ዳሰሳ አዲስ-Access Addis
7.6K subscribers
1.41K photos
131 videos
23 files
183 links
በዳሰሳ አዲስ ኅትመት እና ማስታወቂያ

ፊልም፣ ሙዚቃ፣ ኮንሰርት፣ የተለያዩ ኪነ-ጥበብ ቱርፋቶች፣ የታዋቂ ሰዎች ግለ ታሪክ እንዲሁም በወር አንዴ ጊዜ "ዙር ሰላሳ" የተሰኝች በመዝናኛው ዘርፍ ላይ ብቻ አትኩሮቷን ያደረገች ዲጂታል መፅሔት ተዘጋጅቶ ይቀርባል!

ለማንኛውም አስተያየት
👇

[email protected]

+251924312097

@InfoDasesaBot
Download Telegram
የተዋናይት ፍያት የማነ ገዓት ባህላዊ ስነ-ስርዓት!

በትግራይ ባህል መሰረት ገዓት ማለት ከሰርግ በፊት ለሙሽሪት የሚደረግ ባህላዊ ስርዓት ነው። ፍርያት ነገ በሸራተን አዲስ ሆቴል ጋብቻ ስነ-ስርዓት ትፈፅማለች።
@AccessAddis
የተማሪዎቹ ጉዳይ መረሳት የለበትም!

#BringBackOurGirls #BringBackOurStudents
ዙር ሰላሳ ዲጂታል መፅሔት ተመልሳለች!

የካቲት ወር ቅጽ2 ቁጥር2 የፊታችን ቅዳሜ ወደ እናተ የምትደርስ ይሆናል።
@AccessAddis
ኮረንቲ ፌስቲቫል!

የካቲት 14 እና 15 በደብረዘይት ኩሪፍቱ ሪዞርት ዋተር ፓርክ።
@AccessAddis
አሜሪካዊት የሆሊውድ ተዋናይትና የቴሌቪዥን ጋዜጠኛ ልጇን ‹‹ምኒልክ›› ብላ ስም አውጥታለች

የአፍሪካ ልጅ በሆነው የኢትዮጵያ ንጉሥ ዳግማዊ ምኒልክ ልጇን ስትሰይም መልእክቱ ...

"የጥበበኛ ልጅ እንዲሁም ታላቅ"

አሻራን ለማመላከት ነውም ብላለች።
ምንጭ፡ ጌቱ ተመስገን
@AccessAddis
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አርቲስት ሔኖክ ድንቁ ለፍቅረኛው ሜላት ነብዩ የጋብቻ ጥያቄ አቀረበላት።
@AccessAddis
#ጥቆማ
ሜዳ ቻት መተግበሪያ እና ሶደሬ ቲዩብ

ሶደሬ ቱዩብ ከሜዳቻት ጋር በመተባበር በርከት ያሉ የሃገኛ አዳዲስ ፊልሞችን በሜዳቻት መተግበሪያ አማካኝነት በክፍያ ማቅረብ ከጀመረ ቆየት ያለ ሲሆን ሲሆን ለ1 ሳምንት አዳዲስ አማረኛ ፊልሞችን በሜዳ ቻት መተግበሪያ በኩል በነፃ ማቅረባቸውን አስታውቀዋል ሜዳ ቻት መተግበሪያ ውስጥ በመግባት አዳዲስ የሃገችን ፊልሞች ይመልከቱ።
@AccessAddis
በተለያዩ መንገዶች ምነው? ምን ሆናችሁ? እያላችሁ ስትጠይቁን፣ መቼም ጠያቂ አያሳጣን እያልን በልባችን መደሰታችንን ልንደብቅ አንችልም።

ጠፋ ብሎ የተመለሰን ሰው "እጅ ከምን?" ማለት አይቀርምና እኛም ባዶ እጃችንን አልተመለስንም። ከተወሰነ የአቀራረብ ለውጥና ከአዳዲስ ነገሮችን ይይዘናል።

ዙር ሰላሳ ዲጂታል መፅሔት የካቲት ወር 12 እትም
መልካም ንባብ!
@AccessAddis
ዙር30-ቅጽ2-ቁጥር 2.pdf
2.3 MB
ዙር30-ቅጽ2-ቁጥር 2
ዙር ሰላሳ!!
የካቲት ወር አስራ ሁለተኛ እትም!!
ዲጅታል መፅሔት!!
በሐገርኛ ቋንቋ
@AccessAddis
@AccessAddis
የቴዲ አፍሮ ኢትዮጵያ ወደ ፍቅር ኮንሰርት የካቲት 14 በመስቀል አደባባይ።
@AccessAddis
ሱፐር ኤግል ድራይ ጅን
በአዲስ መልክ ከላቀ ጣዕም፣ ጥንካሬ፣ መዓዛ ጋር።
ይገባዎታል!
ማሳሰቢያ:- ከ 21 ዓመት በላይ ለሆኑ ብቻ
#Supereaglenewdrygin #gin #supereagle
የቴዲ አፍሮ ኮንሰርት የካቲት 14 በመስቀል አደባባይ ይካሄዳል!

ከደቂቃዎች በፊት የአርቲስቱ ማናጀር አቶ ጌታቸው ማንጉዳይ ከነገረኝ:

"ኮንሰርቱ ቅዳሜ የካቲት 14 ከ10 ሰአት ጀምሮ በመስቀል አደባባይ ይካሄዳል። ከውጪ የሚገቡትን የድምፅ ሲስተሞች እና መሳርያዎችን ወጪ ለመሸፈን ብቻ በጣም ትንሽ ክፍያ ይኖራል። ኮንሰርቱ ምንም አይነት ስፖንሰር አይኖረውም። አሁን ከማዘጋጃ ጉዳዮችን ጨራርሰን እየወጣን ነው። በሌሎች ከተማች ስለታሰበው ኮንሰርት ወደፊት እነግርሀለው።"

ምንጭ: ኤልያስ መሰረት
@AccessAddis
ድምፃዊ ያሬድ ነጉ ሰው ደብድቧል ተብሎ በቁጥጥር ስር ዋለ።

ባሳለፍነው ሳምንት ሐሙስ ጥር 28 ለሊት 8:30 ቦሌ ሸገር ህንፃ ላይ ሚውዚክ ሪቮልሽን በተባለ መዝናኛ ቤት ሚላ ሐዱሽ በተባለ ለግለሰብ ላይ ባደረሰው ጉዳት ተጠርጥሮ በፓሊስ ቁጥጥር ስር የዋለው።

ያሬድ ነጉ እና ሚላን ሐዱሽ በእለቱ እየተዝናኑ በነበረበት ሰዓት አለመግባባት መፈጠሩን እና አለመግባባታቸው ወደ ጠብ ተቀይሮ በአልኮል መጠጥ ያለው ጠርሙስ ሚላን ሀይሉ ላይ ያሬድ ጥቃት የፈፀመ ሲሆን ጥቃቱ የተፈፀመበት ግለሰብ ራሱን ሲስት ያሬድ ነጉም በዕለቱ በፓሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል ሲል ኢትዮፒካሊንክ የአይን እማኞችን ጠቅሶ ዘግቧል።

ያሬድ ከሐሙስ እለት ጀምሮ በፓሊስ ጣቢያ ጉዳዩን ሲከታተል ከቆየ በኃላ ጥቃት የደረሰበት ግለሰብ አገግሞ ከሆስፒታል ወደቤት በመግባቱ ያሬድም ቅዳሜ ዕለት ጉዳዩን በውጪ ሆኖ እንዲከታተል በ10ሺ ብር ዋስ ተፋቷል።
@AccessAddis
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኮረንቲ የሙዚቃ ፌስቲቫል በኢትዮጵያ የመጀመርያው የኤሌክትሮኒክ ሙዚቃ ዝግጅት ሲሆን በቢሾፍቱ ኩሪፍቱ ሪዞርት በአመት አንድ ጊዜ ይካሄዳል። ዝግጅቱ ለሁለት ቀናት የሚቆይ ሲሆን የተለያዩ ዲጄዎች ባማረ የስቴጅ ዲዛይን ታጅበው የኤሌክትሮኒክ ሙዚቃ እያጫወቱ ህዝቡን የሚያዝናኑበት ነው።

የዘንድሮው ዝግጅት የካቲት 14 እና 15 በቢሾፍቱ ኩሪፍቱ ዋተር ፓርክ ይካየዳል።
@AccessAddis
አንጋፋው አርቲስት ጀምበሬ በላይ አረፉ።

በመድረክ ትወና ከ40 ዓመታት በላይ ያገለገልሉት አንጋፋው አርቲስት ጀምበሬ በላይ አረፉ።

አርቲስቱ በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከ1949 እሰከ 1953ዓ.ም በያኔዉ የሀገር ፍቅር ማህበር በአሁኑ የሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት በመድረክ ትወና አገልግለዋል።

እንዲሁም ከ1953ዓ.ም እስከ 1988 ዓ.ም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር በመድረክ ትወና አገልግለዋል።

አርቲስት ጀምበሬ ከተወኑባቸዉ ሥራዎች መካካል የአዛውንቶች ክበብ፣ ኦቴሎ፣ የከተማዉ ባላገር፣ ሐምሌት፣ የዋናው ተቆጣጣሪ፣ የእጮኛዉ ሚዜ፣ የልብ ፅጌሬዳ፣ 1ዓመት ከ1 ቀን፣ የፌዝ ዶክተር፣ የእግር እሳት፣ የሚስጠር ዘብ፣ የድል አጥቢያ ጥቂቶቹ ናቸው።

በተጨማሪም የዘመቻው ጥሪ፣ አመል አለብኝ፣ ግራ የገባው ግራ፣ ያልተከፈለው እዳ የተሰኙ የቴሌቪዥን ድራማዎች ላይ ተውነዋል።

አርቲስት ጀምበሬ በላይ በ1933 ዓ.ም በቀድሞ አጠራር ጎጃም ክፍለ ሀገር የተወለዱ ሲሆን፣ የሁለት ሴት እና የአራት ወንድ ልጆች አባት ነበሩ።

ምንጭ ፦ ኢዜአ
@AccessAddis
የካቲት 14 እና 15 ኮረንቲ የኤሌትሮኒክስ ሙዚቃ ፌስቲቫል በኩሪፍቱ ዋተር ፓርክ።

መግቢያ ትኬቶች በቦስተን ደይ ስፓ ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ይሸጣሉ።

ቅድመ ትኬት ሽያጭ 500 ብር
በዕለቱ በር ላይ 800 ብር
@AccessAddis
ቴስ ኦፍ አዲስ!

ለ21ኛ ጊዜ የሚዘጋጀው ቴስት ኦፍ አዲስ የምግብ እና መጠጥ ፌስቲቫል የካቲት 14-15 በጉዮን ሆቴል ይካዬዳል።
@AccessAddis