FBC (Fana Broadcasting Corporate)
206K subscribers
67.7K photos
1.22K videos
23 files
57.5K links
This is FBC's official Telegram channel.

For more updates please visit www.fanabc.com
Download Telegram
የሰው ሰራሽ አስተውሎት ዘርፍን ያስደነገጠው ዲፕሲክ የሳይበር ጥቃት ደረሰበት

ይፋ በሆነ አጭር ጊዜ ውስጥ ታዋቂነትን ያተረፈው የቻይና የቴክኖሎጂ ዲፕሲክ በደረሰበት የሳይበር ጥቃት ምክንያት አዳዲስ ተጠቃሚዎችን ለጊዜው መመዝገብ ማቆሙን አስታወቀ፡፡ የቴክኖሎጂ ዓለምን ያስደነገጠው የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቻትቦት “ዲፕሲክ” በአገልግሎቶቹ ላይ “ትልቅ ተንኮል አዘል ጥቃቶች” ደርሶብኛል ብሏል። አዲስ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ሞዴል የሆነው ዲፕሲክ ለተጠቃሚዎች ከተዋወቀ በኋላ የቴክ ኢንዱስትሪ ውስጥ ከፍተኛ ትኩረት አግኝቷል። ኩባንያው የቻትጂፒቲ…

https://www.fanabc.com/archives/280839
ዩክሬን የሩሲያ ነዳጅ ማጣሪያን በድሮን መታች

አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ዩክሬን በአንድ ሣምንት ውስጥ ሁለተኛውን የሩሲያ የነዳጅ ማጣሪያ በአራት ሰው አልባ አውሮፕላኖች መምታቷ ተሰምቷል፡፡ ከምስራቅ ዩክሬን በ800 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው የሩሲያ ክስቶቮ ከተማ የሚገኘውን የነዳጅ ማጣሪያ መምታቷን ነው ዩክሬን ያስታቀወቀችው። በዚህም ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ ተነግሯል። በማህበራዊ ድረ-ገጾች ላይ የተለጠፉ ቪዲዮዎች በኢንዱስትሪ ተቋም ላይ…

https://www.fanabc.com/archives/280843
በደቡብ ሱዳን በተከሰተ የአውሮፕላን አደጋ የ20 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ሱዳን ዩኒቲ ግዛት አነስተኛ አውሮፕላን ተከስክሶ የ20 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ። አውሮፕላኑ ከግዛቷ ተነስቶ ወደ ደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ ጁባ በማቅናት ላይ እያለ መከስከሱን የግዛቱ ኮሙኒኬሽን ሃላፊ ጋትዌች ባይፓል መግለጻቸውን ሬውተርስ ዘግቧል። በአደጋው ህይወታቸውን ያጡት የቻይናው ብሔራዊ ፔትሮሊየም ኮርፖሬሽን እና የደቡብ ሱዳን መንግስት ተቋም…

https://www.fanabc.com/archives/280846
ቅዱስ ጊዮርጊስ ወላይታ ድቻን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 17ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ወላይታ ድቻን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ ቀን 9 ሰዓት በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደ ጨዋታ አብዱ ሳሚዮ እና አማኑኤ ኤርቦ የቅዱስ ጊዮርጊስ ግቦችን አስቆጥረዋል፡፡ ውጤቱን ተከትሎም ፈረሰኞቹ ነጥባቸውን ወደ 28 ከፍ አድርገዋል። የ17ኛ ሳምንት…

https://www.fanabc.com/archives/280854
የርዕደ-መሬት ክስተትና አሁናዊ ሁኔታ…

አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአሁኑ ወቅት በአፋር አዋሽ ፈንታሌና ዱለሳ እና በኦሮሚያ ፈንታሌ ወረዳዎች ላይ የሚታዩትን ጂኦሎጂካል እንቅስቃሴ ከቀይ ባህር በሰሜን እስከ ሞዛምቢክ በደቡብ ባለው የምስራቅ አፍሪካ ስምጥ አካል እንደሆነ ይገለፃል፡፡ ይህ የርዕደ መሬት ሁኔታ በመስከረም ወር 2017 ዓ/ም ለተወሰኑ ቀናት ከተሰማ በኋላ ከታህሳስ ወር ጀምሮ በድግግሞሽ በመጠንና በመሬት…

https://www.fanabc.com/archives/280861
Live stream finished (43 seconds)
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የሰብዓዊ መብት ኮሚሽነር ሹመት

በአውሮፕላን አደጋ 20 ሰዎች ሞቱ
Live stream finished (1 hour)
የሩዋንዳ ፓትሪዮቲክ ፍሮንት (አር ፒ ኤፍ) ዋና ፀሐፊ ዌለርስ ጋሳማጌራ አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሁለተኛው የብልጽግና ፓርቲ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ የሩዋንዳ ፓትሪዮቲክ ፍሮንት (አር ፒ ኤፍ) ዋና ፀሐፊ ዌለርስ ጋሳማጌራ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡ ዋና ፀሐፊው ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የቱሪዝም ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ አቀባበል…

https://www.fanabc.com/archives/280881
ዓለም ባንክ ለማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ድጋፉን እንደሚቀጥል አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ዓለም ባንክ ኢትዮጵያ ተግባራዊ ላደረገችው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ፡፡ የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴ ከዓለም ባንክ የኦፕሬሽን ማኔጂንግ ዳይሬክተር አና ቢየርድ እና ከዓለም ባንክ የምስራቅ እና ደቡብ አፍሪካ ሀገራት ምክትል ፕሬዚዳንት ቪክቶሪያ ኩዋኩዋ ጋር ተወያይተዋል፡፡ በዚህ ወቅት ሚኒስትሩ በዓለም ባንክ በተገኘ ከ17…

https://www.fanabc.com/archives/280900
የሞሮኮ ብሔራዊ ነፃነት ሰልፍ ፓርቲ ተወካይ ሞሀመድ ሲዲቂ አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሞሮኮ ብሔራዊ ነፃነት ሰልፍ ፓርቲ ተወካይና የቀድሞው የሞሮኮ ግብርና ሚንስትር ሞሀመድ ሲዲቂ በብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባዔ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።

የፓርቲው ተወካይ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የሰላም ሚኒስትር መሃመድ እድሪስ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ቀደም ሲል የሩዋንዳ ፓትሪዮቲክ ፍሮንት (አር ፒ ኤፍ) ዋና ፀሐፊ ዌለርስ ጋሳማጌራ በብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወቃል፡፡

በጉባዔው ላይ ከ15 ሀገራት የተውጣጡ የጎረቤት ሀገራት እህት ፓርቲዎች እና የብሪክስ አባል ሀገራት እህት ፓርቲዎች 43 ከፍተኛ አመራሮች እደሚታደሙ ይጠበቃል፡፡

የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ ጉባዔ ከጥር 23 እስከ ጥር 25 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ “ከቃል እስከ ባሕል” በሚል መሪ ሐሳብ በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡

በአለምሰገድ አሳዬ
የቱርኪዬ ኤኬ ፓርቲ ምክትል ሊቀ መንበር አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቱርኪዬ ኤኬ ፓርቲ ምክትል ሊቀ መንበር ዛፈር ሲራካያ በብልጽግና ፓርቲ ጉባዔ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡

ምክትል ሊቀ መንበሩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

ቀደም ሲል የሞሮኮ ብሔራዊ ነፃነት ሰልፍ ፓርቲ ተወካይ ሞሀመድ ሲዲቅ እና የሩዋንዳ ፓትሪዮቲክ ፍሮንት (አር ፒ ኤፍ) ዋና ፀሐፊ ዌለርስ ጋሳማጌራ በብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ ጉባዔ ለመሳተፍ አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወቃል፡፡

በጉባዔው ላይ ከ15 ሀገራት የተውጣጡ የጎረቤት ሀገራት እህት ፓርቲዎች እና የብሪክስ አባል ሀገራት እህት ፓርቲዎች 43 ከፍተኛ አመራሮች እደሚታደሙ ይጠበቃል፡፡

የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ ጉባዔ ከጥር 23 እስከ ጥር 25 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ “ከቃል እስከ ባሕል” በሚል መሪ ሐሳብ በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡

በአለምሰገድ አሳዬ
የሞሮኮ ብሔራዊ ነጻነት ሰልፍ ፓርቲ ተወካይ ሞሃመድ ሲዲቂ ማን ናቸው...

አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ ማምሻውን አዲስ አበባ የገቡት የሞሮኮ ብሔራዊ ነጻነት ሰልፍ ፓርቲ ተወካይ ሞሃመድ ሲዲቂ ማን ናቸው...

የ68 ዓመቱ መሃመድ ሲዲቂ የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ከሃሰን ሁለት ዩኒቨርሲቲ አግኝተዋል።

በተጨማሪም በ1990 ከሚኒሶታ ዩኒቨርሲቲ በአግሪ ካልቸራል ኢኮኖሚክስ የዶክትሬት ዲግሪ አላቸው።

መሃመድ ሲዲቂ ከ1984 እስከ1990 በመምህርነት፣ ከ2005 እስከ 2021የሞሮኮ ሳይንስና ምርምር ማዕከል ዳይሬክተር እንዲሁም የሃሰን ሁለት ዩኒቨርሲቲ አግሮ ኢኮኖሚክስ ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር በመሆን አገልግለዋል።

ከ2021 ጀምሮም የግብርና፣ የአሳ ሃብት፣ የውሃ እና የደን ልማት ሚኒስትር በመሆን ማገልገላቸው ተመላክቷል።
የአልጄሪያ ብሔራዊ ነጻነት ፓርቲ ዋና ጸሃፊ አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአልጄሪያ ብሔራዊ ነጻነት ፓርቲ ዋና ጸሃፊ አብዱልከሪም ቤን መብሪክ (ፕ/ር) በብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ዋና ጸሃፊው ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ቀደም ሲል የቱርኩ ኤኬ ፓርቲ ምክትል ሊቀ መንበር ዛፈር ሲራካያ በብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባዔ ለመሳተፍ አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወሳል።

እንዲሁም የሞሮኮ ብሔራዊ ነፃነት ሰልፍ ፓርቲ ተወካይና የቀድሞ የሞሮኮ ግብርና ሚኒስትር ሞሃመድ ሲዲቂ እና የሩዋንዳ ፓትሪዮቲክ ፍሮንት (አር ፒ ኤፍ) ዋና ጸሃፊ ዌለርስ ጋሳማጌራ በብልጽግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባዔ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።

በጉባዔው ከ15 ሀገራት የተውጣጡ የጎረቤት ሀገራት እህት ፓርቲዎች እና የብሪክስ አባል ሀገራት እህት ፓርቲዎች 43 ከፍተኛ አመራሮች እደሚታደሙ ይጠበቃል፡፡

የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ ጉባዔ ከጥር 23 እስከ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ “ከቃል እስከ ባሕል” በሚል መሪ ሐሳብ በአዲስ አበባ ይካሄዳል።
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በኢትዮዽያ በሁሉም የአየር ጠባይ የሚያገለግሉ መንገዶች በስድስት አመታት ብቻ ከ126,000 ኪሎ ሜትር ወደ 170,000 ኪሎ ሜትር እንዳደገ ያውቃሉ?

በፌደራል መንግሥት የተሰሩ የአስፋልት መንገዶች ብቻ 26,722 ኪሎ ሜትር ያህል ሲሆኑ በአሁኑ ወቅት በተለያየ የአፈፃፀም ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

ከነዚህም መካከል የ63 ኪሎ ሜትር የጅማ-አጋሮ-በሻሻ የመንገድ ፕሮጀክት የሚገኝበት ሲሆን ወደ ታሪካዊው የጅማ አባጅፋር ቤተ መንግሥት የሚያዳርስ ዐበይት ከተሞችን የሚያገናኙ ሰፋፊ መንገዶች የተካተቱበት መንገድ ይገኛል። በጅማ እና አጋሮ ብቻ ከ20 ኪሎ ሜትር በላይ የከተማ መንገዶች የተለዩ የብስክሌት መጋለቢያዎች አካተዋል።

#PMOEthiopia
የዕለቱ የምንዛሪ ዋጋ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ