የአሚጎስ የገ/ቁ/ብ/ህ/ስ/ማህበር የ2017 በጀት አመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት እና የ2018 በጀት አመት እቅድን አጠቃላይ የማህበሩ ሰራተኞች ባሉበት በደማቅ ሁኔታ አካሂዷል፡፡
ቀን ሃምሌ 8፣ 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ "ስተይ ኢዚ" ሆቴል በተካሄደው የማጠቃለያ ስብሰባ የማህበሩ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ፍጹም አብርሃ እንደገለጹት "ይህ የበጀት አመት እንደቀደሙት ዓመታት ሁሉ በስኬት የተጠናቀቀ መሆኑን" አሳውቀዋል፡፡ በዚህ ዓመት የአባላት ብዛት ከመጨመር አኳያ ፤ የአባላት ተቀማጭ ገንዘብ እና ለአባላት የተሰጠ ብድር መጠን ከመቼውም በበለጠ በስፋት እና በጥራት የተሰራበት እና በተጨባጭም ውጤት የመጣበት መሆኑን አሳውቀዋል፡፡
በተጨማሪም ራዕያችን አሚጎስን እ.አ.አ በ 2030 አለምአቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የፋይናንስና ኢ-ፋይናንስ አገልግሎት አቅራቢ ተቋም ማድረግ መሆኑን ያስታወሱት ስራ አስፈጻሚው በ2018 ይህን መርህ በመከተል የአባላትን ፍላጎት ለማሳካት እና እርካታ ለመጨመር ከመችውም በበለጠ የምንሰራበት አመት መሆኑን አሳውቀዋል፡፡ የማህበሩ ሰራተኞችም በበኩላቸው የ2017 በጀት አመት የስራ አፈጻጸም ያኮራቸው መሆኑን ገልጸው በ2018 የተያዘውን እቅድ ለማስፈጸም ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
በዚሁ እለትም ማህበሩ በአመቱ የላቀ አፈጻጸም ያሳዩ ሰራተኞች እና የስራ ክፍሎችን የእውቅና እና የሽልማት መስጠት ስነስርአት አከናውኗል፡፡

👍32❤14👏9