TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ቡራዩ⬆️

የቡራዩ ከተማ ነዋሪዎች በከተማዋ በንፁሃን ነዋሪዎች ላይ የተፈፀመውን ድርጊት #በማውገዝ ዛሬ ሰልፍ አካሂደዋል።

የከተማዋን ነዋሪ የማፈናቀሉ ተግባር የቡራዩን ከተማ #ወጣት በአጠቃላይ ነዋሪውን አይወክልም ብለዋል።

ሰለፍኞቹ ከተማዋ የሁሉም የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦች ናት በማለትም ተፈናቃዮቹ ወደ ከተማቸው #እንዲመለሱ ጥሪ አቅርበዋል።

የተፈናቀሉ ወገኖቻቸውንም መልሶ #ለማቋቋም ዝግጁ መሆናቸውንም ነው ያስታወቁት።

በተጨማሪም ሰልፈኞቹ በአዲስ አበባ በኦሮሞ ተወላጆች ላይ ጥቃት የማድረስ ተግባርን እንደሚያወገዙ በመግለፅ መንግስት ድርጊቱን እንዲያስቆም ጠይቀዋል።

©ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አብዴፓ‼️

የአፋር ብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አብዴፓ) በቅርብ በሚያካሄደው ድርጅታዊ ኮንፊረንስና ጉባዔ በአገሪቱ የተጀመረውን የለውጥ እንቅስቃሴን በክልሉ  ለማስቀጠል ብቃት ያላቸው #ወጣት አመራሮችን እንደሚመርጥ ተገለጸ።

ፓርቲው በክልሉ የተከሰተውን ችግር አስመልክቶ ላለፉት ሶሰት ቀናት በአዲስ አበባ ያካሄደውን ጉባኤ መሰረት በማድረግ  ዛሬ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጋር ውይይት አካሂደዋል።

በዚህም ለለፉት ሶስት ቀናት ባደረጉት ግምገማ የለዩትን ችግሮችና ያስቀመጡትን የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅርበዋል።

በሚኒስትር ማዕረግ የኢህአዴግ ፖለቲካ ፓርቲዎች፣ አጋር ድርጅቶችና የሲቪል ማህበራት አስተባባሪ አቶ ፍቃዱ ተሰማ ከውይይቱ በኋላ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንዳሉት  ፓርቲውና የክልሉ መንግስት ከፍተኛ የአመራር ውድቀት እንዳጋጠመው በግምገማ ተለይቷል።

ከዚህም በተጨማሪ በአመራሩ መካከል ተወያይቶ መፍትሄ ከማምጣት ይልቅ ከፍተኛ የሆነ የስልጣን ሽኩቻ፣ የክልሉን ሃብት ለህዝብ ጥቅም ከማዋል ይልቅ በኔትዎርክ ተደራጅቶ ለራስ ጥቅም የማዋል ችግርም መኖሩን ነው የገለጹት።

ለዚህም በጨውና ሌሎች በክልሉ ባሉት ማዕድናት ላይ የሚሰራ የማጭበርበር ስራም ጎልቶ መታየቱን በማከል።

የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችም በክልሉ አስተዳደር ላይ እንደሚታይም ተገምግሟል ብለዋል አቶ ፍቃዱ።

ከነዚህ ችግሮች ለመላቀቅም የተከሰቱትን ችግሮች ማስተካከል የሚችሉ አሰራሮች መዘርጋትና የአመራር ለውጥ ማድረግም እንደ መፍትሄ ተቀምጠዋል።

የክልሉ ፕሬዝዳንት ሃጅ ስዩም አወል በበኩላቸው እሳቸውን ጨምሮ በድርጀቱ ለረዥም ጊዜ ያገለገሉ ከፍተኛ አመራሮች ስልጣን ለቀው ወጣቶች እንደሚተኩ ተናግረዋል።

ይህን ለማድረግም በቅርቡ የአባላት ኮንፊረንስ እንደሚያደረጉና የፊታችን ህዳር 24 በሚካሄደው ድርጅታዊ ጉባዔም የክልሉን ህዝብ ፍላጎት የሚመጥን ለውጥ የሚያመጣ ውሳኔዎች ይታላለፋሉ ብለዋል።

እስከዚያው ደግሞ ህብረተሰቡ አካባቢውን እየጠበቀ በትዕግስት እንዲጠብቃቸው ጥሪ አስተላልፈዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድም ፓርቲው አጠቃላይ ሪፎርሙንና የአመራር መተካካትን ሲያካሄዱ ከግልኝነትና ቡድናዊ ስሜት ጸድቶ የህዝቡን ጥቅም ባማከለ መልኩ እንዲሆን አሳስበዋል።

የፌዴራል መንግስቱም አስፈላጊውን ሁሉ እገዛ እንደሚያደርግ ቃል ገብቷል።

ምንጭ፦ ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጌዴኦ በጌዴኦ ዞን ለሚገኙ ተፈናቃይ ወገኖች በእናተ በTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት በኩል የተሰባሰበው ገንዘብ ከ95 ሺ ብር በላይ መሆኑ ትላንት አሳውቀን ነበር። በዛሬው ዕለት በነበረው የኔትዎርክ ችግር ምክንያት ምን ያህል እንደደረሰ ሳንገልፅላችሁ ውለናል። በነገው ዕለት የምዕራፍ 1 ማጠቃለያ ይሆናል። በመጀመሪያው ምዕራፍ የሚገኘውን 100,000 ብር በምን ላይ መዋል እንዳለበት፤ በምን ላይ እንደዋለ እና በአግባቡ ወገኖቻችን ጋር እንደደረሰ #በማስረጃዎች አስደግፌ ይፋ አደርጋለሁ።

አሁንም ድጋፍ ማድረግ የምትፈልጉ፦

#ዶክተር_መላኩ #ወጣት_ሜላት
Account number(CBE): 1000277462439

@tsegabwolde @tikvahethiopia
122,383 ብር --- የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት እያደረጋችሁት ያለው ድጋፍ ቀጥሏል። በየሰዓቱ መጠኑ የሚጨምር ስለሆነ ያለውን እንቅስቃሴ በፍጥነት አሳውቃችኃለሁ። #ጌዴኦ #ቲክቫህኢትዮጵያ

#ዶክተር_መላኩ #ወጣት_ሜላት
Account number(CBE): 1000277462439

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
የ25 ዓመቱ ወጣት የፖለቲካ ድርጅት አመራር...

#ወጣት_ቢሊሱማ_ብርሃኑ_አራርሳ
#Mekelle #AddisAbaba

• " ክልከላው ላይ የለንበትም ፤ መፍትሄ እንዲሰጥ ከፌደራል መንግስት እየተነጋገርን ነው " - የትግራይ ክልል አስተዳዳሪዎች

• " ስለተባለው ነገር መረጃ የለኝም። እኛ የምናውቀው ነገር የለም። ... ለአየር መንገዱ ከመንግሥት በኩልም ቢሆን ምንም አይነት ክልከላን የሚመለከት መመሪያ አልተሰጠውም " - የኢትዮጵያ አየር መንገድ

• " ዝርዝሩን ለማወቅ እናጣራለን " - የፌዴራል ፖሊስ

ካለፉት ሶስት ቀናት ወዲህ ከመቐለ ወደ አዲስ አበባ በሚደረግ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመንገደኞች በረራ ላይ በተለይም #ወጣት መንገደኞች እንዳይጓዙ ክልከላ ስለመኖሩ መንገደኞች እየገለፁ ይገኛሉ።

ትናንት ታህሳስ 30/2015 ዓ/ም ከመቐለ ወደ አዲስ አበባ ለመጓዝ የአየር ቲኬት ቆርጠው አሉላ አባነጋ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት የተገኙት #በርካታ_ወጣቶች ጉዟቸው መሰረዙ ተሰምቷል።

መንገደኞች እንደሚሉት ከሆነ ክልከላው ከ16 ዓመት በላይ እና ከ64 ዓመት እድሜ በታች በተለይ ደግሞ ወጣቶችን ትኩረት ያደረገ ነው።

አንድ ቃሉን ለቢቢሲ የሰጠ መንገደኛ (የአዲስ አበባ ነዋሪ) ፤ " የልጆች እናት፣ የህክምና ሪፈር ያላቸው እና በእድሜ የገፉት ግን መሄድ እንደሚችሉ ነው የፌደራል ፖሊስ አባላቱ የነገሩን " ብሏል።

ይኸው መንገደኛ ፤ አዲስ አበባ ከተማ እንደሚኖር ፤ መታወቂያውም የአዲስ አበባ እንደሆነ ወደ አዲስ አበባ ለመመለስ እንደሄደና አስፈላጊውን መረጃ እንዳረበ ነገር ግን ሊቀበሉት እንዳልቻሉ አመልክቷል።

የአየር መንገዱ ሠራተኞች ክልከላው ከቁጥጥራቸው ውጪ እንደሆነ ነግረውናልም ብሏል።

አንድ መንገደኛ ደግሞ አዲስ አበባ የሚያስተዳድረው ተቋም መኖሩን የሚገልፅ መረጃ ካሳየ በኃላ በረራ እንደተፈቀደለት ለቢቢሲ ተናግሯል።

ክልከላው ከመቐለ በተጨማሪም #በሽረ ኤርፖርትም ስለመኖሩ ተገልጿል።

ጉዳዩን በተመለከተ ማን ምን አለ ?

የትግራይ ክልልን እያስተዳደሩ ያሉ አካላት ፤ ለክልሉ ቴሌቪዥን ጣቢያ (ትግራይ ቴሌቪዥን) በሰጡት ቃል በዚህ ክልከላ እንደሌሉበት እና የክልከላው እርምጃ በፌደራል መንግስት የተወሰደ እንደሆነ ገልፀዋል።

በጉዳዩ ዙርያ መፍትሄ እንዲሰጥ ከፌደራል መንግስት እየተነጋገረ መሆኑን አሳውቋል።

#የኢትዮጵያ_አየር_መንገድ የንግድ ዘርፍ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ለማ ያደቻ (ለቢቢሲ አማርኛ ክፍል) ፦

" ስለተባለው ነገር መረጃ የለኝም። እኛ የምናውቀው ነገር የለም።

እንደምታውቁት የኢትዮጵያ አየር መንገድ የእድሜና ጾታ ክልከላ የለውም። ምክንያቱም በሕግ እና በሥርዓት ነው የሚተዳደረው። እስከ ዛሬ እንዲህ አይነት ክልከላ የለንም። ወደ ድረ ገጻችን ብትገቡም ምንም አይነት ክልከላ እንደሌለ ታያላችሁ።

በተጨማሪም ለአየር መንገዱ ከመንግሥት በኩልም ቢሆን ምንም አይነት ክልከላን የሚመለከት መመሪያ አልተሰጠውም።

ምናልባት #የአካባቢው_መመዘኛ_ወጥቶ እንደሆነ የክልሉ ባለሥልጣናትን ብትጠይቁ የሚሻል ይመስለኛል።

በእኛ በኩል ግን እስካሁን የደረሰን ምንም አይነት መረጃ የለም። ከመንግሥት የተሰጠ ትዕዛዝም የለም። "

የፌደራል ፖሊስ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጄይላን አብዲ (ለቢቢሲ አማርኛ ክፍል) ፦

" መረጃው የለኝም።

ተጓዦች በእድሜ ተለይተው በአውሮፕላን እንዳይጓዙ ተከልክለዋል የሚለውን መረጃ አሁን ከእናንተ ነው የምሰማው።

ዝርዝሩን ለማወቅ እናጣራለን። "

በጦርነት ምክንያት ለረጅም ወራት ያህል ተቋርጦ የነበረው ወደ መቐለ እና ሽረ እንደስላሴ የሚደረገው የመንገደኞች በረራ በቅርቡ ዳግም መጀመሩ የሚዘነጋ አይደለም።

@tikvahethiopia
#EOTC

በአዲስ አበባ ከተማ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ኦርቶዶክሳዊ #ወጣት የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት ዋዜማን በቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ካቴድራል በዝማሬ እና በፀሎት አክብሮ ውሏል።

" ጃንደረባው ትውልድ " በተሰኘ ማህበር አዘጋጅነት በተዘጋጀ " የአእላፋት ዝማሬ " የሚል ስያሜ በተሰጠው መርሃ ግብር እጅግ በጣም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ምእመን አብዛኛው #ወጣት በቤተክርስቲያን ተገኝቶ የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት ዋዜማን በልዩ #በሃማኖታዊ ስነስርዓት ተቀብሏል።

በመርሐ ግብሩ ላይ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ፣ ብፁዕ አቡነ አብርሃም  የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ፣ የባሕር ዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና ሌሎች ብፁዓን አባቶች ተገኝተው ነበር።

" የጃንደረባው ትውልድ ማኅበር " በቅርቡ በመንበረ ፓተርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የማኅበራት ምዝገባ ክትትልና ቁጥጥር መምሪያ የእውቅና ምሥክር ወረቀት ማግኘቱ ተነግሯል።

ፎቶ፦ TMC / ከማህበራዊ ሚዲያ

@tikvahethiopia