Ethio Verse
87 subscribers
57 photos
1 link
Read Design Share
@ethioverse
Download Telegram
Ethio Verse pinned a photo
ፍቅር የሚጠይቀው ብቸኛ ስጦታ ፍቅር ብቻ ነው፡፡
#Love #Ethiovese @nikodimos @ethioverse
የትም ስትሄድ በሙሉ ልብህ ሂድ፡፡
@ethioverse @nikodimos
ጠላቶቸች አሉህ
ካሉህ ጥሩ ነው ፤
ይሄ ማለት በህይወትህ የቆምክለት ጥሩ ነገር አለ ማለት ነው፡፡
@ethioverse @nikodimos
ፈገግታ የንዴት ማብረጃ ፤ የውበት ማድመቂያ ናት!!
#ethioverse #smile #ethiopia @nikodimos @ethioverse
ባለፈው ሕይወትህ ምንም ዓይነት
ውጣውረድ ብታሳልፍም
ዛሬ ላይ ግን የትናንቱ መከራህ ሃይል የለውም፡፡
ምክንያቱም ሕይወት ማለት አሁን ነውና፡፡
#Ethioverse #OprahWinfrey #Ethiopia
ወደፊቱን ጊዜ ስመለከተው የብርሃን ውጋጋኑ አይኔን ያቃጥለኛል፡፡
#Ethioverse #Ethiopia #oprah @ethioverse @nikodimos
ጉዞህን እስካላቋረጥክ ድረስ በቀስታ መሄድህ ችግር የለውም፡፡
ዋናው ነገር ከጉዞህ አለመቆምህ ነው፡፡
#Ethiopia @ethioverse @nikodimos
ተፈጥሮን በጥልቀት ተመልከት ያን ጊዜ ሁሉንም ነገሮች በተሻለ ትረዳለህ፡፡
#Ethioverse #Ethiopia #AlbertEinstein
#ለምንድነው_መኖር_የደከመህ??
.
ለምን መኖር ደከመህ? ለምን ህይወት ድግግሞሽ ሆነብህ? ለምን ራስህን ለማጥፋት ወሰንክ? በስደት ስላለህ? በህመም ስለሆንክ? ያሰብከው ስላልተሳካ? ያመንከው ስለከዳህ? አሞታለሁ ብለህ ለምን ታስባለህ? አበቦች ሲፈኩ እንደሚደርቁ ያውቃሉ፡፡ ግን እደርቃለሁ ብለው ሳይፈኩ አይቀሩም፡፡ ሰውም ሟች ነው ግን ሟች ነኝ ብሎ መተው የለበትም፡፡ ሁሉም ሰው በየመስኩ ያብብ፡፡ ወዳጄ እፅፍልሀለው አንተ አላስፈልግም ትላለህ እንጂ ያላንተ የማይሆኑ ብዙ ነገር አለ፡
☞ያላንተ የማይሞቅ ቤት አለ፡፡
☞ያላንተ የማይሳካ ህልም አለ፡፡
☞ያላንተ የማያምር ጨዋታ አለ፡፡
☞ያላንተ የማይደምቅ ቤት አለ፡፡
☞ያላንተ የማይነበብ ፅሁፍ አለ ይኸው ስላለህ ይህንን አነበብክ ታስፈልገናለህ፡፡

ይህቺ አለም ትልቅ ዳመራ ናት አንተ በዳመራው ስር ያለህ አንድ ችቦ ነህ አንተ ስትጠፋ የዳመራው ብርሀን ይቀንሳል፡፡ የቻልከውን ያህል ብራ አንተ ከነገሮች በላይ ነህ፡፡ በነገሮች አትረበሽ፡፡ እደግመዋለሁ ህይወት ልክ እንደ ክራር ጨዋታ ነው፡፡ አጨዋወቱን ያወቀ ጥሩ ሙዚቃ ይሰማል ያላወቀ ደግሞ ዝብርቅርቅ ጩኸቷን ለመስማት ይገደዳል፡፡ አሁንም እልሀለው ህይወት በደመነፍስ አትሄድም ስልቷን እወቀው፡

፡ በህይወትህ ትላንት ያለፈውን መጥፎ ህይወትህን መቀየር ማስተካከል መሰረዝ አትችልም፡፡ የምትችለው አምኖ መቀበልና ለተሻለ ነገ መስራት ነው፡፡ "መቀየር የማንችለውን ነገር መቀበል ማለት ተስፋ መቁረጥ ወይም መሸነፍ ማለት ሳይሆን አቅማችንን የምንችለው ነገር ላይ ማዋል ማለት ነው::"
በፍፁም ተስፋ አትቁረጥ ግን አቅምህን የምትችለው ነገር ላይ አውለው፡፡ ሳትኖር ለመሞት አትቸኩል ይሄ ማለት ሳትፅፍ ለማጥፋት ሞክር ማለት ነው፡፡
ታሪክህን ፃፍ እናንብህ፡፡
መልካም ኑሮ🙏

@Abysinia @ethioverse
ተፈጥሮን ከመታዘዝ ውጪ ልናዝዛት አንችልም
#ethioverse #ethiopia #neture
ተስፋችን እንዲቀጥል እና የተሻለ እንድንሠራ ጥረት ማድረግ አለብን፡፡
#Ethioverse #Ethiopia #kofiannan
የሰላም ቀን
#Ethiopia #Pagume #Ethioverse
ጳጉሜ ፪ የፍቅር ቀን
#Pagume #Ethiopia #Land_of_Origin @Ethioverse
ጳጉሜ ፫
የይቅርታ ቀን
#Ethiopia #Land_of_origin #Pagume3 @ethioverse
ጳጉሜ ፬
የመደመር ቀን

እኔ + አንተ + አንቺ = እኛ
#Ethiopia #Pagume #Land_of_origin @ethioverse