TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሜቴክ⁉️

ካለፉት ሳምንታት ወዲህ የተረዳነውና ራሳችንን ይዘን እንድንገረም ያደረገን በሜቴክ በኩል ሲዘራ የሰነበተው ገንዘብ ጉዳይ ነው፡፡ ይኸች #ድሃ ሃገር፣ ተለቅታም፣ ተበድራም፣ ሸጣም ያገኘችው የውጭ ምንዛሬ ሲመዠረጥ መክረሙ ብዙ ጥያቄዎችን የሚቀሰቅስ መሆኑ የታወቀ ነው፡፡

ከ2 ቢሊዮን ዶላር በላይ እንደዋዛ ሲቀር ተመልካች የለም ነበር ወይ? ኧረ ለመሆኑ፣ ቢሊየኖች የገበያ ሥርዓትን በተከተለ መንገድ ሳይሆን እንደተፈለገ ግዥ ላይ ሲውል የፋይናንስ ሥርዓቱንስ አያወላግደውም ወይ? የሚሉና ተያያዥ ጥያቄዎች ይነሳሉ፡፡

ሸገር FM 102.1 (ንጋቱ ሙሉ) እነዚህንና ሌሎችንም ጥያቄዎች ይዞ ከምጣኔ ሐብት ባለሙያዎች ጋር ቆይታ አድርጓል።

ከላይ ያለውን ፋይል ከፍታችሁ አድምጡ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኧረ እንንቃ‼️

በዚህች #ድሃ በሆነች ሀገር ላይ እየኖርን #የጎደለንን ለሟሟላት ከመጣር ይልቅ ያለንን #በማጉደል ላይ ተጠምደናል። ምቀኝነት፣ ተንኮል፣ ክፋት፣ መጠላለፍ፣ ማጥላላት፣ መከፋፈል፣ መባላት፣ ለጦርነት መንደርደር፣ ሰው አለማክበር የማንነታችን መገለጫ ሊሆን አይገባም። ያለችን አንድ ሀገር ናት ሰርተን እንቀይራት!! እንዋደድ፤ እንከባበር፤ መጥፎ ስራዎችን እየፀየፍ፤ አንድ የሚያደርገን #ሰውነት ነው።

#TikvahEthiopia #ቲክቫህኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia