THIKVAH-ETHIOPIA
3.95K subscribers
6.58K photos
218 videos
39 files
721 links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
THIKVAH-ETHIOPIA
#ፋይዳ #NationalID " ከፍርድ ቤት እና ከብሔራዊ ደኅንነት ጥያቄው ከዛ እስካልመጣ [የግል መረጃ] ለመንግስት የሥራ አስፈጻሚ አይሰጥም " - አቶ ዮዳሄ አርአያሥላሴ ኢትዮጵያ የዲጂታል መታወቂያ ፕሮግራምን በይፋ ካስተዋወቀችበት ጀምሮ እስከ አሁን 12 ሚሊዮን የሚሆኑ ዜጎች ተመዝግበዋል፤ እስካሁንም ይህንን አገልግሎት ከ50 በላይ ከሆኑ አገልግሎቶች ጋር የማስተሳሰር ሥራም ተሰርቷል። ይህ ፕሮጀክት…
#ፋይዳ #NationalID

" የትምህርት እና የጤና መረጃን በፋይዳ ለማረጋገጥ የሚያስችል የዋሌት ሥርዓት እየሰራን ነው " - ራሄል አብርሃም  የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ምክትል አስተባባሪ

° " በምዝገባ ሥርዓቱ ውስጥ የግል ተቋማት በቅርቡ ይቀላቀላሉ ! "

ስለ ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች በተሰበሰቡ ጥያቄዎች ላይ የተቋሙ ምክትል አስተባባሪ ራሄል ምላሽ ሰጥተዋል። በዋናነትም ከትግበራና አፈጻጸም ላይ ተያይዞ ያሉ ጥያቄዎች ቀርበዋል።

ምክትል አስተባባሪዋ፥ በዚህ ወቅት ለቀረቡት ጥያቄዎች ምላሽ በሰጡበት ወቅት እንደገለጹት በቀጣዮቹ አምስት ወራት ወደ 30 ሚሊዮን ዜጎችን ለመመዝገብ መታቀዱን ጠቁመዋል።

ለዚህም አሁን ላይ በአጋርነት ከሚሰሩት ኢትዮ ፖስት እና ኢትዮ ቴሌኮም በተጨማሪ፥ የግል ተቋማትን ወደ ምዝገባ ሥርዓቱ ለማስገባት ጨረታ መውጣቱን ገልጸው፤ ለዚሁ የሚያስፈልጉ የቁሳቁሶች ግዢም በሂደት ላይ መሆኑን ተናግረዋል።

የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ በቅርቡ ዜጎች የተለያዩ አገልግሎት የሚያገኙበትን የራሱን የሞባይል መተግበሪያ በ Android እንዲሁም  IOS አስተዋውቋል። እንደ ም/አስተባባሪዋ ከሆነ በቅርቡ የዋሌት ሥርዓትም እንደሚዘረጋ ጠቁመዋል።

የአዲሱ የፋይዳ የዋሌት ሥርዓት ምንድን ነው ?

አዲሱ የዋሌት ሥርዓት "የትምህርት እና የጤና መረጃህን ከፋይዳ ጋር በማገናኘትና በማረጋገጥ በስልክህ ይዘህ እንድትንቀሳቀስ ያስችልኃል" ሲሉ ገልጸዋል።

"ስኮላርሺፕ የሚጠቀሙ ተማሪዎች አንድን የትምህርት ዶክመንት ለማረጋገጥ በተማሩበት ትምህርት ቤት ተገኝተው በመኃተም ወይም ትምህርት ቤታቸው ለሚያመለክቱበት ት/ቤት ማስላክ ነበር። ይህንን አላስፈላጊ መጉላላት የሚያስቀር ዋሌት እየሰራን ነው።" ራሄል አብርሃም

የዋሌት ሥርዓቱ አላስፈላጊ መረጃ እንዳይሰጥ ጭምር ያግዛል ያሉት ምክትል አስተባባሪዋ "አላስፈላጊ መረጃም እንዳይሰጥ ይጠቅማል፤ እድሜህን ብቻ የሚፈልግ ተቋም እድሜህን ብቻ በፋይዳ በኩል Verifiable Credentials (VCs) በመፍጠር ለዛ ተቋም መላክ ትችላለህ፥ ያም ተቋም  ያንን አይቶ አገልግሎት የሚሰጥበትን እየሰራን ነው" ሲሉ ገልጸዋል።

"ፋይዳ ላይ ያለው ፎቶዬ ተበላሽቷል እንዴት መቀየር እችላለሁ?"

ይህ ጥያቄ ከበርካታ ቤተሰቦቻችን የተነሳ ጥያቄ ሆኖ አግኝተነዋል። ይህንንም አስመልክቶ የፋይዳ መታወቂያ ላይ ያሉ መረጃዎችን እንዴት መቀየር እንችላለን ብለን ለምክትል አስተባባሪዋ ጥያቄውን አቅርበንላቸዋል።

በምዝገባ ወቅት የሚፈጠሩ የቃላት ግድፈት፤  የዶክመንት አለመገናኘት እና መሰል ስህተቶች በፋይዳ ዌብሳይት ላይ በመግባት እና ማስተካከያ በመጠየቅ እንዲስተካከል የሚያስችል አሰራር አሁን ላይ መኖሩን ገልጸዋል።

ሆኖም የፎቶ እንዲሁም ማንነት ላይ ለውጥ የሚያመጡ የባዮሜትሪክ መረጃዎች ለውጥ በተመለከተ የህግ ማዕቀፎች መዘጋጀታቸውንና አሁን ላይ በምዝገባ ላይ ላሉ አጋር ተቋማት የሥልጠና ሥራ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

የፎቶ ቅያሬን በተመለከተም በአጭር ጊዜ ውስጥ ዜጎች በምዝገባ ተቋማት በመሄድ ፎቶ መቀየር እንዲችሉ የሚያስችላቸውን ሥርዓት በመዘርጋት ላይ እንገኛለን ብለዋል።

- የፋይዳ ካርድ በድጋሜ ማሳተም ይቻላል?
- የጣትና የአይን አሻራ የሌላቸው ዜጎች መመዝገብ ይችላሉ ?
- የጥሪ ማዕከላችሁ ይሰራል ? እና መሰል ከቲክቫህ ቤተሰቦች የተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል።

📱 የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ምክትል አስተባባሪ ራሄል አብርሃም ለቀረቡት ጥያቄዎች የተሰጡትን ምላሾች ይመልከቱ https://youtu.be/7cYEVy3sDd8

@thikvahethiopia
" ይህ ተግባር ሕዝብን ለማስተዳደር ሥልጣን ላይ ካለ አካል የማይጠበቅ አስፀያፊ ተግባር መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን " - የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ ፓርቲ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) በላከው መግላጫ ፤ " ባለፉት ጥቂት ቀናት በአዲስ አበባ ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች ላይ ወጣቶች በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች እየታፈኑ የት እንደገቡ ሳይታወቅ መሰወራቸውን ከቤተሰቦቻቸው እና ከተለያዩ አካላት ለመገንዘብ ችያለሁ " ሲል ገለጸ።

" ይኽን የመንግሥት ተግባር ይበልጥ አስከፊ የሚያደርገው እነዚህ ታፍነው የተወሰዱ ወጣቶች የት እንደሚገኙ አለመታወቅና ቤተሰቦቻቸውም በመንግሥት አካል የተያዘ ግለሰብ ሊገኙባቸው ይችላሉ የሚሏቸውን ቦታዎች ቢያስሱም ለማግኘት አለመቻላቸው ነው " ብሏል።

" በተጨማሪ አንዳንዶቹ ከተወሰኑ ቀናት መሰወር በኋላ በድንገት የት እንደነበሩ እንኳ መናገር በማይችሉበት ሁኔታ ውስጥ ሆነው ወደቤታቸው መመለሳቸው ነው " ሲል ገልጿል።

ፓርቲው " ይሕ ሕጋዊ መንገድን ያልተከተለ የመንግሥትን ተግባር በሕግ ተጠያቂ መሆን ያለበትን አካል በቁጥጥር ሥር ማዋል ሳይሆን በወንበዴ የሚፈፀም አይነት አፈና እንደሆነ እና ይኽም ሕዝብን ለማስተዳደር ሥልጣን ላይ ካለ አካል የማይጠበቅ አስፀያፊ ተግባር መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን " ብሏል።

አሁንም በዚህ አይነት አፈና ውስጥ ያሉ ወጣቶች እንዳሉ ፓርቲው ማረጋገጡን ቤተሰቦቻቸውም በከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ እንዳሉ ለማወቅ እንደቻለ አመልክቷል።

ፓርቲው በዚሁ መግለጫው " መንግሥት አፍኖ የያዛቸውን ወጣቶች የት እንደሚገኙ ይፋ እንዲያደርግ " ሲል ጠይቋል።

" መንግሥት አፍኗቸው ያሉ ወጣቶች የወንጀል ተጠያቂነት አለባቸው ካለ ክሱን በግልጽ መሥርቶ እራሣቸውን የመከላከል መብታቸው እንዲያከብር አልያም በቶሎ እንዲፈታቸው " ብሏል።

" ያፈናቸውን ወጣቶች ቤተሰብ እንዲጎበኛቸው፣ የሕግ ጠበቃ እንዲቀርብላቸው እና አስፈላጊው ጥበቃ እንዲደረግላቸው "ም ብሏል።

ፓርቲው " ሕገወጥ ተግባሩን የፈፀሙ የመንግሥት አካላትን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽንን ጨምሮ ሌሎች የመንግሥት አካላትን በማሳተፍ ተጠያቂነት እና የሕግ የበላይነት እንዲሰፍን እንዲያደርግ እንጠይቃለን " ብሏል።

" ይህን አለማድረግ ግን ሥርዓት አልበኝነትን መጋበዝ፣ ለሕገወጥ ተግባራት ሽፋን መስጠት ብሎም ድጋፍ በማድረግ ቡራኬ እንደመስጠት እንቆጥራለን " ሲል ገልጿል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ጉዳዩን ተመልክቶ የሚመለከተውን አካል ተጠያቂ እንዲያደርግም ፓርቲው በመግለጫው ጥሪ አቅርቧል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@thikvahethiopia
THIKVAH-ETHIOPIA
“የባለስልጣናት ያልተገሩ ንግግሮችና የመንግስትም ተቀዳሚ ተግባሩን ፍጹም መርሳት ሕዝብን ለእልቂት እየዳረገ ነው”- ፓርቲው እናት ፓርቲ ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ ባወጣውና ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መግለጫ፣ “መልኩንና ቦታውን እየቀያየረ መላ ኢትዮጵያውያንን የደኅንነት ዋስትና ያሳጣው ሀገራዊ እልቂት አሁን አሁን ወደ ሀገራዊ ቀውስነት እያደገ ነው ለማለት ያስደፍራል” ሲል ተችቷል። አክሎ፣ “ለዚህ…
#Update

በጅማ ዞን ጌራ ወረዳ በተፈጠረው ችግር የተፈናቀሉና ቤት ንብረታቸው ለተቃጠለባቸው ሰዎች ልዩ ትኩረት እንዲሰጥ፣ በጥቃቱ የተሳተፉት አካላትም ለሕግ እንዲቀርቡ እናት ፓርቲ አሳሰበ።

ወደ 10 ሺሕ ወገኖችን የከፋ ዞን በቀናነት ተቀብሎ እንዳስጠለለና የተወሰኑት ወደ ቄያቸው እየተመለሱ እንደሆነ መገንዘቡን፣ ተፈናቃዮችን ወደ ቄያቸው የመመለሱን ተግባር በመልካሙ እንደተረዳው፣ ይሁን እንጂ አሁንም ትኩረት የሚሹ ወገኖች እንዳሉ በላከንልን መግለጫ ገልጿል።

“ በአንጻሩ ቤት፣ ንብረት የተቃጠለባቸው በትምህርት ቤቶች ተጠልለው ስለሚገኙ፣ አሁንም አላስፈላጊ ወከባዎችና ‘ያላስረከባችሁት መሣሪያ አለ አምጡ’ በሚል ማንነት ተኮር ማሳደድ እየደረሰ እንደሚገኝ” አስረድቷል።

“እንዲያውም የተወሰኑ ሰዎች ተመልሰው ለመፈናቀል እየተዳረጉ መሆኑን፣ በግድያና ማቃጠል የተሳተፉ በውል ተጣርቶ ለፍርድ አለመቅረባቸውና ፍትህ አለመስፈኑ ችግር እንደፈጠረ፣ ሕዝቡ ሀብትና ንብረቱን ስላጣ ለረሃብ እንደተጋለጠ ለመረዳት ችለናል” ነው ያለው።

“ ስለሆነም አሁንም በአቅራቢያ የሚገኘው የመከላከያ ኃይል የማረጋጋቱን ሥራ ወስዶ እንዲሰራና ቤታቸው ተቃጥሎ በድንኳንና ትምህርት ቤት የተጠለሉ ወገኖቻችን በአፋጣኝ የሚቋቋሙበት ሁኔታ እንዲመቻች በአጽንዖት እንጠይቃለን ” ሲል አሳስቧል።

የተፈጠረውን “ሞትና ከፍተኛ የንብረት ውድመት” ያስከተለ፣ “እጅግ አስከፊ ማንነት ተኮር ጥቃት” በማውገዝ የመከላከያ ኃይል ቦታውን እንዲቆጣጠረው፣ ተፈናቃዮች ወደ የቄያቸው እንዲመለሱ፣ “ወደ እልቂት የሚመሩ የባለስልጣናት ያልተገሩ ንግግሮች እንዲታረሙ” ከዚህ ቀደም ማሳሰቡን ፓርቲው አስታውሷል።

(የፓርቲው ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)
            
@thikvahethiopia
#MPESASafaricom

🪄 ዳታው በርክቷል! ወርሃዊ የዳታ ጥቅሎችን እየገዛን እስከ 25% የበለጠ ዳታ አግኝተን በየሄድንበት በፈጣኑ ኢንተርኔት ፈታ እንበል! 🥳

M-PESA ላይ ስንገዛ ሁሉም ቅናሽ አላቸው! 

በልዩ ልዩ አማራጮች የቀረበልንን የሳፋሪኮም የኢንተርኔት ጥቅል የM-PESA Appን በመጠቀም አሁኑኑ እንግዛ! በአስተማማኙ ኔትወርክ ዳታ እንንበሽበሽ!

#1wedefit
#Furtheraheadtogether
THIKVAH-ETHIOPIA
#Update " ከ3,000 ወጣቶች ወደ 130 የሚሆኑት ወጡ ተብሎ ዝም የሚባል ከሆነ ለቀሪዎቹ አደጋ ነው " - የወላጆች ኮሚቴ ሰርተው ለመለወጥ በሚል ከኢትዮጵያ የተሰደዱ ዜጎች በማይናማር በአጋቾች የከፋ ስቃይ እያሳለፉ በመሆኑ መንግስት ከስቃይ እንዲታደጋቸው በተደጋጋሚ መጠየቁ አይዘነጋም።  የወላጆች ኮሚቴ፣ ኢትዮጵያዊያኑ በታገቱበት የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው፣ አጋቾች ልጆቹን ዶላር ማጭበርበር…
#Update

🔴 “ መንግስት እንዲመጡ ስላላደረገ ከእገታው የወጡት ኢትዮጵያዊያንም በፓሊስ ተመልሰው እየተወሰዱ ነው። እስካሁን ሰባት ልጆች ተወስደዋል ” - ቤተሰብ

🔵
እኛ ዜጎች አይደለንም እንዴ? መንግስት ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ትዕዛዝ መስጠት አይችልም? ” - ኢትዮጵያዊ በታይላንድ

➡️ “ ልጆቻችን በረሃብ ሊያልቁብን ነው ” - የወላጆች ኮሚቴ

ሰርተው ለመለወጥ ሲሉ ተታለው ወደ ታይላንድ የተሰደዱና በታጣቂዎች በማይናማር ታግተው ቆይተው የወጡና አሁንም በእገታ ያሉ ኢትዮጵያዊያን መንግስት እንዲደርስላቸው በተደጋጋሚ መጠየቁ ይታወሳል።

በሺዎች ከሚቆጠሩት ኢትዮጵያዊያን ታጋቾች ውስጥ 13ዐ የሚሆኑት ከሳምንታት በፊት ከእገታ እንደተለቀቁ፣ ሌሎች በርካቶች ደግሞ ገና ከእገታው እንዳልወጡ፣ የወጡትም ሆኑ ያልወጡት የመንግስትን ድጋፍ እየተጠባበቁ መሆኑን መረጃ አድርሰናችሁ ነበር።

በታይላንድ ያሉ ኢትዮጵያዊያኑ አሁንስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አሉ ?

“ ከመግደል ያላነሰ ድብድባ ነው የሚካሄደውኮ። እኛ ዜጎች አይደለንም እንዴ? መንግስት ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ትዕዛዝ መስጠት አይችልም ?

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ታይላንድ በረራ እንዳለው እያየን ነው። እሺ ገበያውም አይዘጋበት ቢያንስ ሰው ይዞ ወደ ታይላንድ መጥቶ ሲመለስ የተወሰኑ ሰዎችን እየቀላቀለ ቢመልሰን ማቃለል አይችልም ? 

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኛ አይደለም እንዴ ? ለሥራ ብለን ነው የመጣነዎኮ ስለተቸገርን ገንዘብ ለማግኘት። ገንዘብ ይዘን ደግሞ ወደ ሀገራችን ለመመለስ። 

‘መንግስት አላችሁ?’ ተብለን እስከምንጠየቅ መድረሳችን በጣም ያሳፍራል። የኢትዮጵያ መንግስት ለሌላ አገር ‘ገንዘብ ረዳሁ’ ብሎ ከሚያወራ እዚህ ያሉትን ዜጓቹን አያስወጣም እንዴ ? 

እኛስ መቼም ምግብ ባይቀርብልም ከነበርንበት ሁኔታ አንጻር ምንም አይመስለንም። ትኩረት የሚሹት በማይናማር ከእገታ ያልወጡት እኛ ባለን መረጃ ብቻ እንኳ ከ400 በላይ ለሆኑ ኢትዮጵያዊያን ነው። እነርሱ የሚወጡት ደግሞ እኛ ቦታውን ስንለቅላቸው ነው።

እኛ ማይናማር ቦርደር ላይ ነው ያለነው። ሞኤ የሚባል ወንዝ እንደተሻገን። በጣም ሐበሻዎች አሉ። ከአንድ ካምፓኒ ብቻ እስከ 500 የሚደርሱ ሐበሻዎች አሉ።

አብዛኛው ኢትዮጵያ ያለበት አንዱ ካምፓኒ ‘ወደ ሌላ ቦታ እንስዳችኋለሁ’ እያለን ነው። ሌላ ቦታ የሚወስደን ሁሉንም ነገሮች ቁጥጥሩ ለማድረግ ነው። አሁን ያለንበት ቦታ ላይ ደኀንነታችን የተጠበቀ ነው። 

ማይናማር ግን ብዙ ሰው እየተጎዳ፣ እየተሰቃዬ ያለበት ፎረይን ፓሊሶች የሌሉበት አካባቢ ነው። ያለንበትን ካምፓኒ አቋርጠን ለመውጣት 2,500 ዶላር ይከፈላል። ያለንበት ግቢ እስከ 25 ካምፓኒዎች አሉ። ወደ ሌላ ግቢ ላለመሄድ ነው ጥረት እያደረግን ያለነው።

ሐበሾችን እየጠበቅን ነው ገና ከእገታ ያልወጡ ስላሉ። አመት ድረስ የቆዩ አሉ። በራሳችን ፈቃድ ስለማያስወጡን። 

እስካሁን ወደ ኢትዮጵያ ያልመጣንበት ዋነኛው ምክንያት ሙሉ ወጪ መሸፈን ስላማይችል ነው። 

ምክንያቱም ወደ ኢትዮጵያ መንግስት ደብዳቤ ልከው ከኢትዮጵያ መንግስት ምንም አይነት ምላሽ እንዳላገኙ ነው መረጃ የሰጡን። የታይላንድ መንግስት ለኢትዮጵያ መንግስት ደብዳቤ ልኳል። ግን እስከ ሳምንት ምላሽ አልተሰጠም።

ካለንበት ካምፕ ወጥተን ወደ ታይላንድ/ሜኢሶት ኤርፓርት ነው መሄድ ያለብን። ከታይላንድ መንግስት ጋር በመነጋገር ወንዝ ያሻግሩናል። ፓስፓርት የሌለው አንድ ወር መቆየት እንደሚችል ነው የተነገረው። 

የተጎዱ ሀበሿች፣ ጀርባቸው ላይ ለምጥ ያለ፣ የታመሙ፣ የተደበደቡ በሙሉ ካምፕ ነው ያሉት። እኛን ኢትዮጵያዊያንን ብቻ ነው ያልጠየቁን እንጂ ህንዶችን፣ ቻይናዎችን ‘አለንላችሁ’ የሚሉ አሉ። 

ምን እያደረጉ እንደሆነ የምናውቀው ነገር የለም። የምናውቀው ዘገባ እያደረጉና ዜግነታችንን ለይተው ብዙ ነገር እየጠየቁ እንደሆነ ነው። 

የኢትዮጵያ ዜጎች ብቻ ናቸው የቀሩት። ከኢትዮጵያ መንግስት ምላሽ ስላላገኙ። ምላሽ ቢያገኙ ይወጡ ነበር የሚቆዩበት ምክንያት የለም። ለኛም ስጋት የሆነው እነርሱ ባለመሄዳቸው የተነሳ ምናልባት የታይላንድ መንግስት ላይቀበለን ይችላል ” ሲሉ ተናግረዋል። 

የኢትዮጵያዊያኑ ቤተሰቦችስ በሰጡን ቃል ምን አሉ ?

“ ከእገታው ያልወጡ ኢትዮጵያዋያን ስቃይ ላይ ናቸው። ከእገታ ከወጡት 261 ዜጎች 138 ኢትዮጵያዊያ ናቸው። ከማይናማር ተነስተው ታክ በሚባል ካምፕ ነው ያሉት፤ ከቦርደሩ 82፣ ለባንኮክ 377 ኪሎ ሜትር ርቀት።

ቦታው አሁን ለደኀንነታቸው አስተማማኝ እየሆነ አይደለም። ምክንያቱም ከወጡት 261 የ18 ሀገራት ዜጎች በስምንት ቀናት ሁሉም ወደ ሀገራቸው ሂደዋል። የቀሩት የኢትዮጵያ ዜጎች ብቻ ናቸው።

ከእገታው እንደወጡ ኢንተርቪው ተደገው ነበር በዛው አካባቢው አካላት፣ የደረሰባቸውን ስቃይ ተናግረው ነበር። ቃለመጠይቁን የሰሙ የታይላንድ ፓሊሶችም መልሰው ወስደዋቸዋል። መንግስት እንዲመጡ ስላላደረገ የወጡት ኢትዮጵያዊንም በፓሊስ ተመልሰው እየተወሰዱ ነው። እስካሁን ሰባት ልጆች ተወስደዋል። የተመለሰ የለም።

የሌሎቹ ሀገሪት ዜጎችም ኢንተርቪው ተደርገው የነበር፤ ነገር ግን ኤምባሲዎች ሂደው በቀናት ውስጥ ነው የወሰዷቸው። 138ቱ ኢትዮጵያዊን ከእገታው ቢወጡም ወደ ኢትዮጵያ ስላልወጡ አደጋ ላይ ናቸው።

በታይላንድ ካምፕ ላይ ያሉት 138፣ በሌላ ጉዳይ ምክንያት በታይላንድ ፓሊስ ቁጥጥር ስር የሚገኙ፣ ገና ቦርደር ላይ እየጠበበቁ ያሉ 100 በአጠቃላይ 259 ኢትዮጵያዊያን ስም ዝርዝራቸው እንደተላከለት ውጪ ጉዳይ ነግሮናል።

በስም ዝርዝራቸው መሠረት መረጃዎችን እያደራጀ እንደሆነ ቢገልጽልንም እስካሁን ድረስ ግን ምንም አይነት ተጨባጭ የሆነ በኢትዮጵያ መንግስት በኩል የተሰራ ነገር የለም።

የወጡት ኢትዮጵያዊያን ከኢትዮጵያ መንግስት የሚጠብቁት ምን እንደሆነ፥ የአገልግሎት ጊዜው ያለቀ ፓርፓርት ያላቸው ልጆች ስላሉ ማንንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ ወደ ታይላንድ መንግስት እንዲልክላቸው፣ የበረራ ትኬቶች እንዲስተካክልላቸው ነው” ብለዋል።

የወላጆች ኮሚቴ በበኩሉ ፦

“ የታይላንድ መንግስት ‘ዜጎቻችሁን ውሰዱ’ ካለ በኋላ ብዙ ሀገራት ልጆቻቸውን አስወጥተዋል። የኢትዮጵያ ልጆች ግን እየተሰቃዩ ነው ያሉት።

የተወሰኑት አምልጠው ሲወጡ ተከትለው ለወጣት የምከሩ ኢትዮጵያዊያን ማይናማር በወታደሮች ካምፕ ታጉረዋል። ከእገታ የወጡት ወደ ሀገቸው ስላልመጡ ሌሎች ያልወጡት ታጋቾችም እየተሰቃዩ ነው።

አሁንም ወታደራዊ ካምፕ ያሉ ኢትዮጵያዊያኑ ብቻ ናቸው። ምግብም እየተሰጣቸው አይደለም። ልጆቻችን በረሃብ ሊያልቁብን ነው። ልጆቹ ያልወጡበት ምክንያት ያገራችን መንግስት ባለመቀበሉ ብቻ ነው” ሲል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ ለምን ከእገታ የማጡት ኢትዮጵያዊንን በአፋጣኝ ማምጣትና የታገቱትን ወገኖች ለማስለቀቅ ለምን እንዳልተቻለ ለውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ጥያቄ ቢያቀርብም እስካሁን ምላሽ አላገኘም።

#ThikvahEthiopiaFamilyAA

@thikvahethiopia
" ሞባይል ስልክ ይዞ ወደ ቤተ ክርስቲያን መግባት በጥብቅ ተከልክሏል " - የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት

አገልጋዮች በቅዳሴና ለሌሎች መንፈሳዊ አገልግሎት ሰዓት ሞባይል ስልክ ይዘው ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዳይገቡ መከልከሉን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አስታወቀ።

ሀገረ ስብከቱ የዐቢይ ጾምን አስመልክቶ አገልግሎቱ እንዴት መከናወን እንዳለበት ከሁሉም ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ጸሐፊዎችና ሰባክያነ ወንጌል እንዲሁም ቄሰ ገበዞች ጋር ውይይት አድርጓል።

ውይይትቱን ተከትሎ ስምምነት ላይ በመደረሱ የተለያዩ መመሪያዎች ተላልፈዋል።

ከመመሪያዎች አንዱ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሚከናወኑ የጸሎተ ቅዳሴና ሌሎች መንፈሳዊ አገልግሎቶች የእጅ ሞባይል ስልክ ይዞ መግባት በጥብቅ የተከለከተለ መሆኑ ነው።

ይህም ጥብቅ ክልከላ ለሁሉም ገዳማትና አድባራት እንዲያውቁት የመመሪያ ደብዳቤ ተልኳል።

ሀገረ ስብከቱ ፤ " በኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እምነትና ሥርዓት መሠረት ቅዳሴ የሁሉም ጸሎታት ማጠናቀቂያ ፣ ቀራንዮ ላይ ምንገኝበት፣ የበጉ ሠርግ ላይ የምንታደምበት፣ የጌታችንን የአምላካችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን በአንድነት ለሓጢአት ሥርየት፣ ለነፍስ ሕይወት፣ ለሃይማኖት ጽንዐትና ለመንግሥተ ሰማያት መውረሻ ይሆነን ዘንድ የምቀበልበት ታላቅ የጸሎት ሰዓት ነው " ብሏል።

በመሆኑም " አላስፈላጊ የእጅ ስልክ አጠቃቀም ጎልጎታን ከሚያስረሱ ፣በረከትን ከሚያሳጡና ጸጋን ከሚያስወስዱ ድርጊቶች መካከል አንዱ በመሆኑ ተከልክሏል " ሲል ገልጿል።

መመሪያውን የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎችና ሰበካ ጉባኤያት ጥብቅ ክትትል በማድረግ እንዲያስፈጽሙ ታዘዋል።

@thikvahethiopia
“ አንዳንድ ጊዜ አደጋዎች ከተስፋፉ በኋላ የመደወል ሁኔታ አለ። በ939 ፈጥኖ መደወልም ያስፈልጋል ቶሎ ደርሰን እንድንቆጣጠር ” - ኮሚሽኑ

ዛሬ አዲስ አበባ ፤ ኮልፌ ቀራኒዮ፣ ወረዳ 2 በተለምዶ ካሬ ቆሬ ብቄላ መናፈሻ አካባቢ ተነስቶ የነበረው የእሳት አደጋ በሰው ላይ ጉዳት ሳያደርስ በቁጥጥር ሥር መዋሉን የእሳትና አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ንጋቱ ማሞ በሰጡን ቃል፣ “ እሳቱ ሙሉ ለሙሉ በቁጥጥር ስር ውሏል ” ብለዋል።

“ የፍራሽ መስሪያ የሚሆኑ (ቁርጥራጭ ጨርቅ) የመሳሰሉ ግብዓቶች መጋዘን ላይ ነው የእሳት አደጋው ያጋጠመው ” ያሉት አቶ ንጋቱ፣ የኮሚሽኑ ሰራተኞች፣ ህብረተሰቡ ባደረጉት ርብርብ እሳቱ ወደ መስጊድና መኖሪያ ቤት ሳይዛመት መቆጣጠር መቻሉን አስረድተዋል።

“ በእሳት አደጋው ሰው ላይ ጉዳት አልደሰም። የቀረው መረጃ በኢኮኖሚ ላይ የደረሰው ጉዳትና የአደጋ መንስኤ ነው። እሱን ከፓሊሶች ጋር ሆነን እያጣራን ነው ” ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል። 

የእሳት አደጋ እየተደጋገመ ያለበት ሁኔታ እየተስተዋለ ነው፤ ማህበረሰቡ ምን አይነት ጥንቃቄ ማድረግ አለበት ? ስንል ሳቀረብንላቸው ጥያቄ አቶ ንጋቱ፣ “ ትክክል ነው እሳት አደጋ የተደጋገመመበት ሁኔታ አለ። አሁን ያለንበት ወቅት ነፋሻማና ደረቅ አየር ነው ” የሚል ምላሽ ስጥተዋል።

“ እሳት እንዲከሰት ከሚያደርጉ ሦስት መሰረታዊ ጉዳዮች ውስጥ ሁለቱን አሁን ካለው የአየር ፀባይ እናገኛለንና መዘናጋትና ቸልተኝነት ዋጋ የሚያስከፍልበት ሂደት ስላለ ህብረተሰቡ በመኖሪያ፣ በስራ አካባቢ እሳትና የኤለክትሪክ ኃይል ምንጮችን ሲጠቀም ከወትሮው በተለዬ ሁኔታ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል ” ሲሉ አክለዋል።

“ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ ያድርግ። ከዚህ አልፎ ለሚያጋጥም አደጋ፥ አንዳንድ ጊዜ አደጋዎች ከተስፋፉ በኋላ የመደወል ሁኔታ አለ። በ939ኝን ፈጥኖ መደወልም ያስፈልጋል ቶሎ ደርሰን እንድንቆጣጠር” ሲሉ አሳስበዋል።

#ThikvahEthiopiaFamilyAA

@thikvahethiopia
Caption:

Empower Your Entrepreneurial Journey with Jasiri!

The Jasiri Talent Investor is calling all aspiring women entrepreneurs to join our 8th cohort. Seize this opportunity to transform your vision into reality, build your business from the ground up, and achieve the entrepreneurial success you've always dreamed of!

Apply today 👉 https://bit.ly/40Ai4oR

For more information @jasiri4Africa
የአውሮፓ የሻምፕየንስ ሊግ የመጀመሪያ ዙር ጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች የካቲት 25 እና 26 ይደረጋሉ!

ማን ይሆን ወደ ሩብ ፍፃሜ የሚደርሰው?

ሁሉንም የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎችን እና ምርጥ ምርጥ መዝናኛዎችን ያካተቱ ከ125 በላይ በአዲሱ ሜዳ ስፖርት ፓኬጅ!

🎊 ከጥር 5 እስከ መጋቢት 22 ባሉት ቀናት አሁን ካሉበት ከቤተሰብ ፓኬጅ ወደ ሜዳ ከፍ ሲሉ… እኛ ሜዳ ስፖርት ፓኬጅን እንመርቅሎታለን!

ፓኬጅዎን ያሳድጉ!
👇
https://bit.ly/3RFtEvh

#ChampionsLeagueAllonDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia #DStvSelfServiceET #StepUp
ከUK ገንዘብ በM-PESA እንቀበል 10% ስጦታ እና 1 ጊ.ባ ኢንተርኔት ተጨማሪ አሁኑኑ እናግኝ! *ቪዛ* ፣ *ማስተርካርድ* ወይም *አሜክስ ካርድ* በመጠቀም በካሽ ጎን በኩል እንላክ።

በምንዛሬ ተመን
*1 GBP = 172 ብር*

ካሽ ጎን ይህንን ሊንክ ተጠቅመን ማውረድ እንችላለን፡ https://play.google.com/store/apps/details?id=com.bankofabyssinia.cashgo

ገንዘቦን በዳሽን ባንክ እለታዊ ምንዛሬ ያግኙ + 10%ስጦታ ።

#MPESAEthiopia #MPESASafaricom
#Ethiopia #Somalia

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ ረፋድ በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ የሥራ ጉብኝት አድርገዋል።

ሁለቱ ሀገራት ገብተውበት ከነበረው የዲፕሎማሲ እና የፖለቲካ ውጥረት በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ መሆኑ ነው።

የሶማሊያው ፕሬዚደንት ሐሰን ሼክ መሐሙድም ቱርክ ሁለቱን ሀገራት አንካራ ላይ ካስማማች በኋላ ባለፈው ጥር 3 ቀን አዲስ አበባን ጎብኝተዋል።

አስከትለውም በአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ታድመው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር ተነጋግረዋል።

በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በጋራ በወጣው መግለጫ " ይህ ጉብኝት ባለፉት ጥቂት ወራት ውስጥ የተደረጉ ተከታታይ ግንኙነቶችን የተከተለ፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነትም ወደ መደበኛ ሁኔታ የሚመልስ ነው " ብሏል።

ሁለቱ መሪዎች ለጋራ ጥቅም ትብብራቸውን ለማጠናከር ቁርጠኝነታቸውን ስለማረጋገጣቸው እና በዲፕሎማሲያዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ትብብር " መተማመንን ማሳደግ አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል " ተብሏል።

የዚህ ጉብኝት እንደምታን በሚመለከት ቃላቸውን ለዶቼ ቨለ ሬድዮ የሰጡት ፤ በውጭ ጉዳይ ኢንስቲቲዩት የአፍሪካ ጉዳዮች የሥራ ክፍል ኃላፊ እና ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት ዶክተር ግዛቸው አስራት ፥ ሁለቱ ሀገራት መተማመን በሚያስችል ሁኔታ መነጋገር የሚችሉበት ዕድል እንደሚሆን ገልፀዋል።

" የቴክኒክ ቡድኑ (የአንካራ ስምምነት) ከሁለት ሳምንት በፊት አንካራ ላይ ተገናኝቶ ሲነጋገር ተመልክተናል። መስማማቶች እና መግባባቶች ላይ የደረሱበት፣ መተማመን በሚያስችል ሁኔታ ንግግሮች እያደረጉ ያሉበት ሂደት ነው " ብለዋል።

" የቱርክ መንግሥት አካባቢውን ካላስፈላጊ ውጥረት ታድጓል "  ያሉት ተመራማሪው እንዲህ ያሉ መልካም ልምዶች በዚህ ቀጣና ብዙም አይታዩም ብለዋል። ይህን መሳይ የውይይት፣ የድርድር እና የሰላም መንገዶች ሲታዩ ማመስገን ያስፈልጋል ብለዋል። 

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የጋራ ጥቅሞችን በማሳደግ፣ ሰላምና ደህንነትን በማስፈን እና የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን በማጠናከር ለዜጎቻቸውና ለሰፊው የአፍሪካ ቀንድ ቀጣና በጋራ ለመስራት ቁርጠኛ መሆናቸውም ጉብኝቱን ተከትሎ በወጣው የጋራ መግለጫ ላይ ተጠቅሷል።

ዶክተር ግዛቸው አስራት " ቀጣናዊ ትብብርን " የተመለከቱ ውይይቶች እንደሚኖሩ ገልፀዋል።

የዛሬውን ጉብኝት በሚመለከት አስቀድመው የወጡ ዘገባዎች ሞቃዲሾ ውስጥ ከፍተኛ የፀጥታ ጥበቃ መደረጉን ያመለክታሉ።
#DW

@TIKVAHETHIOPIA
" በአደራ የሰበሰብነውን ከ22 ሚሊዮን ብር በላይ ለተለያዩ አገር በቀል ግብረ-ሰናይ ድርጅቶች ለግሰናል " - ዳሽን ባንክ

ዳሽን ባንክ ዛሬ “ ሸሪክ ” የተሰኘውን ከወለድ ነፃ አገልግሎት የ7ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በዋና መስሪያ ቤቱ አክብሯል።

በዚህም ከደንበኞቹ በአደራ የሰበሰበውን ከ22 ሚሊዮን ብር በላይ ለተለያዩ አገር በቀል ግብረ-ሰናይ ድርጅቶች መለገሱን አስታውቋል፡፡ 

በዛሬው ዕለትም ለ31 ሀገር በቀል ግብረ ሰናይ ድርጅቶች የገንዘብ ድጋፍ መደረጉ ነው የተገለጸው።

በከወለድ ነፃ አገልግሎት ብቻ ከ1 ሚሊዮን በላይ ደንበኞች ማፍራት መቻሉ የተገለጸ ሲሆን፣ የአገልግሎቱ ቺፍ ኦፊሰር አቶ መስፍን በዙ ባደረጉት ንግግር አመኔታቸውን ለሰጡ ደንበኞች ምስጋና አቅርበዋል።

የካቲት 26/2010 ዓ/ም በአንድ መስኮት የተጀመረው አገልግሎት አድጎ ከ80 በላይ ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የሚሰጡ ቅርንጫፎችና ከ800 በላይ በሆኑ ቅርንጫፎች በመስኮት ለደንበኞቹ የተሟላ የባንክ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ተጠቁሟል።

በሱማሌ ክልል ለሚገኙ ሴት ስራ ፈጣሪዎች ከወለድ ነጻ በሆነ መንገድ 100 ሚሊዮን ብር ተዘዋዋሪ ብድር ማቅረቡን አስታውሷል።

" ሸሪክ " እ.ኤ.አ ህዳር 28/ 2023 በባህሬን ማናማ በተካሄደው 9ኛው የኢስላሚክ ሪቴል ባንክ ሽልማት ላይ “ጠንካራ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት በኢትዮጵያ የሚሰጥ ባንክ” በሚል አይ ኤፍ ኤ ከተሰኘው ድርጅት ዕውቅና ማግኘቱ ተገልጿል።

#ThikvahEthiopiaFamilyAA

@thikvahethiopia