TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ኦነግ⬇️

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀ-መንበር አቶ #ዳዉድ_ኢብሳ በቅርቡ ከዋልታ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ኮርፖሬት ጋር ቃለ-ምልልስ አድርገዋል። ቃለ ምልልሱን መሰረት አድርጎ ዘገባ የሰራዉ ዋልታም «ኦነግ ወደ አገር ቤት ሲመለስ ትጥቁን ፈቶ ነዉ የገባዉ የሚለዉን መረጃ» አቶ ዳዉድ ኢብሳ ማስተባበላቸዉን ገልፀዋል። አቶ ዳዉድ «ትጥቅ መፍታት የሚባል በጣም ሴንሴትቭ [ጥንቃቄ የሚያስፈልገዉ] ጥያቄ ነዉ። ትጥቅ ፈታ አይባልም። ትጥቅ ፈታን፣ ፈቱ መባልም አንፈልግም። ምክንያቱም ከዚህ ጋር ተያይዞ ያለዉ ምንድነዉ፣ አንዱ ትጥቅ የሚፈታ፣ አንዱ ትጥቅ የሚያስፈታ ይመስላል። አይደለም፣ እንደሱ አይደለም የመጣነዉ። በአጠቃላይ አገሪቱ በሰላም እንድትጠበቅ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ያለዉ ሚና፣ በዚህ ዉስጥ እንዴት እንደሚሳተፍ፣ በዚህ ዉስጥ የኛ ሚና ምን እንደሚሆን፣ በዚህ ነዉ የተሰማማነዉ»

ይህ በተንቀሳቃሽ ምስል የወጣ ሲሆን በዋልታ የፌስቡክ ገፅ ላይ የወጣዉ ደግሞ እንደሚከተለዉ ይነበባል፣ «ኦነግ ወደ ሀገር ቤት የገባው ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ትጥቁን ፈትቶ #በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ነው ተብሎ የሚነገረው መሰረት ቢስ ወሬ ነው። እኛ ትጥቅ እንድንፈታ የተስማማንበት ስምምነት የለም። የታጠቀው አካል ትጥቅ ይዞ እያለ እኛ ትጥቅ የምንፈታበት ምክንያት አይኖርም።»

ይህ በፌስቡክ ገፅ ላይ የወጣዉ ከተንቀሳቃሽ ምስል ይዘት ዉጭ በተሳሳተ ትርጉም ከአውድ ዉጭ የተወሰደዉና ከፍተኛ አከራከሪ ነጥብ መሆኑን የኦነግ ስራ አስፈጻም ኮሚቴ አባል፣ የልዑክ መሪ እንድሁም የድርድሩ ኮሚቴ አባል አቶ #ኢብሳ_ናጋዎ ለDW ተናግረዋል። በተንቀሳቃሽ ምስሉ ላይ የኦነግ ሊቀ-መንበር አቶ ዳዉድ ያሉት አንደኛ ወደ አጋር ቤት እንድንመጣ በሰላማዊ መንገድ ለመታገል፣ እንዲሁም ደግሞ ባለፈዉ ጊዜ በጦርነት ላይ ስለነበረን ጦርነቱ ቆሞ፤ የትጥቅ ጥያቄ እንዳከተመ ብዙ ጊዜ ተናግረናል፣ በዚህ ሒደት ዉስጥ የኦነግ ሰራዊት ደግሞ በተመክሮ አማካኝነት በአገሪቱ ዉስጥ ከፀጥታ ሃይሎች ጋር ሆኖ ሊጫወት የምያስችል ምና የቀየሰ ነዉ፣ ሲሉ አቶ ኢብሳ አብራርተዋል። ከዚህ ዉጭ ግን አሁን በፌስቡክ ላይ የኦነግ ሰራዊት «ትጥቅ ፈቶ ይበተናል፣ የለም መታጠቅ አለበት የምለዉ ነገር አቅጣጫዉን የሳተ ዉዥንብር ነዉ» ስሉ የድርድሩ ኮሚቴ አባል አቶ ኢብሳ ገልፀዋል።

ምንጭ፦ ዶቼ ቨለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia