቡት ውስጥ 36ቱ በሰብዓዊ መብት ጥሰት የተጠረጠሩ ሲሆኑ በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩት ደሞ 27 ናቸው፡፡ አቃቤ ሕግ በሁለቱም ምድብ ተጠርጣሪዎች ላይ የጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው ጠይቋል፡፡

ምንጭ፦ ዋዜማ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አውሮፕላን ተከሰከሰ👆

በጅማ ዞን ኦሞ ቤየም ወረዳ በአቢሲኒያ ፍላይት መለማጀማ አውሮፕላን ላይ #መከስከስ አደጋ መድረሱ ተገለፀ። የአቢሲኒያ ፍላይት ሰርቪስ የፕሮጀክት ማናጀር አቶ #አሸናፊ_ፀጋዬ ለfbc እንዳስታወቁት፥ አደጋው በዛሬው እለት ጠዋት ላይ ጎና ቤየም በሚባል ቀበሌ አሰንዳቦ አካባቢ ነው የደረሰው።

በአውሮፕላኑ ላይ የመከስከስ አደጋው የደረሰው አንድ ተለማማጅ የአውሮፕላን አብራሪ በማብረር ላይ እያለ መሆኑንም አስታውቀዋል። የመከስከስ አደጋው የደረሰበት አውሮፕላን “C 172” ሞዴል ሲሆን፥ አራት መቀመጫዎች ያሉት ነው ብለዋል አቶ አሸናፊ

በአሁኑ ወቅትም የአደጋውን የጉዳት መጠን እና #መንስኤ ለማጣራት የባለሙያዎች ቡድን ወደ ስፍራው መላኩንም አስታውቀዋል። ወደ ስፍራው የተጓዘው የባለሙያዎች ቡድን ወስጥም የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን የፍለጋ እና የነብስ አድን ሰራተኞች እና የአቢሲኒያ ፍላይት የደህንነት አባላት የተካተቱበት ነው።

የአደጋው መንስኤም እስካሁን አለመታወቁን እና በመጣራት ላይ መሆኑንም የአቢሲኒያ ፍላይት ሰርቪስ የፕሮጀክት ማናጀር አቶ አሸናፊ ፀጋዬ ተናግረዋል።

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 በህገወጥ መንገድ መሬት በመውረር ግንባታ ያከናወኑ የተገኙ የፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር ዋሉ።

fbc አረጋግጫለሁ እንዳለው በቁጥጥር ስር ከዋሉት የፖሊስ አባላት መካከል ዋና ሳጅን #ዘሪሁን_ወልዴ፣ ረዳት ሳጅን #አሸናፊ_ካንኮ፣ ረዳት ሳጅን #አግማስ_አንዱዓለም እና ረዳት ሳጅን #ሀብተማርያም_ጓንጉል ይገኙበታል።

በቀጣይነትም በህገወጥ የመሬት ወረራ ላይ ተሳትፈው የተገኙ የመንግስት አካላት፣ ባለሃብቶች እና ግለሰቦች ላይ የከተማ አስተዳደሩ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድም ተገልጿል።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሻሸመኔ⬆️"ዛሬ ሻሸመኔ ከተማ ላይ በከተማው መስተዳደር በጎ ፍቃደኞች ወጣቶች በጋራ በመሆን ለከተማው አቅመ ደካማ ለሆኑ ቤተሰቦች የተለያዩ በርካታ ቁሳቁስ እና አልባሳት የተለያዩ የከተማው የስራ ክፍል ሀላፊዎች በተገኙበት ተሰጥቷል።" #አሸናፊ/TIKVAH-ETH

@tsegabwolde @tikvahethiopia