Crohn's & Colitis Ethiopia
647 subscribers
52 photos
1 video
7 files
44 links
Crohn's & Colitis Ethiopia aims to serve as a hub for patients and families with IBD to learn, share and support eachother. Disclaimer: all information is for educational purposes only.
Questions? Talk to us at @IBDETHIOPIA
Download Telegram
ቃለመጠይቁ እንደጠቀምዎት እንዲሁም ጥያቄዎን እንደመለስን ተስፋ እናደርጋለን። አብራችሁን ለለነበራችሁ እንዲሁም እንግዳችንን ዳይተሺያን ትርሲት ደምሰውን ከልብ እናመሰግናለን!

የድምጽ ቅጂውን በመጪው እሁድ የምንለቅ ይሆናል።

በፕሮግራሙ ላይ ስለተጠቀሰው የምግብ ማስታወሻ መች ተመርቆ ለእናንተ እንደሚደርስ በቅርቡ የምንገልጽ ይሆናል።

ይከታተሉን!

መልካም ምሽት!
#ጤናረቡዕ

ዛሬ በጤና ረቡዕ የውይይት ገፃችን ላይ ስለ የአንጀት ቁስለት ህመምና የአመጋገብ ስርዓት እንድንወያይበት እንዲሁም ጥያቄዎቻችሁ በባለሙያዎች እንዲመለሱ የቀጥታ ስርጭት ፕሮግራም ይዘን መጥተናል።

እንደተለመደው ከምሽቱ አንድ ሰዓት ላይ የአንጀት ስፔሻሊስት የሆኑትን ዶ\ር ኃይለሚካኤል ደሳለኝ እንዲሁም የስነ ምግብ ህክምና ስፔሻሊስት የሆኑትን ዶ\ር ዘላለም ደበበን ይዘን ቀርበናል።

ስለባለሙያዎቹ በዝርዝር ከላይ በፎቶ አያይዘናል።

ከምሽቱ አንድ ሰዓት ላይ በቲክቫህ ማጋዚን ላይ ብቻ!

@tikvahethmagazine @ibdeth
ውድ ቤተሰቦቻችን
#ጤናረቡዕ ፕሮግራም ላይ ስለ አንጀት ቁስለት እና አመጋገብ ስርዐት ከ ዶ\ር ዘላለም ደበበ እንዲሁም ዶ\ር ሀይለሚካኤል ደሳለኝ ጋር የቀጥታ ስርጭት ቆይታ ነበረን።

የድምጽ ቅጂውን በዩትዩብ ገጻችን የለቀቅን ሲሆን ይህንን ማስፈንጠሪያ በመጫን መከታተል ይችላሉ።

እናመሰግናለን!

https://youtu.be/TXT4DFTlcoU
Forwarded from TIKVAH-MAGAZINE
#ጤናረቡዕ

ውድ የጤና ረቡዕ ተከታታዮቻችን በዚህኛው የጤና ረቡዕ የዝግጅት ምዕራፍ "ጤናማ የሆድ እቃ፣ ጤናማ አዕምሮ" በሚል ርዕስ ሳይንሳዊ መረጃዎችን ለተከታታይ ሳምንታት እናቀብላችኋለን፡፡

እንደሚታወቀው በአሁኑ የክረምት ወቅት በሀገራችን በተማሪዎችም ሆነ በሰራተኞች ዘንድ የተወሰነ የስራ መቀዛቀዝ የሚስተዋልበት ጊዜ እንደመሆኑ የአዕምሮ ጭንቀትና ድባቴ በርከት ያሉ ሰዎችን ያጠቃል፡፡ ይህ ደግሞ በተለያየ ስር የሰደደ ህመም ባጋጠማቸው ሰዎች ላይ በተወሰነ መልኩ ተባብሶ ይታያል፡፡

ለዚህም ለተከታታይ ሶስት ሳምንታት ስለ የአዕምሮ ጤናና የሆድ እቃ፣ እንደ የአንጀት ቁስለት ያሉ ስር የሰደዱ ህመሞችና የመድሃኒቶቻችው የጎንዮሽ ጉዳት በአዕምሮ ጤና ላይና የእነዚህ ስሜቶች ተግባሪያዊ ማሳያዎችና መፍትሄዎችን እንዳስሳለን፡፡

በአራተኛውና በመጨረሻው ሳምንትም ባለሞያ ጋብዘን በዚሁ ርዕስ ዙሪያ ከእናንተ የሚመጡልንን ጥያቄዎች በቀጥታ ስርጭት የምንመልስ ይሆናል።

በዚህ ሳምንትም፦

✔️ የአዕምሮ ጤናና የሆድ እቃ ጤና እንዴት ይገናኛሉ?

✔️ የሆድ እቃ ጠቃሚ ረቂቅ ተህዋሲያን ተፅዕኖ በአዕምሮ ጤና ላይ

✔️ ከአካባቢያዊ ሁናቴዎችና የአኗኗር ዘይቤ ተፅዕኖ በአዕምሮና በሆድ ዕቃ ጤና ላይ በሚሉት ርዕሶች ላይ ሳይንሳዊ ማብራሪያ ይዘን ቀርበናል፡፡

የበለጠ ለማንበብ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ https://telegra.ph/Healthy-Gut-Healthy-Mind-08-17

@tikvahethmagazine @ibdeth
እንኳን ለደብረ ታቦር (ቡሄ) በዓል አደረሳችሁ

ክሮንስ ና ኮላይተስ ኢትዮጵያ 🇪🇹
Crohn's and colitis Ethiopia 🇪🇹
Forwarded from TIKVAH-MAGAZINE
#ጤናረቡዕ ለህክምና ተማሪዎች!

የአንጀት ቁስለት ህክምና ተማሪ ስኮላር ፕሮግራም

ይህ የአንጀት ቁስለት ህክምና ተማሪ ስኮላር ፕሮግራም በአይነቱ ለየት ያለ ለህክምና ተማሪዎች የቀረበ ሲሆን፤ የውስጥ ደዌ እንዲሁም የአንጀት ጤና ስፔሻሊስት መሆን ለሚሹ ከአንደኛ እስከ አራተኛ አመት ህክምና ትምህርት ላይ ላሉ የተዘጋጀ ነው።

ይህ እድል በአለማችን ላይ ስላሉት ከአንጀት ቁስለት ህመም ህክምና ጋር የተያያዙ ጉድለቶች እንዲሁም ከዚህ ህመም ጋር ያሉ ወጣት እና ጎልማሳ ሰዎች ምን አይነት የህክምና ትኩረት ይፈልጋሉ የሚለውን ይዳስሳል።

መስፈርት

-ማንኛውም አመት ላይ ያለ የህክምና ተማሪ
-የአንጀት ጤና ስፔሻሊቲ የመማር ፍላጎት
-ከየትኛውም የአለማችን ክፍል

ፕሮግራም

- 90 በመቶ የወርሀዊ ውይይት ዝግጅት መሳተፍ
- በየወሩ ከሚደረገው ስብሰባ በኃላ ስለ ስብሰባው የሚጻፍ ጽሁፍ መሳተፍ\ማገዝ
- ከአንጀት ቁስለት ህመም ጋር የሚኖሩ ወጣቶች ጋር በቅርበት ስለሚያስፈልገው ልዩ ትኩረት መረዳት
- ከድርጅቱ የህክምና አማካሪ ቦርድ እና አመራር ጋር በቅርብ መገናኘት
- በአመት አንድ ጊዜ ለሚካሄደው የአንጀት ቁስለት ህመም ኮንፈረንስ በፈረንጆች አቆጣጠር 2023 አመተ ምህረት ላይ ወደ አሜሪካ የመጓዝ እድል (የጉዞ ድጋፍ እስከ 1000 የአሜሪካ ዶላር)

ስለፕሮግራሙ ዝርዝር ከላይ ተያይዟል።

ለማመልከት ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ

https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSfflOypTySxTtFYjoGKvbojfO2EV7-vKSMoyz2Kaf9OZv3srA/viewform

#ጤናረቡዕ ላይ ስትሳተፉ የነበራችሁ የህክምና ተማሪዎች @IBDETHIOPIA ላይ በመጻፍ የምስክር ደብዳቤ ማግኘት ትችላላችሁ።

@tikvahethmagazine @ibdeth
#quickfact

በዚህ ሳምንት ስለ አንጀት ቁስለት እና የወር አበባ ዑደት እንወያያለን። ከምንዳስሳቸው ነጥቦች ውስጥ:-

✔️የወር አበባ ምንድን ነው?
✔️የወር አበባ ዑደት እና የአንጀት ቁስለት ግንኙነት
✔️የወር አበባ የህመም ስሜት ለምን በአንጀት ቁስለት ህመም ታካሚ ሴቶች ላይ ሊብስ እንደሚችል

በቀጣይ ሳምንት ምን አይነት መፍትሄ እና አማራጮች እንዳሉት እንወያያለን።

ማስፈንጠሪያውን በመጫን በሰፊው ያንብቡ ።

https://telegra.ph/IBD--Menses-08-20
Forwarded from TIKVAH-MAGAZINE
#ጤናረቡዕ

የአመጋገብ ስርዓት እና የአይምሮ ጤና

[ በ @ibdeth የቀረበ ]

- አካላዊ ጤና እና የአመጋገብ ስርዓት ዘርፈ ብዙ ተዛምዶ አላቸው።

- ደካማ የአመጋገብ ሥርዓት ለወረደ ስሜት አንደኛው ምክንያት ሊሆን ይችላል፤ በሌላ ጎኑ ተገቢ የአመጋገብ ሥርዓት ጉልህ በሚባል ደረጃ የአዕምሮን ጤና ያሻሽላል።

- የአመጋገብ ስርዓታችን በሆድ እቃችን ውስጥ በሚገኙ ረቂቅ ተህዋሳት ላይ በሚያመጣው ተፅዕኖ የአዕምሮን ጤና ላይ በተላያየ መንገድ ተፅዕኖ እንደሚያሳድር የተለያዩ ጥናቶች አረጋግጠዋል።

- የዘወትር የማዕዳችን ሥርዓት፥ እንደ ትኩራት ማጣት እና በስሜት ግፊት ነገሮችን በማድረግ የሚገለጠውን Attention Deficit Hyperactivity Disorder/ADHD/ ያሉ የአዕምሮ ጤና ችግሮች ጋር ተያያዥነት አለው።

- ኦሜጋ-3 ፋቲ አሲድ በተላዩ ምግቦች ውስጥ የሚገኝ ንጥረ ነገር ሲሆን የተለያዩ የአዕምሮ ህመም ተጠቂዎች ላይ እራሱን ችሎ ወይም እንደ አባሪ መድኃኒት መጠቀም ስኬታማ ውጤትን አሳይቷል።

- የአመጋገብ ሥርዓታችን በተለያየ መንገድ የአዕምሮ ጤና ላይ ተፅዕኖ ያደርጋል። በአዕምሮ ምግቦች የበለጠጉ ምግቦችን መጠቀም ስኬታማ እና በእንፃራዊ መልኩ ደግሞ ቀላል በሆነ መንገድ የአይምሮ ጤናን ለማሻሻል እንዲሁም ከአይምሮ ህመም ለማገገም አይነተኛ መንገዶች ናቸው።

🔗 ተጨማሪ በ 👉 INSTANTVIEW ያንብቡ

@tikvahethmagazine @WriteforTikvahbot
Crohn's & Colitis Ethiopia
#quickfact በዚህ ሳምንት ስለ አንጀት ቁስለት እና የወር አበባ ዑደት እንወያያለን። ከምንዳስሳቸው ነጥቦች ውስጥ:- ✔️የወር አበባ ምንድን ነው? ✔️የወር አበባ ዑደት እና የአንጀት ቁስለት ግንኙነት ✔️የወር አበባ የህመም ስሜት ለምን በአንጀት ቁስለት ህመም ታካሚ ሴቶች ላይ ሊብስ እንደሚችል በቀጣይ ሳምንት ምን አይነት መፍትሄ እና አማራጮች እንዳሉት እንወያያለን። ማስፈንጠሪያውን በመጫን…
#quickfact

የወር አበባ ዑደትና የአንጀት ቁስለት               

ክፍል 2                  

ለማንበብ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ

https://telegra.ph/IBD--Menses-08-27
Our very own Dr. Armoniam Mulatu Teshome has graduated from medical school! He works in supporting our health awareness campaigns and is the mastermind behind most of our Amharic content. Happy graduation Dr!
Forwarded from TIKVAH-MAGAZINE
#ጤናረቡዕ

ጤናማ የሆድ እቃ፣ ጤናማ አዕምሮ

- ስር የሰደዱ ህመሞችና የአእምሮ ጤና

✔️ የተለያዩ ስር የሰደዱ ህመሞች ጭንቀት፣ ስጋት እና ድባቴን በመፍጠር በአንድ ሰው ህይወት ላይ እክልን ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡

✔️በሌላ በኩል ፣ የአእምሮ ጭንቀት ሁኔታ ሲከሰት የተለያዩ የስር የሰደዱ ህመሞች ምልክቶች እና የህመሞቹን መልሶ መቀስቀስ ሊያስከትል ይችላል፡፡

👉ከሁለቱ የቱም ይቅደም የቱ፣ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ጭንቀት፣ ስጋት እና ድባቴ በቀጥታ ስር የሰደዱ ህመሞችን ላያስከትሉ ቢችሉም ቀድሞ ለተፈጠረው ህመም አፀፋዊ ምላሽ ናቸው፡፡

👉ከጭንቀት፣ ስጋት እና ድባቴ በተጨማሪ ስር የሰደዱ ህመሞች ያለባቸው ሰዎች ሌሎች ተጨማሪ የስሜት ለውጦችን ሊያስተናግዱ ይችላሉ፡፡

ሆኖም ያጋጠመንን ህመም መቀበል የለት ተዕለት ኑሯችንን በተገቢው ሁኔታ ለማስኬድ፣ የሀኪማችንን ምክር በአግባቡ ተቀብሎ ለመፈፀም እና ጤናማ ህይወት ለመኖር ይረዳናል፡፡

🔗 ተጨማሪ ያንብቡ 👉 https://telegra.ph/NCDs--Mental-Health-08-31

#በቀጣይሳምንት

በቀጣይ ሳምንት እስካሁን ስንወያይበት በቆየንበት ጤናማ የሆድ እቃ፣ ጤናማ አዕምሮ በሚለው ዙሪያ ባለሙያ ጋብዘን፤ ከእናንተ የሚደርሱንንም ጥያቄዎች አካተን ሰፊ ማብራሪያን በቀጥታ ስርጭት ይዘን እንቀርባለን፡፡
በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ያሎትን ጥያቄ በ @IBDETHIOPIA ያድርሱን!

@tikvahethmagazine @ibdeth
#ቃለመጠይቅ #ጤናረቡዕ

ከስነ-አዕምሮ ባለሙያ ጋር

በጤና ረቡዑ ‹‹ ጤናማ የሆድ እቃ፣ ጤናማ አእምሮ›› በሚል ርዕስ ላለፉት ሳምንታት መረጃን ስናቀብላቹ ነበር፡፡
በቀጣይ ሳምንት በዚሁ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ከስነ-አዕምሮ ባለሙያ ጋር በቀጥታ ስርጭት ውይይት እናደርጋለን።

ከምንዳስሳቸው ርዕሶች ውስጥ:-
✔️ስር የሰደደ ህመም ከአእምሮ ጤና ጋር ያለውን ግንኙነት እንቃኛለን።
✔️የአንጀት ቁስለት ህመም እና ተመሳሳይ ህመሞች ያለበት ሰው እንዴት የስነ ልቦና ጤናውን መጠበቅ እንደሚችል እንወያያለን።
✔️የአእምሮ ጤናን ለመጠበቅ ቀን በቀን መተግበር ያለብንን የተለያዩ ተግባሪያዊ የስነልቦና የጤና ስልቶች በዝርዝር እናያለን።

በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ላይ እንዲብራራሎት የሚፈልጉት ጥያቄ አሎት?
@IBDETHIOPIA መልዕክቶን ይላኩልን፡፡ በቀጥታ ስርጭቱ ላይ ተገቢውን ማብራሪያ እና ምላሽ በባለሙያ እንዲሰጦ እናደርጋለን፡፡

👉 ከዚህ በተጨማሪም ከእንግዳችን ከስነ-አዕምሮ ባለሙያው ናትናኤል ጋር የአንድ ለአንድ የስነ-ልቦና ድጋፍና ምክክር ለሚፈልጉ የትና እንዴት ማግኘት እንደሚችሉ ከቀጥታ ስርጭቱ በሗላ የምናሳውቅ ይሆናል።

ይከታተሉን!

@tikvahethmagazine @ibdeth
Forwarded from TIKVAH-MAGAZINE
#ጤናረቡዕ

🟣ማስታወሻ

ዛሬ በጤና ረቡዕ የውይይት ገፃችን ላይ ስለ የሆድ እቃ ጤናና የአእምሮ ጤና እንድንወያይበት እንዲሁም ጥያቄዎቻችሁ በባለሙያ እንዲመለሱ የቀጥታ ስርጭት ፕሮግራም ይዘን መጥተናል።

ከቀኑ ሰባት ሰዓት ላይ የስነ-ልቦና ባለሙያ የሆነውን ናትናኤል ሰይፉን ይዘን እንቀርባለን።
ይከታተሉን!

በቲክቫህ ማጋዚን ላይ ብቻ!

@tikvahethmagazine @ibdeth
መልካም አዲስ አመት የክሮንስ እና የኮላይተስ ኢትዮጵያ ቤተሰብ!

ይህ ዓመት ለእርስዎ እና ለቤተሰብዎ የበለፀገ ዓመት ይሁንልዎ።

@ibdeth