FBC (Fana Broadcasting Corporate)
206K subscribers
68.1K photos
1.25K videos
23 files
57.7K links
This is FBC's official Telegram channel.

For more updates please visit www.fanabc.com
Download Telegram
አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ የአሜሪካ የሱዳን ልዩ መልዕክተኛን አነጋገሩ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ የአሜሪካ የሱዳን ልዩ መልክተኛ ቶም ፔርሎን ተቀብለው አነጋግረዋል።

በውይይቱ የሱዳን ግጭት ዘላቂ ፖለቲካዊ መፍትሔ እንዲያገኝ ለማድረግ በሚደረጉ ጥረቶች ዙሪያ ሀሳብ ተለዋውጠዋል።

በተመሳሳይ ከጃፓን የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳድር ሺሚዙ ሺንሱኬ ጋር የተወያዩት አምባሳደር ምስጋኑ፤ የኢትዮጵያ መንግስት ከጃፓን መንግስት ጋር በንግድ እና ኢንቨስትመንት ዘርፎች በጋራ ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡


https://www.fanabc.com/archives/271062
ፖል ፖግባ በ2025 ወደ ሜዳ ይመለሳል

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ፈረንሳዊው አማካይ ፖል ፖግባ ከቅጣት መልስ በፈረንጆቹ 2025 ወደ እግር ኳስ ሜዳ እንደሚመለስ ተገለፀ፡፡ የ31 ዓመቱ አማካይ ከማንቼስተር ዩናይትድ ወደ ጁቬንቱስ ካቀና በኋላ የተከለከለ ንጥረ ነገር ተጠቅሞ መገኘቱን ተከትሎ ለአራት አመታት በማንኛውም ዓለም አቀፋዊ ውድድሮች ላይ እንዳይሳተፍ ቅጣት ተላልፎበታል፡፡ ሆኖም ግን በፈረንጆቹ 2023 የተላለፈበት የአራት…

https://www.fanabc.com/archives/271122
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#የቅዳሜ ልዩ #90ደቂቃ በፖድካስት
ከጠዋቱ 2 ሰዓት ይጠብቁን !
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ሰራተኞች ደም ለገሱ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ሰራተኞች ደም ለግሰዋል።

ሠራተኞቹ ደም መለገስ የሰውን ሕይወት መታደግ መሆኑን ገልጸው፤ ሠራተኞቹ ኅብረተሰቡ ደም የመለገስ ባህሉን በማዳበር ለወገኑ አለኝታነቱን በተግባር እንዲያሳይ ጠይቀዋል።
ተቋማቱ የሥራ ርክክብ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን እና የአዲስ አበባ ከተማ መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን የሥራ ርክክብ ፈጸሙ። በርክክብ ሥነ-ስርዓቱ ላይ የአዳስ አበባ መንገዶች ባለስልጣንና ዋና ዳይሬክተር ሙዲን ረሻድ (ኢ/ር)፤ የመንገድ ዳር መብራቶች ከመንገድ መሰረተ ልማት ጋር ሲተዳደሩ መቆየታቸውን አስታውሰዋል። ነገር ግን የመንገድ ዳር መብራቶች አስተዳደር አዲስ ለተቋቋመው…

https://www.fanabc.com/archives/271132
የአክስቱን ልጅ በሸኔ ታግቷል በማለት ህይወቱ እንዲያልፍ ያደረገና ከወላጆቹ ገንዘብ የተቀበለው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአክስቱን ልጅ በሸኔ ታግቷል በማለት ህይወቱ እንዲያልፍ ያደረገና ከወላጆቹ ገንዘብ የተቀበለው ግለሰብ በ21 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ የምስራቅ ጉራጌ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ወንጀል ችሎት ወሰነ። የምስራቅ ጉራጌ ዞን ፍትህ መምሪያ ዐቃቤ ሕግ ያዕቆብ አሸናፊ በተባለ ግለሰብ ላይ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀጽ 539 (1)…

https://www.fanabc.com/archives/271135
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ከተቋማት ጋር በትብብር መስራቱን እንደሚቀጥል ገለፀ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ማህበረሰባዊ ለውጥ ለማምጣት ከተቋማት ጋር በትብብር መስራቱን እንደሚቀጥል አስታወቀ፡፡ ፋና እና ኤፍ ኤች አይ 360(FHI_360 ) የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ተራድኦ ድርጅት (ዩኤስ ኤይድ) በትብብር ያዘጋጁት ከጤና እና ማህበራዊ ጉዳዮች ጋር የተያያዙ የይዘት ስራዎችን ለማሻሻል የሚያስችል የአሰልጣኞች ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ በስልጠናው ማጠናቀቂያ የፋና…

https://www.fanabc.com/archives/271141
የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔን ለማስተናገድ የሚደረገው የቅድመ ዝግጅት ሥራ ተገመገመ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ እና የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ዝግጅት አስተባባሪ ብሔራዊ ኮሚቴ ሁለተኛ ዙር የዝግጅት ሥራ አፈጻጸም ግመገማ አድርጓል፡፡ በመድረኩ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሕብረት ዋና መስሪያ ቤት መገኛ እና አስተናጋጅ ሀገር እንደመሆኗ መጠን ዘንድሮ የሚካሄደውን የመሪዎች ጉባኤ በተሳካ ሁኔታ ለማዘጋጀት ዘርፈ ብዙ ዝግጅቶች…

https://www.fanabc.com/archives/271152
Live stream finished (1 hour)
የወባ በሽታ የመከላከል ጥረትን የሚደግፍ መድሃኒት ከቻይና ይገባል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በቻይና ኤይድ ፕሮጀክት በኩል ድጋፍ የተደረገ የወባ መድሃኒት በሚቀጥለው ሳምንት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገባ የጤና ሚኒስቴር ገለጸ። የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ከቻይና ኤምባሲ ሚኒስትር ካውንስል ዶ/ር ያንግ ዪሃን ጋር ተወያይተዋል። በውይይታቸውም የኢትዮጵያ እና የቻይና ትብብርና ወዳጅነት ከምንግዜውም በላይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል። ዶ/ር ያንግ፤ የዶክትሬት ዲግሪ…

https://www.fanabc.com/archives/271163