TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አፍሪካ ኢኖቬሽን ሳምንት🔝

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከኢኖቬሽን ቢዝነስ አክስለሬሽን (IBA Ethiopia) ጋር በመተባበር የአፍሪካ የኢኖቬሽን ሳምንት ከጥቅምት 17/2012 እስከ ጥቅምት 21/2012 ለማካሄድ ወስነዋል።

የኤግዚብሺኑ ዋና ዓላማ ወጣቶችን ብሎም ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደረጉ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ማስተዋወቅና ወደ ስራ እንዲገቡ
አስቻይ ሁኔታዎችን መፍጠር ነው፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር ኢንጂ.) የኢኖቬሽን ሳምንቱ መዘጋጀት ሚኒስቴሩ ለያዘው የቴክኖሎጂ የስራ ፈጠራ ስራ አጋዥ ይሆናል ብለዋል፡፡

በተለይ ለሴቶች ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ የአይ ቤ ኢትዮጵያ ዳይሬክተር አቶ አሸናፊ ሙሉጌታ ተናግረዋል፡፡

ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ #ኃይለማሪያም_ደሳለኝ በዚህ ስራ ተሳታፊ ናቸው።

አቶ ሃይለማርያም የስራ አጥ ቁጥር መበራከት እንደሚያሳስባቸው ገልፀው ይህንን ችግር ለመቅረፍ ቴክኖሎጂ ማበልፀግ ላይ ትኩረት ሰጥቶ መሰራት እንደሚገባ ጠቁመዋል።

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በናይጄሪያ #ሰላማዊ_ምርጫ መካሄዱን የአፍሪካ ህብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን መሪ አቶ #ኃይለማሪያም_ደሳለኝ አስታወቁ፡፡ ባሳለፍነው ቅዳሜ በናይጄሪያ የተካሄደው ምርጫ ሰላማዊ እንደ ነበር የአፍካ ህብረት የናይጀሪያ ምርጫ ታዛቢ ቡድን መግለጹ ተነግሯል፡፡ ከምርጫ #ግብዓቶች ጋር በተያያዘ ለአንድ ሳምንት በተራዘመውና በሳለፍነው ቅዳሜ በተካሄደው የናይጄሪያ ምረጫ ላይ አስተያየቱን በመስጠት የህብረቱ ታዛቢ ቡድን የመጀመሪያው ነው ተብሏል፡፡

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia